አሰኞ ኡኒኮ ፋሚልያረ

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on telegram

አሰኞ ኡኒኮ ፋሚልያረ ማለት በአንዳንድ ሁኔታዎች በእያንዳንዱ ቤተሰብ ስር ለሚኖሩ ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆች 21 ዓመታቸው እስከሚደርሱ የሚሰጥ የኤኮኖሚ ድጋፍ ነው።   

ቸኩ ወይም አሰኞው የሚከፈለው  ከኢንፕስ በኢሴ (ISEE) ወይም የቤተሰብ የኤኮኖሚ ሁኔታ በሚያመላክተው መሰረት ነው። ድጎማውን ለማግኘት ቤተሰቦች ከጃንዋሪ 1 2022 ጀምሮ ለኢንፕስ (INPS) ወይም እንደ  ፓትሮናቶ ደጋፊ ተቋማት ማመልከት ይችላሉ። ተቆራጩ ከመጋቢት 2022 ጀምሮ INPS ይከፈላል። 

ቼኩን እስከ ጁን 302022 ድረስ መጠየቅ ይቻላል፣ እንዲሁም ላለፈው ወርሃዊ ክፍያ (ከማርች 2022 ጀምሮ) የማግኘት መብት አለው።

ለቼኩ ማን ማመልከት ይችላል

ለቼኩ ለማመልከት የሚከተሉትን መስፈርቶች ሊኖርዎት ይገባል ፦

 • የጣልያን ዜግነት፣ ወይም የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገር (ወይም የቤተሰባቸው አባላት) ዜግነት፣ ወይም የአውሮፓ ህብረት አባል ያልሆነ ዜጋ በመሆን የአውሮፓ ህብረት የመኖሪያ ፍቃድ የረጅም ጊዜ የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸው፤ ወይም ከስድስት ወር በላይ የሥራ እንቅስቃሴን ለማከናወን የተፈቀደ የሥራ ፈቃድ መኖርያ ፈቃድ የተሰጣቸው መሆን፤ ወይም በጣሊያን ውስጥ ከስድስት ወር ለሚበልጥ ጊዜ ለመቆየት በተፈቀደላቸው በምርምር ምክንያቶች የመኖሪያ ፈቃድ ባለቤት መሆን;
 • ጣሊያን ውስጥ የገቢ ግብር ክፍያ የሚያከናውኑ;  
 • በጣሊያን ውስጥ ቢያንስ ለሁለት ዓመታት መኖር ምንም እንኳን ቀጣይ ባይሆንም ወይም ቢያንስ ለስድስት ወር ቋሚ ወይም ቋሚ ያልሆነ የሥራ ውል ያላቸው

የቼኩ ባህሪያት 

 • ድጎማው ሁለንተናዊ ነው ሁሉም የገቢ ምንጮች መብት ኣላቸው ቀጣይ የገቢ ምንጭ (ISEE) በቀነሰ መጠኑ ይጨምራል።
 • ድጎማው አዲስ ልጅ ከተወለደ በ 120 ቀናት ውስጥ፣ ከተፀነሰ 7 ኛው ወር ጀምሮና ለእያንዳንዱ በቤተሰቡ ስር ያለ ልጅ እስከ 21 አመት ድረስ ሊጠየቅ ይችላል።
 • ዕድሜያቸው 18 በላይ ለሆኑ እና 21 ዓመት በታች ለሆኑ በቤተሰብ ስር ያሉ ልጆች ለድጎማው ብቁ ለመሆን ከሚከተሉት ሁኔታዎች ውስጥ አንዱን ማሟላት አለባቸው:
  • የትምህርት ቤት ሙያዊ ስልጠና ኮርስ ወይም የዲግሪ ኮርስ ለሚከታተሉ;
  • የስራ ልምድ ኮርስ የሚከታተልና አጠቃላይ ገቢ በዓመት 8000 በታች ነው;
  • ወይም እንደ ሥራ አጥነት ተመዝግቦ ከሕዝብ የሥራ ስምሪት አገልግሎት ጋር ሥራ እየፈለገ ነው;
  • ሁለንተናዊ ሲቪል ሰርቪስ ያካሂዳል።
 • ማመልከቻው አንዴ ከቀረበ በኋላ ቼኩ ከማርች ወር ጀምሮ  በማንኛውም ሁኔታ 60ቀናት ውስጥ ይታወቃል።
 • ቼኩ የሚከፈለው በዜግነት ገቢ ተጠቃሚዎች ካልሆነ በስተቀር በባንክ ሒሳብ ቁጥር (IBAN) ወይም በአገር ውስጥ የባንክ ሒሳብ ማስተላለፍ ነው።
 • ድጎማው አጠቃላይ የቤተሰብ ገቢን አይነካም።

ማሳሰቢያ: በማመልከቻው ጊዜ, ተመጣጣኝ ቼክ ለማግኘት የኢሴ (ISEE) የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይቻላል. የኢሴ የምስክር ወረቀት ሳይያያዝ ማመልከቻ ከገባ፣ ገቢ ምንም ይሁን ምን ኢንፕስ (INPS) አነስተኛውን መጠን ብቻ ይከፍላል።

የድጎማው ተኳኋኝነት ከሌሎች ማህበራዊ እርዳታዎች ጋር

ከማርች 2022 ጀምሮ፣ ድጎማው ልጆች ላሏቸው ቤተሰቦች ያነጣጠሩ አንዳንድ የመንግስት ኢኮኖሚያዊ ድጎማዎችን ይተካል።

 

 • አሰኞ ፋሚልያረው የወሊድ ጉርሻን (የነገ እናት ቦነስ) የወሊድ አበል (የህፃን ቦነስ) ኣሰኞ ፋሚልያረ (የቤተሰብ አበል) እና ከ21 አመት በታች ለሆኑ ከቤተሰብ የሚኖሩ ልጆች የሚቀነሱትን ይተካል። 
 • አሰኞ ፋሚልያረው ወይም የቤተሰብ የኤኮኖሚ ድጎማ፡ ከዜጋው ገቢና ከህፃናት እንክብካቤ ድጎማ ጋር ተኳሃኝ ነው።

ማሳሰቢያ፡ የዜግነት ገቢን አስቀድመው ከተቀበሉ፣ ኣሰኞ ፋሚልያረው ቀጥሎ ይቀበላል።

የቼኩን መጠን ማመሳሰል 

በዚህ ድረ ገጽ በመግባት ቼኩን፡ በኢንፕስ (INPS) ተመሳሳይ ኣሰራር ማስላት ይችላሉ።:

https://servizi2.inps.it/servizi/AssegnoUnicoFigli/Simulatore

ከአሰኞ ፋሚልያረው የተገለሉ ተጠቃሚዎች

በአሁኑ ወቅት፣ ቼኩን ለማግኘት ከተዘረዘሩት የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸው ውጪ አንዳንድ የዜጎች ምድቦች አሁንም አልተካተቱም። በዚህ ረገድ፣ ይህንን በሚመለከት ማንኛቸውም ለውጦች ካሉ፣ በዚህ ገጽ ላይ ይቀርባሉ።

እንዴት ማመልከት ይቻላል – ለማመልከት ወደ ኢንፕስ (INPS) ድህረ ገጽ መግባት አለባቹህ:

https://serviziweb2.inps.it/PassiWeb/jsp/spid/loginSPID.jsp?uri=https%3a%2f%2fservizi2.inps.it%2fservizi%2fAssegnoUnicoFigli&S=S

ወይም 803164 (ከመደበኛ ስልክ) ወይም 06164164 (ከሞባይል ስልክ) ይደውሉ ወይም በኢንፕስ 0 በታወቁ ፓትሮናቶዎች በኩል ይጠይቁ  https://www.inps.it/servizi-online/servizi-per-i-patronati/informazioni/gli-enti-di-patronato

 

ጣልያንኛ ስለማትናገሩ አስተርጓሚ ከፈለጋቹህ ለጥገኝነት ጠያቂዎች እና ስደተኞች ነፃ የስልክ ቁጥር (አርቺ ARCI) ያግኙን 800 905 570 ለላይካ ሞብይል፥ 3511376335 assegno unico
Pidgin English
Bambara
Pular
Soninke
Evidenza

የ2023 የህዝብ ውድድር ማሻሻያ፡ በምርጫው ውስጥ ስደተኞችን እና የውጭ ዜጎችን ማካተት

የህዝብ ውድድሮች ማሻሻያ (በኦገስት 6 ቀን 2021 ወደ ህግ ቁጥር 113 የተለወጠው አዋጅ ቁጥር 80/2021) በህዝብ አስተዳደር ውስጥ የቅጥር ተደራሽነትን እና ጥራትን ለማሻሻል አስፈላጊ ለውጦችን

 3,085 Visite totali,  11 visite odierne

Continua a leggere »
Asilo e immigrazione

አዲስ የስደት አዋጅ 2023፡ በመግቢያ ፍሰቶች ላይ ቀላልነት፣ ከ”መደበኛ ያልሆነ” የኢሚግሬሽን እና የልዩ ጥበቃ ገደቦች ተቃራኒ

አዲሱ የኢሚግሬሽን አዋጅ (የደንብ ህግ 20/2023) ስራ ላይ ውሏል። ከዚህ በታች ዋናዎቹ ለውጦች: “ያልተለመደ” ከኢሚግሬሽን ጋር በተያያዙ ወንጀሎች ላይ የቅጣት መጠን መጨመር፦ “ከሕገወጥ ስደት ጋር

 3,808 Visite totali,  11 visite odierne

Continua a leggere »

የሱዳን አምባሲ በካርቱም

ሱዳን የሱዳን አምባሲ በካርቱም አድራሻ የአውሮፓ ሃውስ ኮምፕሌክስ፣ 21ኛው መንገድ 39 ፡ ብሎክ 61 ፡ ካርቱም 2 ፖ.ሳ.ቁ. 739  ካርቱም ፡ ሱዳን https://goo.gl/maps/3NQ12KmnMmVKjfJ48    መገናኛ

 4,046 Visite totali,  11 visite odierne

Continua a leggere »