የትኞቹ በውጭ አገር የሚደረጉ የፀረ ኮቪድ ክትባቶች ናቸው በጣሊያን ውስጥ አረንጓዴ ማለፊያ ለማግኘት ተቀባይነት ያላቸው፦
- ኮቪሺልድ (የህንድ የሴረም ተቋም),
- አር – ኮቪ (አር ፋርም) R-CoVI (R-Pharm)
- ኮቪድ-19 ክትባት–ዳግመኛ (ፊዮክሩዝ) Covid-19 vaccine recombinant (Fiocruz),
ትክክለኛውን እውቅና ሊጠቀሙ የሚችሉ፦
- የጣልያን ዜጎች (በውጭ የሚኖሩ ነዋሪዎችን ጨምሮ) እና አብረው የሚኖሩ የቤተሰብ አባሎቻቸው
- ለሥራ ወይም ለትምህርት ምክንያት በጣሊያን የሚገኙ የውጭ ዜጎች በብሔራዊ የጤና አገልግሎት ወይም በ “SASN” (ለሰራተኞቹ የጤና እርዳታ) የተመዘገቡ ቢሆኑም ባይሆኑም
- በብሔራዊ የጤና አገልግሎት የተመዘገቡ እና በውጭ አገር ከ SARS-CoV-2 የተከተቡ
የተሰጠው የክትባት የምስክር ወረቀቶች ትክክለኛነት በጣሊያን ግዛት ከተሰጠው አረንጓዴ የኮቪድ-19 ሰርተፍኬት (EU – የአውሮጳ ሕብረት ዲጂታል ኮቪድ ሰርተፍኬት) ጋር ተመሳሳይ ይሆናል።