
ሱዳን
የሱዳን አምባሲ በካርቱም
አድራሻ
የአውሮፓ ሃውስ ኮምፕሌክስ፣ 21ኛው መንገድ 39 ፡ ብሎክ 61 ፡ ካርቱም 2
ፖ.ሳ.ቁ. 739 ካርቱም ፡ ሱዳን
https://goo.gl/maps/3NQ12KmnMmVKjfJ48
መገናኛ
ስልክ +249 1 83471615/6/7 | +00249183471615
ኢመይል: ambasciata.khartoum@esteri.it|
የሚከፈትበት ሰዓታት
የቪዛ ቢሮ፡ ማክሰኞ ከ9፡00 እስከ 10፡45።
ኤምባሲ፡ ከእሑድ እስከ ሐሙስ ከ 9፡00 እስከ 16፡00
ለቤተሰብ ዳግም ውህደት መረጃ
ከኢሚግሬሽን ጽህፈት ቤት ለ “ቤተሰብ ዳግም ውህደት ” የቅድሚያ ፈቃድ
- ማክሰኞ ከቀኑ 9፡00 እስከ 12፡00 ወደ ቢሮ በመሄድ በቆንስላ ፅህፈት ቤት ሰነዶችን ህጋዊ ማድረግ። እዚህ ከቪዛ ጽ/ቤት ጋር ቀጠሮ ለመያዝ ይቻላል ወይም ህጋዊነት ከተረጋገጠ በኋላ በቀጥታ ይገናኙዎታል።
- ደረሰኙን ከቀጠሮው ቀን እና ሰዓት ጋር በማተም በቃለ መጠይቁ ቀን በኤምባሲው መግቢያ ላይ ያቅርቡ። የተወሰነ ቀጠሮ መሰረዝ አይቻልም; በቀጠሮ ያልተገኙ በአጭር ጊዜ ውስጥ አዲስ የመጠየቅ እድል አይኖራቸውም።
- በሁሉም መስክ ተሞልቶ መፈረም ያለበትና ፓስፖርቱ ላይ ከተመለከቱት ጋር የሚገጣጠሙ ሙሉ የግል ዝርዝሮችን የያዘ የቪዛ ማመልከቻ ያቅርቡ። 5ቱ ገፆች መታተም አለባቸው (በ2ዲ ባርኮድ) እና ከዚህ ኤምባሲ ቪዛ ቢሮ ጋር በቃለ መጠይቁ ቀን መቅረብ አለባቸው።
የአሰራር ሂደቱ ከተጠናቀቀ በኋላ አመልካቹ ፓስፖርቱን ለመውሰድ የማይችል ከሆነ, ለሦስተኛ አካል እንዲሰበስብለት የሚፈቅድ አግባብነት ያለው ህጋዊ ውክልና (በሶስተኛ ወገን ፓስፖርት ለመሰብሰብ የሚፈቅድ ሥልጣን) መሙላት አስፈላጊ ይሆናል።
- የቪዛ ማመልከቻ ቅጽ።
- የቤተሰቡ አባል(ወይም ኣባሎች) ፓስፖርትና መታወቂያ ሰነድ። በዲፕሎማሲው ባለሥልጣኖች መስጠት በማይቻልበት ጊዜ የጣሊያን ኤምባሲ ከአገሪቱ ለቀው እንዲወጡ ላሻፓሳረ የሚል ፈቃድ ሊሰጥዎት ይችላል፤ በሌላ መንገድ፣ በስደተኛ ካምፖች ውስጥ ለሚኖሩ፣ የኮንቬንሽን የጉዞ ሰነድ ለማውጣት ለ ዩኤንኤችሲአር ማመልከት ይቻላል።
- ኑላ ኦስታው ከ6 ወራት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ብቁ በሆነው የስፖርቴሎ ኡኒኮ ጽ/ቤት (የኢሚግረሽን ጽ/ቤት) ይሰጣል።
- የልደት፣ ጋብቻ፣ የሲቪል ሁኔታ የምስክር ወረቀቶች።
- የዝምድና ትስስርን የሚያረጋግጡ ሌሎች ሰነዶች ከሌሉ የቤተሰብ አባላት የዲኤንኤ ምርመራ እንዲያደርጉ ይጠበቅባቸዋል።
አስፈላጊ ሰነዶች



በነፃ ስልክ ቁጥር 800905570 ወይም (+39)3511376335 ወይም በኢሜል numeroverderifugiati@arci.it ያግኙን