ከኤፕሪል 1 ጀምሮ ስለ ጭምብል እና አረንጓዴ ማለፊያ አዲስ ህጎች

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on telegram

decreto 17 marzo

ጭምብሉን እና አረንጓዴ ማለፊያን አጠቃቀም በተመለከተ አዲስ ህጎች (decreto del 17 marzo 2022): ከኤፕሪል 1 ቀን 2022 ጀምሮ በሥራ ላይ የሚውሉ ዋና ዋና ነገሮችና አዳዲስ ደንቦች እዚህ አሉ። 

በማርች 31 የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮቪድ-19 ያበቃል።  

 

ጭንብሎች

እስከ ኤፕሪል 30 – 2022 የኤፍኤፍፒ2 (FFP2) ጭንብል መጠቀም ግዴታ ነው:

 

  • በመጓጓዣዎች
  • ለሕዝብ ክፍት የሆኑ ትርኢቶች በሚካሄዱባቸው ቦታዎች 

 

በሥራ ቦታ፡ የመተንፈሻ መከላከያ መሳሪያዎችን መልበስ በቂ ይሆናል (ኤፍኤፍፒ2  ጭምብሎች መልበስ 

የግድ አይደሉም) ።

 

የአረንጓዴ ማለፊያ በሥራ ቦታ

ከኤፕሪል 1 ጀምሮ ሁሉም ሰራተኞች በመሰረታዊ አረንጓዴ ማለፊያ ወደ የስራ ቦታዎች መድረስ ይችላሉ።  ከ መይ 1 ጀምሮ ግን ከአሁን በኋላ አስገዳጅ አይሆንም።

 

እስከ ዲሴምበር 31 ቀን 2022 ክትባቱ በጤና ባለሙያዎች በሆስፒታሎች እና በአረጋውያን መንከባከቢያ ውስጥ ላሉ ሰራተኞች የግዴታ እንደሆነ ይቆያል: ይህንን ግዴታ ሳይወጡ የሚቀሩ ሰራተኞች ከስራ መታገዳቸውን ይቀጥላል። 

 

አረንጓዴ ማለፊያ እስከ ዲሴምበር 31 ድረስ ለአረጋውያን ጎብኚዎች (RSA) ፣ በሆስፒታልና በሆስፒታል ክፍሎች የግዴታ ሆኖ ይቆያል:  ነገር ግን ከኮቪድ ከተፈወሱና ግሪን ፓስ ከያዙ ታምፖነ ማድረግ ግዴታ አይሆንም።

 

ትምህርት ቤት

ለመዋዕለ ሕፃናት፣ አንደኛ ደረጃና መለስተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ እና ሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች: ቢያንስ 4 አዎንታዊ (ፖዚቲቭ) ጉዳዮች ባሉበት ጊዜ ክትትሉን በተገኙበት ይቀጥላሉ, እና ከስድስት ዓመት በላይ ለሆኑ ተማሪዎች፡ በመሃላቸው ፖዚቲቨ የሆነ ከተገኘ፡ ለ አስር ቀናት ፡ የ ፍፍጵ፪ ጭምብሎችን መጠቀም መጠቀም ኣለባቸውው። ሁሉም በኮቪድ ኢንፌክሽን ለተጠቁ ተማሪዎች ተለይተው ከሆነ፡ የርቀት ትምህርት እንቅስቃሴን (DAD) የሕክምና የምስክር ወረቀት ካላቸው መከታተል ይችላሉ። የፈጣን ወይም የሞለኪውላር አንቲጂን ምርመራ ኣሉታዊ ወይም ነጋቲቨ ውጤት ካላቸው ወደ ክፍል ለመመለስ በቂ ነው። 

 

ማግለልና ኳራንታይን 

ከኤፕሪል 1 ጀምሮ በኮቪድ ላይ አዎንታዊ ከሆነ ሰው ግንኙነት ያለው ማንኛውም ሰው እራሱን ማግለል የለበትም። ስለዚህ ማግለያው ተሰርዟል ነገር ግን ራስን መቆጣጠር እንዳለበት ተረጋግጧል:   ምልክቶች ካሉ ከተያዙ ከ 5 ቀናት በኋላ ታምፖነ ወይም ምርመራ ማድረግ አስፈላጊ ነው ፣ በጣም አስፈላጊ ለሆነ ጉዳይ ብቻ መውጣት ይችላሉ።

ለኮቪድ አዎንታዊ ለሆኑ ሰዎች መገለል ኣለባቸው፡ አሉታዊ ውጤት እስኪመጣ ድረስ እቤት ውስጥ መቆየት አለባቸው።

 

ሌሎች ዜናዎች

በተጨማሪ የማርች 17 አዋጅም ያስታውቃል:

 

  • የቀለም ዞኖች ስርዓት መጨረሻ
  • ከኤፕሪል 1 ጀምሮ ከቤት ውጭና የቤት ውስጥ የስፖርት መገልገያዎች አቅም ወደ 100% ይመለሱ።

 3,950 Visite totali,  2 visite odierne

የጣሊያን ኤምባሲ በአዲስ አበባ

ኢትዮጵያ የጣሊያን ኤምባሲ በአዲስ አበባ በኢትዮጵያ፣ በየመን፣ በጅቡቲ፣ በደቡብ ሱዳን ለሚኖሩ ዜጎች ብቃት ያለው ኤምባሲ   አድራሻ ቪላ ኢታልያ ቀበና ፖ. ሳ. ቁ. 1105 አዲስ

 155 Visite totali,  12 visite odierne

Continua a leggere »
aiuti sociali

አሶላቮሮ፡ ለስደተኞች የሥራና የድጋፍ አገልግሎቶች

አሶላቮሮ፡  የስራ የቅጥር ኤጀንሲዎች ብሔራዊ ማህበር፣ ከ UNHCR ጋር በመተባበር ያስተዋውቃል፣ “አኮልየንሳኤላቮሮ ፕሮጀችት” ፦ ለዓለም አቀፍ ጥበቃ፣ ጊዜያዊ ጥበቃና ልዩ ጥበቃ ፈቃድ ተጠቃሚዎች የሥራ ስምሪት

 3,229 Visite totali,  12 visite odierne

Continua a leggere »
decreto flussi
Evidenza

የፍሰት አዋጅ (ዴክሬቶ ፍሉሲ)፡ የማመልከቻው እስከ ሴፕቴምበር 30 መራዘም

የመኖሪያ ፈቃዶችን ለመለወጥና የአውሮፓ ህብረት ላልሆኑ ዜጎች ወደ ውጭ አገር በማሰልጠን ፕሮጀክቶች ውስጥ ለመግባት ማመልከቻ የማቅረቢያ ቀነ፡ ገደብ እስከ መስከረም 30 ቀን 2022 ተራዝሟል። የፍሰት

 3,908 Visite totali,  13 visite odierne

Continua a leggere »