ከዲሴምበር 6 – 2021 እስከ ጃንዋሪ 15 – 2022 ድረስ የሚጸኑ አዲስ ህጎች:
አረንጓዴ ማለፊያው ተጠናከረ (ሱፐር ግሪን ፓስ በመባል ይታወቃል) – ማነው የሚያገኘው?
- የክትባቱን ዑደት ያጠናቀቀ
• ከኮቪድ – 19 ተፈውሶ የዳነ
መሰረታዊ አረንጓዴ ማለፊያ፡ ማን ሊያገኘው ይችላል?
- መደበኛ ምርመራ (ታምፖነ)የሚፈጽም
የሱፐር አረንጓዴ ማለፊያና መሰረታዊ አረንጓዴ ማለፊያ ኣገልግሎት
የሱፐር አረንጓዴ ማለፊያው ከክትባቱ የመጨረሻ ቀን ወይም ከህክምና የምስክር ወረቀት ከተሰጠበት፡ ለ9 ወራት ያገለግላል።
መሠረታዊው አረንጓዴ ማለፊያ በሞለኪውላር ምርመራ ከተመረመረ ለ72 ሰዓታት ያገለግላል፣ በአንቲጂኒክ ምርመራ ደግሞ ለ48 ሰዓታት ያገለግላል።
በሕዝብ ማመላለሻ ላይ ያሉ ኣዳዲስ ሕጎች
በከፍተኛ ፍጥነት ባቡሮችና አውሮፕላኖች፣ የክልል የባቡር ትራንስፖርት (በኢንተርሲቲና በፔንዶላሪ ባቡሮች) ላይ ለመሳፈር፡ ቢያንስ ባለፉት 48 ሰዓታት ውስጥ ወይም ከዛ በፊት የተከናወነ ምርመራ አሉታዊ ውጤት (ነጋቲቭ) ያለው ማሳየት ግዴታ ነው።
አዲስ፡ የታምፖነ ምርመራ ፡ በአከባቢ የህዝብ ማመላለሻ (አውቶቡሶች፣ የከተማ ኣውቶቡሶችና የምድር ውስጥ ባቡሮች)ግዴታ ሲሆን፡ ክትትሎች እንዲሁ በዘፈቀደ የሚከናወኑ ናቸው። የሱፐር አረንጓዴ ማለፊያ ያላቸው በመደበኛነት መጓዝ ይችላሉ።
በዝግ ቦታዎች የጭምብል ኣጠቃቀም
በሁሉም አካባቢዎች ለሁሉም ግዴታ ነው
በክፍት ቦታዎች የጭምብል ኣጠቃቀም
በቢጫ፣ በርቱካናማና (ኣራንቾነ) በቀይ ዞን ውስጥ ግዴታ ነው፦ በሁሉም ቦታዎች ከእርስዎ ጋር መያዝ ግዴታ ነው።
በስራ ላይ እንዴት ይሰራል
ወደ ሥራ ለመሄድ፡ መሰረታዊውን አረንጓዴ ማለፊያ ማሳየት፡ ማለትም ሞለኪውላር ምርመራ (ለ 72 ሰዓታት የሚሰራ) ወይም አንቲጂኒክ (ለ 48 ሰዓታት የሚሰራ) ያድርጉ። ወደ ሜንሳዎች (ምግብ የሚበላበት) ለመግባት ግን የሱፐር አረንጓዴ ማለፊያን መያዝ ግዴታ ይሆናል።
በሥራ ቦታ የሚቆጣጠርና ቅጣት የሚፈጽም ማን ነው
በሥራ ቦታ ላይ ያለው ቁጥጥር ለውጥ የለውም። አሰሪዎች የሰራተኞችን መሰረታዊ የግሪን ማለፊያ መያዛቸውን የማረጋገጥ ሃላፊነት አለባቸው። ቁጥጥሩ በመግቢያው ላይ መከናወን አለበት፡ እና በናሙና መሠረት ሊከናወን ይችላል ። ደንቦቹን የማያከብሩ ሰዎች ከ 600 እስከ 1.500 ዩሮ የሚደርስ ቅጣት ሊቀጡ ይችላሉ። ቁጥጥር የማያደርጉ ከ 400 እስከ 1.000 ዩሮ ቅጣት ሊፈጸምባቸው ይችላል።
የሱፐር አረንጓዴ ማለፊያ የሌላቸው፡ በቡና ቤቶች፣ ምግብ ቤቶችና የምሽት ክለቦች የተከለከሉ ናቸው።
በነጩ ዞን ውስጥ እንኳን፡ ያልተከተቡ ሰዎች ወደ መጠጥ ቤቶች፣ በዝግ ወይም በቤት ውስጥ ምግብ ቤቶች፣ ግብዣዎች፣ ዲስኮዎች፣ ህዝባዊ ሥነ ሥርዓቶች እንዲሁም በስታዲየሞችና በየአደባባዩ ስፖርታዊ ዝግጅቶች ላይ መገኘት አይችሉም።
በምትኩ፣ በመዋኛና በጂሞች መደበኛ ምርመራ አድርገው አሉታዊ ውጤት (ነጋቲቨ) ያገኙ መሳተፍ ይችላሉ።
ማሳሰቢያ፡ በቀይ ዞን በአሁኑ ጊዜ ያልተከተቡ ሰዎች ላይ የሚተገበሩ ገደቦች የሱፐር ግሪን ማለፊያ ላላቸውም ተግባራዊ ይሆናሉ።
የበረዶ ሸርተቴ መገልገያዎች: አዲስ ደንቦች
በነጭና በቢጫ አካባቢ ደግሞ በመሠረታዊ አረንጓዴ ማለፊያ፡ በበረዶ መንሸራተት ይቻላል፡ በብርቱካናማ (አራንቾነ) ቦታ ላይ ደግሞ የሱፐር አረንጓዴ ማለፊያ ካለዎት ብቻ ወደ ቦታው መድረስ ይችላሉ።
በቀይ ዞን የበረዶ መንሸራተቻዎች ለሁሉም ዝግ ናቸው።