[ITALIANO ] [UCRAINO – український] [RUSSO – РУССО] [INGLESE – ENGLISH]
- ጣሊያን እንደደረስክ፣ ወደ ድንበር ፖሊስ መሄድ
- • በማንኛውም ጊዜ በፖሊስ ዋና መሥሪያ ቤ ት – የኢሚግሬሽን ቢሮ (ጁማ ሊንክ ገብተህ ተመልከት)
1) ፍላጎትህን ግልጽ ማድረግ ለመጀመሪያ ጊዜ ፖሊስ ጣቢያ ስትሄድ ለጥገኝነት ማመልከት እንደምትፈልግ መናገር አለብህ ወይም ስምህን፣ የአባት ስምህን፣ የትውልድ ዘመንህን ወዘተ የምትጽፍበትን ወረቀት ኣዘጋጅተህ ጥገኝነት ለማግኘት ማመልከት እንደምትፈልግ በግልፅ መፃፍ ትችላለህ።
ፖሊስ ጣብያው ከተዘጋ ለጥገኝነት ለማመልከት ቀጠሮ በመጠየቅ ኢሜል (ብቻህን ወይም ከጠበቃ ጋር) መላክ ትችላለህ።
2) የፖሊሱ ዋና መሥሪያ ቤት ወረቀት ወይም ቸዶሊኖ (ማህተም እና ፊርማ ያለው) ይሰጥሃል፡ እንዲሁም “የጥገኝነት ጥያቄህ የምትሞላበት” የቀጠሮ ቀን ይሰጠሃል።
3) የጥገኝነት ማመልከቻውን ማቅረብና ፡ የ ቺ – 3 (C-3) ማዘጋጀት። ቺ – 3 ን (C-3) ከጨረስክ በኋላ ለ 6 ወራት የሚቆይና የሚታደስ የጥገኝነት ጠያቂ መኖርያ ፈቃድ መጠየቅ ትችላለህ፡ ይህን ፈቃድ ከተሰጠህ ከሁለት ወራት ቦኋላ መስራት ትችላለህ።
ጥንቃቄ!
ያለ የመግቢያ ቪዛ ጣሊያን ከገባህና ኣሻራ (ፎቶሰኛላሜንቶ) ካልወሰዱብህ፣ የፖሊስ ዋና መሥሪያ ቤት ሁለት ቀጠሮዎችን ሊሰጥህ ይችላል፡ የመጀመሪያው ኣሻራ ለመውሰድ፣ ሁለተኛው ቺ – 3 ለማድረግ።
ኣስታውስ፡ ቺ-3 ማለት የመኖሪያ ፍቃድ አይደለም፣ ግን ሁል ግዜ ካንተ ጋር ይዘሀው መሄድ አለብህ!
የጥገኝነት ማመልከቻውን ለማስገባት ምን ሰነዶች ያስፈልጋሉ?
ምንም ሰነዶች አያስፈልጉህም። በፖሊስ ጣቢያ የሚሰጡህን ቅጾች ትሞላለህ
ጥንቃቄ!
የመታወቂያ ሰነዶች ካንተ ጋር (ለምሳሌ ፓስፖርት) ካለህ ከ 4 ጉርድ ፎቶዎች ጋር ወደ ፖሊስ ዋና መስሪያ ቤት እንድትሰጣቸው ትጠየቃለህ።
ፓስፖርቱ በፖሊስ ዋና መሥሪያ ቤት ለሂደቱ በሙሉ ይቆያል።
በተመሳሳይ ጊዜ፣ ለጥገኝነት ማመልከቻህ ይጠቅማሉ ብለህ ያሰብከውን ሁሉንም ሰነዶች (ዲፕሎማዎች፣ ፎቶግራፎች፣ ጋዜጣ፣ መታወቅያ)፣ እድሜህን፣ ዜግነት ህን፣ ያረፍክበትን ሀገርና ቦታ የሚያመለከቱ ሰነዶችንና የጥገኝነት ጥያቄህን ምክንያት ጨምሮ ማስረከብ ይጠበቅብሃል።
በደንብ አስተውል
የት እንደምትኖር ለማወቅና ከሂደቱ ጋር የተያያዙ ሁሉንም ግንኙነቶች ላንተ ለመላክ አድራሻ ይጠየቃሉ። የጓደኞችህ እንግዳ ከሆንክ እና የእንግዳ ተቀባይነት መግለጫ ከሰጡህ፣ ካንተ ጋር ይዘህላቸው ሂድ!
የመቆያ ቦታ ከሌለህ በፕሬፌክተሩ ወይም በማዘጋጃ ቤቱ የሚተዳደር የህዝብ መቀበያ ማእከል የመግባት መብት አለህ፦ በዚህ ማእከል ውስጥ ለሂደቱ ጊዜ (ሂደቱ እስከሚያልቅ) የመቆየት መብት አለዎት።
አድራሻ ባይኖርህም ለጥገኝነት ማመልከት መብት አለህ!
ለጥገኝነት ካመለከትክ በኋላ የፖሊስ ዋና መሥሪያ ቤት ሰነዶቹን ወደ ግዛቱ ለሚመለከተው የክልሉ ኮሚሽን ይልካል (ብዙውን ጊዜ በእያንዳንዱ የጣሊያን ክልል ቢያንስ አንድ አለ) ።
የግዛት ኮሚሽኑ ከጥገኝነት ጠያቂዎች ጋር ቃለ መጠይቅ የሚካሄድበትና ለአለም አቀፍ ጥበቃ ማመልከቻ ውሳኔ የሚሰጥበት ቢሮ ነው።
በኮሚሽኑ ውስጥ ከሚደረገው የቃለ መጠይቅ ውጤት፣ የሚከተሉት ውሳኔዎች ማስተላለፍ ይችላሉ:
- የዓለም አቀፍ የስደተኛ (አዚሎ ፖሊቲኮ) ጥበቃ እውቅና፦ በዚህ ጉዳይ ላይ “ከፍተኛ” የዓለም አቀፍ ጥበቃ እውቅና አግኝተሃል፡, ምክንያቱም ወደ ትውልድ አገሩ በሚመለስበት ጊዜ እንደሚሰጋና አደጋ እንደሚያጋጥመው ይቆጠራል። በዚህ ውሳኔ ወደ ፖሊስ ዋና መሥሪያ ቤት በመሄድ ለ “ጥገኝነት” የሚሰጥ በየ 5 ዓመቱ የሚታደስ የመኖሪያ ፈቃድና ጥገኝነት ላገኙ የሚሰጠውን የጉዞ ሰነት ማግኘት ትችላለህ።
- የፕሮቴስዮነ ሱሲድያርያ ጥበቃን እውቅና መስጠት፦ ሌላው የአለም አቀፍ ጥበቃ አይነት ሲሆን ይህም በ 5 አመት የሚታደስ የመኖሪያ ፍቃድ የማግኘት መብት ይሰጠሃል።
- ልዩ (ፕሮቴስዮነ ስፔቻለ) ጥበቃን እውቅና፦: ይህ የ “ብሔራዊ” ጥበቃ ዓይነት ፈቃድ ነው፣ እና በፖሊስ ዋና መሥሪያ ቤት ውስጥ የ 2 ዓመት የመኖሪያ ፈቃድ፣ ታዳሽ እና ወደ ሥራ ሊለወጥ የሚችል፣ የማግኘት መብት ይሰጥሃል።
- ለሕክምና አስፈላጊነት ወይም ለጤንነት ችግር የሚሰጥ እውቅና: “ከባድ የስነ፡ልቦና፡አካላዊ ሁኔታዎች ወይም ከከባድ በሽታ” መኖሩን በሚታወቅበት ጊዜ ቢበዛ ለአንድ ዓመት ፈቃድ ይሰጠሃል፡ የሚታደስና ለስራ ምክንያቶች ፈቃድ ሊቀየር ይችላል።
- መከልከል (ዲኔጎ)፡ ኮሚሽኑ የአለም አቀፍ ወይም ልዩ ጥበቃ እውቅና ለማግኘት ሁኔታዎች አለመኖራቸውን ገምግሟል።
ጥንቃቄ!
ለአዲስ ቃለ መጠይቅ ልትጠራም ትችላለህ። ይህ ሊሆን የሚችለው ሙሉውን የግል ታሪክህ ለመረዳትና ውሳኔ ለመስጠት በቂ ካልሆነ ነው። መጨነቅ አያስፈልግም፣ ይህ ማለት ውስብስብ ጉዳይ ነው ማለት ነው!
በቃለ መጠይቁ ወቅት ሁል ጊዜ ያሉህን መብቶች፦
- ቃለ መጠይቁን አፍ በፈታህበት ቋንቋህ (ወይንም በደንብ በምታውቀው ቋንቋ )ወይም በገለልተኛ አስተርጓሚ እርዳታ መምራት;
- ለኮሚሽኑ የምታጋረው መረጃ ምስጢራዊነት – (ከሀገርህ ባለስልጣናት ጋር የማይጋራ);
- በጠበቃ መታገዝ;
- ከአስተርጓሚው ጋር ያለው አለመግባባት መናገር;
- እረፍት መጠየቅ;
- ከባድ ሁኔታዎች በሚያጋጥሙበት ጊዜ እንዲቋረጥ መጠየቅ (ለምሳሌ በጤና ምክንያት);
- ቃለ መጠይቁን እንደገና እንዲነበብልህ ማድረግና ማንኛውም ዓይነት እርማቶች የሚያስፈልጉ ከሆነ ማረም;
በንድፈ ሀሳብ፣ ማመልከቻህን ባቀረብክ በአንድ ወር ውስጥ ለአለም አቀፍ ጥበቃ ማመልከቻህ ምላሽ ማግኘት አለብህ። በተግባር ግን፣ ብዙ ጊዜ ሊወስድ ይችላል፣ እና በእርግጠኝነት ማወቅ አይቻልም።
አስተውል
ለሂደቱ በሙሉ የጥገኝነት ጠያቂ መኖርያ ፈቃዱ ባለቤት ሆነህ ትቆያለህ።
የኮሚሽኑ መልስ፡ እምቢተኝነት (“አሉታዊ”) ከሆነ፣ አሉታዊውን ውሳኔ ለፍርድ ቤት መቃወም (“ይግባኝ”) ማለት ትችላለህ። ሂደቱ እስካለ ድረስ፣ የ 6 ወር የጥገኝነት ጠያቂ ፈቃዱን ለማደስ መብት አለህ። ፍርድ ቤቱ የሚሰጠው የጥበቃ ዓይነት፦ (ዓለም አቀፍ ጥገኝነት (ኣዚሎ)፣ ንዑስ ጥበቃ (ፕሮቴስዮነ ሱሲድያርያ)፣ ልዩ ጥበቃ (ፕሮቴስዮነ ስፔቻለ)፣ ሕክምና(ኩረ መዲከ) እነዚህ እውቅናዎች መስጠት ወይም በአሉታዊ መልኩ ሊወስን ይችላል። ፍርድ ቤቱ አሉታዊውን መልስ ከሰጠህ፣ ለአለም አቀፍ ጥበቃ አዲስ ማመልከቻ ለማቅረብ መገምገም ትችላለህ (ለጥገኝነት ለማመልከት አዳዲስ ምክንያቶች ካሉ “እንደገና መድገም” (ሬተራታ) ይባላል), ወይም ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ። ትኩረት፥ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ማለት የፍርድ ቤቱን አሉታዊነት ወዲያውኑ አያግድም፣ ስለዚህ የመባረር ትእዛዝ እንዳይሰጡህ ስጋት አለ!
በቂ ገንዘብ ከሌልህ አሁንም ለጠበቃ ይግባኝ ማለት ትችላለህ፣ “ነጻ የህግ ድጋፍ” (ግራትዊቶ ፓትሮቺኞ)ተብሎ የሚጠራውን አገልግሎት በማግኘት ግዛቱ ለጠበቃው የሚከፍለው ይሆናል: በዚህ ጉዳይ ላይ ጠበቃው የገቢህን መጠን የምታረጋግጥበት ራሽን የምታዘጋጀው አንዳንድ ወረቀቶች እንድትፈርም ያደርጋል።
የታመነ ጠበቃ የማታውቅ ከሆነ ወደ አንተ ቅርብ ወደሚገኝ ፍርድ ቤት ሄደህ ያሉትን የህግ ባለሙያዎች ዝርዝር ማየት ትችላለህ፣ ከፈለግክ በአቅራብያህ የሚገኘውን የ አርቺ (ARCI) ክበብ ፈልግ፡ በአቅራቢያህ ወደሚገኙ የህግ ኣማካሪዎች ሊመራህ ይችላል። በ jumamap.it በከተማ ውስጥ የህግ አገልግሎቶችን ዝርዝር ማግኘት ትችላለህ።
ያለበለዚያ ለጥገኝነት ጠያቂዎች እና ለስደተኞች ነፃ የስልክ ቁጥር መደወል ትችላለህ። ከመደበኛ ስልክ (800 905 570) እና ከሞባይል ስልክ (3511376335) መደወል የሚቻልበት ነፃ የስልክ መስመር ሲሆን በዚህም የህግ ድጋፍ እና የማማከር አገልግሎት ማግኘት ትችላለህ።