ምግብ የሚበላበትና ምግብ የሚሰራጭበት

ጁማማፕለስደተኞች አገልግሎት በአገር አቀፍ ደረጃ ፡ ጥገኝነት ጠያቂዎችንና የዓለም አቀፍ ጥበቃን ላገኙ፡ አገልግሎቶች የሚሰጥ ካርታ ነው። የፕላትፎርሙ ይዘቶች 15 ቋንቋዎች ይገኛል። የካርታ ስራው በአንድ በኩል ጥገኝነት ጠያቂዎችንና የዓለም አቀፍ ጥበቃን ላገኙ፡ በክልላቸው ላይ የሚፈልጉትን አገልግሎት እንዲያገኙ ለማድረግና በሚያስፈልጋቸው ኣገልግሎቶች፦ ከህጋዊ ድጋፍ እስከ የጣልያን ቋንቋ ኮርሶች ፣ ሁሉ ግዜ መደበኛ ያልሆነ የመቀበያዎች ወይም መጠለያዎች፡ እንዲጠቀሙ የተዘጋጀ ካርታ  ነው። በሌላ በኩል ግን ጁሙማፕ የፍልሰት ክስተት አያያዝን በተመለከተ የተለያዩ ተዋንያንን ለማገናኘት ያለመ ነው፦ የሕጋዊ ጥበቃ አካላት አገልግሎት ኦፕሬተሮች ፣ ተቋማት ፣ የአካባቢ  ባለሥልጣኖች ፣ መደበኛ ያልሆኑ ቦታዎች ፣ ፈቃደኛ ማኅበራት ፣ ትምህርት ቤትና የጤና አገልግሎቶች ለማገናኘት ሲሆን ጁሙማፕ፡ በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኤጄንሲ – በዩኤንኤችሲኣር እና    ለጥገኝነት ጠያቂዎችና ስደተኞች በነጻ  ስልክ ቁጥርን (ኑሜሮ ቬርደ) የአርቺ ናስዮናለ ስ.ቁ. 800905570 / +39 3511376335 (Lycamobile) ድጋፍ የተዘጋጀ ፕሮጀክት ነው። ከ 10 ዓመታት በላይ የሠራ፣ ያለ ክፍያ፡ በነፃ ቁጥር መስመር በመላው አገሪቱ ውስጥ 35 በላይ ቋንቋዎችን ተርጓሚዎች በማካተት ነፃ የእርዳታና የምክር አገልግሎት ይሰጣል። ፕላትፎርሙ፡ ሁሉም እዲገለገሉበት የተዘጋጀ መሳርያ ሆኖ፡ ማሳደስና መጨመር ወይም ማዘመንና ማዋሃድ የሚችሉበት ቦታ ነው። በሚቀጥሉት ወራቶች  በፕልትፎርሙ ላይ የተመዘገቡት ኣካላት፡ የሚያንቀሳቅሷቸውን አገልግሎቶችና መረጃዎች በተናጥል ገብተው ማስተዳደር ይችላሉ። የስደተኞች ካርታ አገልግሎቶች ጥሩ ልምዶችን ለማካፈልና ለእኛ ቅርብ የሆኑትን ተገቢ አገልግሎቶች ለመለየት የሚያስችል የህዝብና የጋራ መጠቀሚያ መሳሪያ መሆን ይፈልጋሉ ፡፡

ከጁምማፕ ዓላማዎች መካከል፦

  • ለምትፈልገው ኣገልግሎት፡ በጣም የቀረበውን ቦታ ማግኘት (መኝታ የሚገኝበት፣ የሕግ ድጋፍ ፣ የጤና እንክብካቤ ፣ የሥነ-ልቦና-ማህበራዊ ድጋፍ ፣ የቋንቋ ትምህርት ቤት የት እንደሚገኝ); 
  • የሚሰጠውን ኣገልግሎትና ስራ ማሳወቅ (ሁሉም ኣካላት፣ የሕዝብና የግል፣ በማፑ ካልተካተቱ፡ የምዝገባ ሰነዳቸውን መላክ ይችላሉ);
  • ማጣቀሻዎችን በየግዜው ማዘመን ወይ ማደስ (ሁሉም በማፑ የተካተቱ ኣካላት፡ የአገልግሎቶቻቸውን መግለጫዎች ለማሻሻልና ለማዘመን መግብያ ይሰጣቸዋል);

ቀደም ሲል ያደረግናቸውን ማንኛውንም ነገር ዋጋ በመስጠት በመስመር ላይ ማስቀመጥ።

ለጥገኝነት ጠያቂዎችና ጥገኝነት ላገኙ በነጻ ስልክ የሚደውሉበት ቁጥር

ለጥገኝነት ጠያቂዎችና ጥገኝነት ላገኙ በነጻ ስልክ የሚደውሉበት ቁጥር, 800 905 570, (እንዲሁም በላይካ ሞባይል ለሚደውሉ: +39 3511376335 ) በአርቺ ብሔራዊ ማሕበር የውጭ ዜጎችና የጥገኞች ጽ/ቤት የሚተዳደር ሆኖ፡ ስደተኞችን ሕግን በሚመለከተ፣ በትርጉምና ከህብረተሰቡ የሚወሃዱበት መንገድ ለመድረስ የሚያስችል፡ ከመደበኛና ከሞባይል ስልኮች በነጻ መደወል የሚያስችል የስልክ ኣገልግሎት መዘርጋት ፈለገ።

አገልግሎቱ የተጀመረው እ.ኤ.አ. በ 2006 በ “ኢኳል ኢንተግራርሲ” ፕሮጀክት የሙከራ እንቅስቃሴ ነበር:   በ ANCI (የጣልያን ማዛጋጃ ቤቶች ማሕበር)ድጋፍና በሚኒስትሮች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት  በሚሰበሰበው የ 8 × 1000   የገንዘብ ድጋፍ ኣገልግሎቱን ቀጠለ ፡፡ እ.ኤ.አ. በ 2013/2014 ጽህፈት ቤቱ በቤተሰብ ውህደት አሰራሮች አያያዝ እና በዱብሊን II እና III ስምምነቶች የተሰጡትን አሰራሮች አያያዝ በተመለከተ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች “የትግበራ አጋር” ሆኖ እውቅና ተሰጠው ፡፡ በተጨማሪም ኡናር (UNAR) በ (እ.ኤ.አ. ሰኔ 2013 / ሰኔ 2015) ውል የፈረመ ሲሆን በዚህ በኩል አለም አቀፍ ጥበቃ አመልካቾችና  ለአለም አቀፍ ጥበቃ ላገኙ፡  በየትኛው የአድልዎ ጥቃት ላይ ጽ / ቤቱን ከጀርባው ልዩ ባለ ሙያተኛ ጋር በመሆን ኣገልግሎት እንዲሰጥ አደራ ብሎታል ፡፡

አገልግሎቱ ለብዙ ጥገኝነት ጠያቂዎችና ስደተኞች የማጣቀሻ ስፍራ መሆኑ የተረጋገጠ ነው ፣ በተለይም ከተቋሙ በቂ ምላሽ ባለመገኘታቸው ፣ ከመቀበያ ፣   ከሕግ ምክርና ድጋፍ አገልግሎቶች በጭራሽ ተጠቃሚ ላልሆኑ። ግዜውን እየጨመረ በሄደ ቁጥር፡ የስልክ ጥሪዎችን በማለፍ ኑሜሮ ቬርደ፡  ኣንድ ፕላትፎርም በማዘጋጀት በጥገኝነት ሕግ መስክ ተሰማርተው በቋሚ ለውጦች ጋር በሚታገሉ  ኦፕሬተሮች፣ ጠበቆችና የሕግ ባለሙያዎች መካከል የልምድ ልውውጥ መድረክም ሆኗል ፡፡ 

ኑሜሮ ቬርደ ለጥገኝነት ጠያቂዎችና ስደተኞች ከክፍያ ነፃ ስልክ ቁጥር ከሰኞ እስከ ዓርብ ከ 9.30 እስከ 17.30  መልስ ይሰጣል፡ እና በቀን ለ 24 ሰዓታት በብዙ ቋንቋዎች መልእክት የሚቀበል ማሽን ኣገልግሎት ላይ ኣውለዋል። 

 መይል: numeroverderifugiati@arci.it

Materiali