ካርታው

ጁማማፕ የስደተኞች አገልግሎት ካርታ ፡ በአገር አቀፍ ደረጃ ፡ ለጥገኝነት ጠያቂዎችና ለአለም አቀፍ ጥበቃ ላገኙ ያነጣጠሩ አገልግሎቶች። የመድረኩ (የፕላትፎርሙ) ይዘቶች 22 ቋንቋዎች ይገኛሉ

በማዘጋጃ ቤቶች ወይም በበጎ አድራጎት ተቋማት የሚንቀሳቀሱ ፣ የሌሊት መጠለያዎች፣ የእናቶችና ህፃናት የቤተሰብ መኖሪያ ቤቶች፣  በማህበራዊ ድንገተኛ አደጋ ስርዓት ውስጥ ያሉ የአዋቂዎች ወይም አዛውንቶች ወይም የታመሙ ሰዎች ሆስቴሎች። እነዚህ አገልግሎቶች በተለይ ከጥገኝነት ጠያቂዎች ወይም ከስደተኞች መቀበያ ስርዓት ውጭ ለሆኑ ወይም ወደ መጠለያው መመለስ ለማይችሉ ስደተኞች ያነጣጠሩ ናቸው።

ሆስፒታሎች፣ ልዩ ክሊኒኮች፣ የበጎ ፈቃደኞች ማህበራት እና ድርጅቶች ነፃ መሰረታዊ እና፨ወይም ልዩ የመድኃኒት አገልግሎቶችን የሚያቀርቡ ድርጅቶች፣ የማህበረሰብና የጤና መመሪያ ለተቸገሩ ሰዎች የጤና ስርዓቱን በቀላሉ ተደራሽ ለማድረግ።

የጣሊያን ቋንቋ እውቀት፡ ጣሊያን ገብተው የመኖር መንገድን ለሚጀምሩ ሰዎች መሠረታዊ መሣሪያ ነው። የትምህርት ቤቱ ስርዓት እና ማህበራት ነጻና ብቁ የሆኑ የጣሊያን ቋንቋ ኮርሶችን ለመከታተል የተለያዩ እድሎችን ይሰጣሉ። ትምህርቶቹ በአዋቂዎችና በህፃናት ላይ ያተኮሩ ሲሆኑ በትምህርት ደረጃ የተከፋፈሉ ናቸው።

ለሥራ ምደባ ዓላማ ነፃ የመረጃ እና የመመሪያ ተግባራትን የሚያካሂዱ የሥልጠና አካላት ፣ የሠራተኛ ማህበራት ፣ ማህበራት ፣ የቅጥር ማእከላት (ሲፒአይ) እና የሥራ አቀማመጥ ማእከላት (COL) ። ከነዚህ በአንዳንዶቹ በኩል ወደ ሥራው ዓለም ለመግባት አስፈላጊ የሆኑትን የስራ ችሎታ ለማጠናከር ዓላማ ያላቸው ልምምዶችን እና፨ወይም የስራ ድጋፎችን ማግኘት ይቻላል።

አስተዳደራዊና የህግ ምክር የሚሰጡ አካላት፣ ማህበራት እና ድርጅቶች። ከዋና ዋናዎቹ ተግባራት መካከል፥ የክልል ኮሚሽኑ እምቢተኝነት ላይ ይግባኝ፤ ለአለም አቀፍ ጥበቃ ጥያቄ ለማቅረብ የታሪኮች መሰብስብ፤ ቤተሰብን መቀላቀል፣ ዜግነትና በመኖሪያ ፈቃዶች ላይ ምክር፦

ሆስፒታሎች፣ ክሊኒኮች፣ ድጋፍ የሚሰጡ መስኮቶች፣ የአድማጭ ማዕከላትና በጤና ጥበቃ ላይ የተካኑ ቡድኖች የተለያዩ አገልግሎቶችን ማግኘት በሚቻልባቸው ቦታዎች፣ ከእነዚህም መካከል፡ የስነ፡ልቦና ወይም የስነ፡አእምሮ ድጋፍ እና ከሐኪም የደረሰበትን ችግር የሚያሳይ ሕጋዊ ማረጋገጫዎች።

የአለም አቀፍ ጥበቃ ጥያቄ የሚቀርብበት የፖሊስ ዋና መሥሪያ ቤት ቦታዎች። ጥያቄውን ያቀረቡት ሰዎች ችሎት የሚካሄድባቸው ለአለም አቀፍ ጥበቃ እውቅና የክልል ኮሚቴዎች ቦታዎች። የቤተሰብ መገናኘት፣ ዜግነት እና ሌሎች አስተዳደራዊ ሂደቶች የሚጀምሩበት የስፖርተሎ ኡኒኮና የፕሬፌቱራ ቢሮዎች።

መሰረታዊ ፍላጎቶችን በነጻ የሚያከፋፍሉ ማህበራትና ተቋማት። በዚህ ክፍል ምግብ አዘጋጅተው የሚሰጡበትና ምግብ የሚከፋፈልባቸውን ቦታዎች ያመለክታል።

የጥቃት ሰለባ የሆኑ ሴቶችንና ታዳጊ ልጆቻቸውን ለመቀበል እና ለመደገፍ የተዘጋጁ መዋቅሮች። ሴቶችንና ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆችን የሚቀበል ቡድን፡ የባህል ልዩነቶችን እና የእያንዳንዷን ሴት ታሪክ በማክበር የድጋፍ መንገዶችን ማረጋገጥ የሚችል ባለብዙ ዲሲፕሊናዊ ክህሎቶችን ማረጋገጥ አለበት።

አካል ጉዳተኞች ከሌሎች ጋር በእኩልነት በህብረተሰቡ ውስጥ ሙሉ እና ውጤታማ ተሳትፎን የሚከለክሉት የአካል ጉዳተኞችና የባህርይ እና የአካባቢ እንቅፋቶች ባላቸው ሰዎች መካከል ያለው መስተጋብር ውጤት ነው።

ማህበራት

2726

ሙሉ አገልግሎት

3828

ከተማ

601

ጉዳዩ የሚመለከት ክፍል

ጋዜጣ

ከ ጁማማፕ ጋር ለመገናኘትና ወቅታዊ ጉዳዮችን ለማወቅ ለጋዜጣችን ይመዝገቡ፦

የእኛ አገልግሎቶች

ዕድል

ዜና

ጨረታዎች

እና ሌሎች ተጨማሪዎች

iscriviti alla nostra newsletter

*campi obbligatori

ኮርሶች እና እድሎች

ለጥገኝነት ጠያቂዎችና ለስደተኞች በነፃ የስልክ ቁጥር ያግኙን

ለኦፕሬተሮች መርጃዎች

የአውታረ መረብ ፕሮጀክቶች

Share on facebook
Share on twitter
Share on whatsapp
Share on telegram
Share on email
Please rate this translation:
Your rating:
Please give some examples of errors and how would you improve them: