ከጃንዋሪ 10 በኋላ የክትባት ግዴታና አረንጓዴ ማለፊያ-አዲሱ ህጎች

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on telegram

obbligo vaccino over 50

በጃንዋሪ 10 – 2022፣ በክትባትና በአረንጓዴ ማለፊያ ላይ ያሉትን ህጎች የሚያድስ አዲስ አዋጅ ተግባራዊ ሆነ። ማን የግዴታ ክትባት መውሰድ አለበት? ሱፐር አረንጓዴ ማለፊያን ማሳየት አስፈላጊ የሚሆነው መቼ ነው እና አሁንም የአረንጓዴ ማለፊያን መያዝ በቂ የሚሆነው መቼ ነው? እስከ ማርች 31 ቀን 2022 ወይም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እስኪያበቃ ድረስ በሥራ ላይ የሚቆዩት በአዲሱ አዋጅ የተጠቀሱት አንዳንድ በጣም አስፈላጊ ህጎች እዚህ አሉ።

በመጀመሪያ ደረጃ: ከጃንዋሪ 10 ጀምሮ የሶስተኛውን መጠን ለመቀበል ጊዜው ይቀንሳል፦ ከ ሁለተኛው ክትባት በኋላ ከ 5 ወራት ይልቅ ከ 4 ወራት  በኋላ ሊከናወን ይችላል። በተጨማሪም በፌብሩዋሪ 1 ላይ አረንጓዴ ማለፊያ 9 ወደ 6 ወራት ይቀንሳል

ከዚያ ለአንዳንድ ልዩ ምድቦች ደንቦች አሉ-የትኞቹን እንይ ።

50 በላይ 

አዲሱ ድንጋጌ ከታች ለተጥቀሱት እንዲከተቡ ያስገድዳል

 • ሁሉም የጣልያንና የውጭ ዜጎች፣ ቢያንስ 50 አመት የሆናቸው (ወይ እስከ ጃንዋሪ 15 የሚሞላቸው፣ በጣሊያን የሚኖሩ ወይም በአገራችን መኖርያ ፈቃድ ያላቸው፣ በብሔራዊ የጤና አገልግሎት ውስጥ የተመዘገቡም ያልተመዘገቡም 

የሕክምና የምስክር ወረቀት ማሳየት የሚችሉት ከክትባት ግዴታ ነፃ ናቸው። የአካባቢ የጤና ባለስልጣን (ASL) በሀኪሙ አስተያየት መሰረት ከፀረ SARS-CoV-2 ክትባት እንደማይወስድ የምስክር ወረቀት ይሰጣል በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በጉዳዩ ላይ የሰጠውን ሰርኩላር በማክበር።

ከፌብሩዋሪ 15 ቀን 2022 ጀምሮ ከሃምሳ በላይ የሆናቸው ሠራተኞች ወደ ሥራ ቦታው በሚገቡበት ጊዜ የተጠናከረ አረንጓዴ ማለፊያ የሌላቸው፣ የሰሩበት የመከፈል መብት ሳይኖራቸው ያለ ምክንያት ከስራ እንደቀሩ ይቆጠራሉ፡ ነገር ግን የዲሲፕሊን መዘዞች ሳይኖር እና የስራ መብታቸው እንደተጠበቀ ሆኖ።

ከፌብሩዋሪ 15 እስከ ጁን 15 ድረስ የሱፐር አረንጓዴ ማለፊያ በስራ ቦታም ግዴታ ይሆናል። የእጅ ባለሞያዎችና ፕሮፌሽናል ሰራተኞች ስራቸውን ለመስራት በሚሄዱበት ቤትም ይሁን በሌሎች መስርያ ቤቶች ወይም ጽ/ቤቶች  ሲሄዱ የሱፐር ግሪን ፓስ እንዲኖራቸው ይጠበቅባቸዋል።

  መሰረታዊ አረንጓዴ ማለፊያ 

      ከጃንዋሪ 20 ጀምሮ ለሚከተሉትን የግድ ይሆናል፦

 • ወደ ፀጉር አስተካካዮችን፣ የሴቶች ፀጉር ሰሪዎችና የውበት ባለሙያዎችን ለመሄድ 

ከፌብሩዋሪ 1 ጀምሮ የመሰረታዊ አረንጓዴ ማለፊያ ማሳየት ከታች ለተዘረዘሩት ኣስፈላጊ ይሆናል፦

 • ወደ ባንኮች ለመግባት
 • ወደ ፖስታ ቤት ለመሄድ
 • የምግብ ሸቀጦችና ፋርማሲዎችን ሳይጨምር ወደ ንግድ ተቋማትን ለመግባት 

ሱፐር አረንጓዴ ማለፊያ  

ከጃንዋሪ 10 ጀምሮ የግዴታ ይሆናል፦

 • በማንኛውም የህዝብ ማመላለሻ ውስጥ ለመግባት
 • ህዝብ ወደ ሚሰበሰብበት እንደ፡ ቡና ቤቶችና ሬስቶራንቶች፣ ሙዚየሞች፣ ሆቴሎችና ለመሄድ 
 • ወደ መዋኛዎችና  ጂሞች ለመሳተፍ  

ክትባቱን ያልወሰዱ 

ያልተከተቡ ሰዎች ከፌብሩዋሪ 15 ጀምሮ የሚሰራ የተጠናከረ አረንጓዴ ማለፊያ ለማግኘት የመጀመሪያውን መጠን እስከ ጃንዋሪ 31 ድረስ መውሰድ አለባቸው።

ክትባቱን ያልወሰዱ ከፌብሩዋሪ 1 ጀምሮ ከታች ወደ ተጠቀሱት መግባት ኣይችሉም፦

 • በማንኛውም የህዝብ ማመላለሻ
 • ወደ ቡና ቤቶችና ሬስቶራንቶች
 • ወደ ሆቴሎችና ሙዚየሞች  
 • ወደ መዋኛዎችና  ጂሞች 

ያልተከተቡ ሰዎች እንደ ፋርማሲዎች፣ ሱፐርማርኬቶች፣ የትምባሆና የፌራመንታ መደብሮች ያሉ መሰረታዊ ፍላጎቶችን ወይም አስፈላጊ ምርቶችን ወደሚሸጡ መደብሮች ብቻ መግባት ይችላሉ።

ደንቦቹን ለማያከብሩ ያሉ ቅጣቶች  

የክትባት ግዴታ እስከሚቀጥለው ጁን 15 ድረስ ፀንቶ ይቆያል። ከፌብሩዋሪ 1 ቀን 2022 ጀምሮ ክትባት ላልወሰዱት የአንድ ጊዜ የ100 ዩሮ ቅጣቶች ይተገበራሉ። ቁጥጥሩን የሚከናወነው በገቢዎች ኤጀንሲ ነው፡ በጤና ካርዱ እና በመታወቅያ መካከል ቁጥጥር ያደርጋሉ። የክትባት ግዴታውን በመጣስ ወደ ሥራ ቦታ ለሚገቡ ሠራተኞችም ቅጣቶቹ ይቀጥላሉ። የድንጋጌዎቹ መጣስ ከ600 እስከ 1500 ዩሮ ክፍያ ይቀጣል።  የንግድ ሥራ ባለቤቶች ቁጥጥሩን ካላከበሩ ቅጣቱ ከ 400 እስከ 1,000 ዩሮ ይደርሳል። 

 2,013 Visite totali,  1 visite odierne

Evidenza

የ2023 የህዝብ ውድድር ማሻሻያ፡ በምርጫው ውስጥ ስደተኞችን እና የውጭ ዜጎችን ማካተት

የህዝብ ውድድሮች ማሻሻያ (በኦገስት 6 ቀን 2021 ወደ ህግ ቁጥር 113 የተለወጠው አዋጅ ቁጥር 80/2021) በህዝብ አስተዳደር ውስጥ የቅጥር ተደራሽነትን እና ጥራትን ለማሻሻል አስፈላጊ ለውጦችን

 4,444 Visite totali,  1 visite odierne

Continua a leggere »
Asilo e immigrazione

አዲስ የስደት አዋጅ 2023፡ በመግቢያ ፍሰቶች ላይ ቀላልነት፣ ከ”መደበኛ ያልሆነ” የኢሚግሬሽን እና የልዩ ጥበቃ ገደቦች ተቃራኒ

አዲሱ የኢሚግሬሽን አዋጅ (የደንብ ህግ 20/2023) ስራ ላይ ውሏል። ከዚህ በታች ዋናዎቹ ለውጦች: “ያልተለመደ” ከኢሚግሬሽን ጋር በተያያዙ ወንጀሎች ላይ የቅጣት መጠን መጨመር፦ “ከሕገወጥ ስደት ጋር

 5,123 Visite totali,  1 visite odierne

Continua a leggere »

የሱዳን አምባሲ በካርቱም

ሱዳን የሱዳን አምባሲ በካርቱም አድራሻ የአውሮፓ ሃውስ ኮምፕሌክስ፣ 21ኛው መንገድ 39 ፡ ብሎክ 61 ፡ ካርቱም 2 ፖ.ሳ.ቁ. 739  ካርቱም ፡ ሱዳን https://goo.gl/maps/3NQ12KmnMmVKjfJ48    መገናኛ

 5,361 Visite totali,  1 visite odierne

Continua a leggere »