አዲስ የስደት አዋጅ 2023፡ በመግቢያ ፍሰቶች ላይ ቀላልነት፣ ከ”መደበኛ ያልሆነ” የኢሚግሬሽን እና የልዩ ጥበቃ ገደቦች ተቃራኒ

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on telegram

አዲሱ የኢሚግሬሽን አዋጅ (የደንብ ህግ 20/2023) ስራ ላይ ውሏል። ከዚህ በታች ዋናዎቹ ለውጦች:

“ያልተለመደ” ከኢሚግሬሽን ጋር በተያያዙ ወንጀሎች ላይ የቅጣት መጠን መጨመር፦

ከሕገወጥ ስደት ጋር በተያያዙ ወንጀሎች የተነሳ ሞት ወይም ጉዳትአዲስ ወንጀል፣ ይህም ለከባድ ቅጣቶች ይሰጣል፡

  • 10 እስከ 20 አመት ለአንድ ወይም ከዚያ በላይ ሰዎች ለከባድ ወይም በጣም ከባድ ጉዳቶች;
  • ለአንድ ሰው ሞት 15 እስከ 24 ዓመታት;
  • ለብዙ ሰዎች ሞት 20 እስከ 30 ዓመታት።

ማባረር፡

የጥፋተኝነት ውሳኔ ተከትሎ የታዘዙትን የመባረር ድንጋጌዎች ተግባራዊ ለማድረግ የዳኛው ውሳኔ ማረጋገጥ አስፈላጊ አይሆንም።

የፍሰት አዋጅ፡

  • የውጭ ሰራተኞችን ህጋዊ የመግቢያ ፍሰት እቅድ ለማውጣት አዳዲስ መንገዶች

ለበታች ሥራ ወደ ጣሊያን የሚገቡ የውጭ ዜጎች ኮታ ለአንድ ዓመት ብቻ ሳይሆን ለሦስት ዓመታት መሆኑ (2023-2025) ይገለጻል።

መደበኛ ያልሆነ የፍልሰት ትራፊክ አደጋ ላይ የሚዲያ ዘመቻዎችን የሚያስተዋውቁ ወንድ እና ሴት ሰራተኞች፡ በቅድምያ መብት ያገኛሉ።

  • ለውጭ አገር ዜጎች የበታች ሥራ የመግቢያና የመኖሪያ ፈቃድ ደንቦች ላይ ለውጦች

የውጭ ዜጎች ከጣሊያን ኩባንያዎች ጋር ያለው የሥራ ግንኙነት ጅምር ቀለል ያለ ይሆናል  እና የኑላ ኦስታው ሂደት የተፋጠነ ይሆናል፡ እንዲሁም ለወቅታዊ ስራዎች።

የስልጠና ፕሮግራሞች

በትውልድ አገራቸው ኮርስ ወስደው ያለፉ የውጭ ዜጎች፡ በጣሊያን እውቅና የተሰጣቸውና በሠራተኛ ሚኒስቴር የተደገፉ የሥልጠና ኮርሶች ያለፉ ወደ ጣሊያን እንዲገቡ ከፍሰቱ ድንጋጌ ኮታ ውጭ ሊጠይቁ ይችላሉ ።

የታደሰው የመኖሪያ ፍቃድ ያለው ጊዜ፡

ለቋሚ ሥራ ፣ ለግል ሥራ ወይም ለቤተሰብ መልሶ ማገናኘት የተሰጠው የመኖሪያ ፈቃድ እድሳት ከፍተኛው የሶስት ዓመት ጊዜ ሲሆን ቢያንስ ለሁለት ዓመት ይቆያል።

በልዩ ጥበቃ ላይ አዳዲስ ገደቦች

ለልዩ  ጥበቃ እውቅና ለማግኘት፣ የሚጠይቅ ሰው የግልና የቤተሰብ ህይወት ጥበቃን የሚያመለክት ማጣቀሻ ተሰርዟል።

ማስጠንቀቂያ፡ ለውጡ የሚመለከተው ከ 10/03/2023 ጀምሮ ለሚቀርቡ ማመልከቻዎች ብቻ ነው፣ ቀድሞ በ ኴስቱራ ቀጠሮ ካላቸው በስተቀር።

በፖሊስ ዋና መሥሪያ ቤት ቀጠሮ ለሌላቸው ነገር ግን ከ10/03/2023 በፊት ላመለከቱ፣ ማመልከቻው በፖሊስ ዋና መሥሪያ ቤት የቀረበበትን ኢ-መይል ያትሙ (እንዲያዙ) እናሳስባለን።

“በዘር፣ በፆታ፣ በቋንቋ፣ በዜግነት፣ በሃይማኖት፣ በፖለቲካዊ አመለካከቶች፣ በግላዊ ሁኔታዎች ወይም በማህበራዊ ጉዳዮች ምክንያት ስደትን ሊያስከትል ይችላል ተብሎ በሚገመገምበት ጊዜ” ልዩ ጥበቃ መስጠቱን ይቀጥላል  (ART 19, Comma 1 del TUI)

ቀደም ሲል 03/10/2023 በፊት የተሰጡ ልዩ ጥበቃ ፈቃዶች ለጥበቃ እውቅና የተሰጣቸው እናየግል እና የቤተሰብ ህይወትን ማክበርለሌላ አመት ሊታደስ ይችላል, እና ሁልጊዜ ወደ ሥራ ፈቃድ ሊለወጥ ይችላል። 

ከ 03/10/2023 በኋላ ለልዩ ጥበቃ ያሉ ጥያቄዎች 

የእኛ ምክር እንደ የጥገኝነት ጠያቂዎች: ለሰብአዊ መብት ጠባቂዎች እንደ አርቺ ለስደተኞች ከክፍያ ነፃ ቁጥር (800905570 ወይም +39 3511376335 ወይም ለ numeroverderifugiati@arci.it በመጻፍ) ወይም ታማኝ ጠበቃን በማነጋገር በማንኛውም ሁኔታ ማመልከቻ ማቅረብ ነው። ለልዩ ጥበቃ, ሰነዶችን ወይም ዝርዝር ዘገባን ከጥያቄው ጋር በማያያዝ እንዲሁም የግል ህይወት ገፅታዎችን (ማህበራዊ-ስራ ማካተትና / ወይም የቤተሰብ ህይወት) በስደተኞች ህግ በአንቀጽ 5 ኮማ  6 የቴስቶ ኡኒኮ ኣንቀጽ 8 ላይ: በሕገ መንግስት ኣንቀጽ 117 ግምት ውስጥ በማስገባት እሱም ሁልጊዜ መከበር ያለበት ሕግ ነው። 

Evidenza

የ2023 የህዝብ ውድድር ማሻሻያ፡ በምርጫው ውስጥ ስደተኞችን እና የውጭ ዜጎችን ማካተት

የህዝብ ውድድሮች ማሻሻያ (በኦገስት 6 ቀን 2021 ወደ ህግ ቁጥር 113 የተለወጠው አዋጅ ቁጥር 80/2021) በህዝብ አስተዳደር ውስጥ የቅጥር ተደራሽነትን እና ጥራትን ለማሻሻል አስፈላጊ ለውጦችን

 4,445 Visite totali,  2 visite odierne

Continua a leggere »

የሱዳን አምባሲ በካርቱም

ሱዳን የሱዳን አምባሲ በካርቱም አድራሻ የአውሮፓ ሃውስ ኮምፕሌክስ፣ 21ኛው መንገድ 39 ፡ ብሎክ 61 ፡ ካርቱም 2 ፖ.ሳ.ቁ. 739  ካርቱም ፡ ሱዳን https://goo.gl/maps/3NQ12KmnMmVKjfJ48    መገናኛ

 5,362 Visite totali,  2 visite odierne

Continua a leggere »