አስፈላጊ ዜና
የአውሮፓ ህብረት በዩክሬን ውስጥ ካለው ጦርነት ጋር በተያያዘ ለጊዜያዊ ጥበቃ የሚሰጠውን መመሪያ ለመቀበል ወስኗል (direttiva 55/2001).
የዩክሬን ዜጎች፣ ጥገኝነት ጠያቂዎች፣ የአለም አቀፍ ጥበቃና የረጅም ጊዜ የመኖሪያ ፍቃድ በዩክሬን የሚኖሩና የቤተሰባቸው አባላት ታዳሽ የመኖሪያ ፍቃድ የማግኘትና የሚከተሉትን አገልግሎቶች የማግኘት መብት አላቸው:
• ትምህርት ቤት
• ሥራ
• መጠለያ
• ማህበራዊ እንክብካቤ
• የጤና ጥበቃ
አስተውል
ጣሊያን የዚህን መመሪያ ማስፈጸሚያ ድንጋጌ እስካሁን አላወጣችም። ሂደቶቹ ሲገኙ እንገልጸዋለን።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ማስታወስ የምንፈልገው:
• ቪዛ እና ፍቃድ ሳያስፈልግ በጣሊያን ለ፺ ቀናት መቆየት ይቻላል። ለማየት እዚህ ተጫን (clicca qui per maggiori informazioni)
• በተገን ጠያቂዎች መቀበያ ማእከላት እንደ(SAI) እና በማዘጋጃ ቤቶች በሚተዳደረው የአቀባበልና ውህደት ስርዓት (ጽዓዒ) ማእከላት የእንግዳ መቀበያ ቦታ ለመጠየቅ ይቻላል ። (clicca qui per maggiori informazioni)
ወደ ዩክሬን የድንገተኛ አደጋ ክፍል ሂድ
Vai alla sezione Emergenza Ucraina