ክትባት የወሰዱ ፣ ነገር ግን በብሔራዊ የጤና ስርዓት ያልተመዘገቡ ፣ የኤሌክትሮኒክ መታወቂያ ካርድ ፣ የጤና ካርድ ፣ SPID ወይም IO የመተግበሪያ አፕሊኬሽን የሌላቸው ፣ ይህንን አሰራር በመከተል አረንጓዴውን ይለፍ ማውረድ ይችላሉ:
- ወደዚህ ጣብያ በመግባት https://www.dgc.gov.it/web/ “የጤና ካርድ” ላይ ጠቅ ያድርጉ;
- በሚታየው ማሳያ ገጽ ላይ እንደ ጉዳዩ ላይ በመመርኮዝ አማራጩን መምረጥ ያስፈልግዎታል “በጣሊያን ውስጥ በብሔራዊ የጤና ኣገልግሎት ክትባት ያልተመዘገበ ተጠቃሚ” (ወይም “የጤና ካርድ የሌለው ተጠቃሚ ወይም በውጭ አገር የተከተቡ” የ AUTHCODE ኮድ ካለዎት), የተለያዩ መስኮችን ይሙሉና “የምስክር ወረቀቱ ሰርስረው ያውጡ” የሚለውን ቁልፍ ጠቅ ያድርጉ ።
- “የግብር ኮድ ወይም በጤና ካርድ በተሰጠው” በመስኩ ላይ ይምሉ
ትኩረት ያድርጉ፡ የቁጥር ኮዱን ብቻ ሳይሆን የፊደላትን ቅድመ ቅጥያ ማስገባት አለብዎት (STP ወይም ENI) ለዚህም ኮዱ ከተለመደው የግብር ኮድ ጋር ተመሳሳይ ርዝመት እንዲኖረው ፣ አለበለዚያ የኮምፒተር ስርዓቱ ኮዱን ላያውቅ ይችላል።
ለምሳሌ: STP123456789 (ያለ ክፍተቶች ኮዱን ይምሉ)
ለምሳሌ: ENI123456789 (ያለ ክፍተቶች ኮዱን ይምሉ)
- ከዚያ በክትባት የምስክር ወረቀት ላይ ያለው ቀኑን ያስገቡ ።
- በሰርቲፊኬቱ ከተጻፈው ቋንቋ ከሚያሳየው አማራጭ በመምረጥ ጠቅ ያድርጉ።
- ኮዱን ይፃፉ (በየግዜው ሲገቡ ይለዋወጣል) ።
- አረንጓዴውን ይለፍ በፒዲኤፍ ቅርጸት ለማውረድ “የምስክር ወረቀት ሰርስረው ያውጡ” በሚለው ላይ ጠቅ ያድርጉ።
ያስተውሉ ፡ ክትባቱን ከተከተቡ ቢያንስ ከ 14 ቀናት በኋላ እንዲያካሂዱ እንመክራለን ፣ በሁለተኛ የክትባት መጠን ፣ 3- 4 ቀናት በቂ ሊሆን ይችላል።
ምንም እንኳን የአሰራር ሂደቱን ቢከተሉም ፣ አረንጓዴውን ማለፊያ ማውረድ ካልቻሉ ፣ እባክዎ ያነጋግሩ:
- ለጥገኝነት ጠያቂዎችና ጥገኝነት ላገኙ ከክፍያ ነፃ ቁጥር (ARCI)
800 905 570 – ለላይካ ሞባይል: 3511376335 - በኮቪድ – 19 አረንጓዴ የምስክር ወረቀት ላይ ለመረጃ እና ለእርዳታ : የህዝብ መገልገያ ቁጥር 1500 (በየቀኑ ለ 24 ሰዓታት ኣገልግሎት የሚሰጥ)
- በዚህ ሊንክ ፎርሙን በሞምላት a questo link ወይም በ 800 90 10 10 የነጻ ቁጥር በመደወል
ለኡናር (UNAR) (የዘር መድልዎን የሚቃወም ብሔራዊ ጽ / ቤት) ሪፖርት ይላኩ
(ምንጭ: Binario95 እና Avvocato di Strada)