የህዝብ ውድድሮች ማሻሻያ (በኦገስት 6 ቀን 2021 ወደ ህግ ቁጥር 113 የተለወጠው አዋጅ ቁጥር 80/2021) በህዝብ አስተዳደር ውስጥ የቅጥር ተደራሽነትን እና ጥራትን ለማሻሻል አስፈላጊ ለውጦችን ያስተዋውቃል። በጣም አስፈላጊ ከሆኑ ዜናዎች መካከል፡–– ከጣሊያን ዜጎች በተጨማሪ ዓለም ኣቀፋዊ የጥገኝነት ዕውቅና ያለው መኖርያ ፍቃድ ያላቸው ሰዎችና የአውሮፓ ህብረት የመኖሪያ ወይም የረጅም ጊዜ የአውሮፓ ህብረት የመኖሪያ ፍቃድ ያላቸው ዜጎች ለህዝብ ውድ ድር ማመልከት ይችላሉ፤
– ለውድድር ሂደቱ መደምደሚያ፡ ከፍተኛው የ 6 ወራት ገደብ ተዘጋጅቷል፤ – ለሕዝብ ውድድሮች ለማመልከት የ “inPA” ምልመላ ፖርታልን ወይም ድረ ገጽ ብቻ መጠቀም አስፈላጊ ይሆናል – www.InPA.gov.it ። በድረ ገጹ ላይ መመዝገብ ነፃ ነው እና በ SPID ፣ CIE እና CNS መለያ ስርዓቶች ብቻ ሊከናወን ይችላል። “SPID: ምን እንደሆነ፣ ማን ሊጠይቀው እንደሚችል እና እንዴት” የሚለውን ገጹን ይመልከቱ – “SPID: a cosa serve, chi può richiederlo e come” ድረ ገጹ በህዝባዊ የስራ አቅርቦት እና ፍላጎት መካከል ያለውን ስብሰባ የሚያቃልል እና የሚያፋጥነውን የፈጠራ ዲጂታል ስርዓት በመጠቀም የህዝብ አስተዳደር ምልመላ ጥራትን ለማሻሻል ያለመ ነው። |
ለበለጠ መረጃ እዚህ ጠቅ ያድርጉ Clicca qui per maggiori info |
915 Visite totali, 7 visite odierne