ደህንነታችን በመጠበቅ ወደ ትምህርት ቤት እንመለሳለን

Share on facebook
Share on twitter
Share on linkedin
Share on telegram

የትምህርት ሻንጣውን ለማዘጋጀት ጊዜው አሁን ደርሷል ፡፡ በዚህ ዓመት ከመጻሕፍትና ከደብተሮች ጋር ወደ አንዳንድ አዳዲስ ልምዶችም መግባት አለብን ፡፡

የተቋሙ ዘመቻ ቁሳቁሶች ለት/ቤት ሰራተኞች ፣ ለቤተሰቦች ፣ ለሴት ተማሪዎችና ተማሪዎች ትምህርትን ዳግም ማስጀመርን ለማጀብ እና አዳዲስ ልምዶች እንዲከበሩ ያበረታታሉ ፡፡

(Fonte: Ministero della Salute)

የሰውነትህን የሙቀት መጠን ለካ
ከመውጣትህ በፊት በየቀኑ ይህንን አድርግ ፡፡ ከ 37.5° በላይ ወይም በኮቪድ – 19 የሚታወቁ ምልክቶች ካለህ በቤትህ በመቆየት ዶክተርህን አነጋግር።

እጅህን ብዙ ግዜ ታጠብ
በትምህርት ቤቱ ውስጥ የሚገኙትን የንጽህና መጠበቅያ ምርቶች ተጠቀም።

ምልክቶቹን ተከተል
መግቢያዎችና መውጫዎች የተለዩ ናቸው ፣ በት/ቤቱ የተዘጋጁትን መመሪያዎች ተከተል።

IMMUNI የሚለውን አፕሊኬሽን ወይም መተግበርያ አውርድ
ዕድሜህ ከ14 ዓመት በላይ ከሆነ አሁን አውርደው፡፡ መተግበሪያው ለኮቪድ – 19 ማንኛውንም ተጋላጭነት ለመለየት ያስችለሃል።.

ርቀትህን ጠብቅ
ማንኛውንም መሰብሰብ አስወግድ። ሁልጊዜ በራስህና በሌሎች መካከል ቢያንስ የአንድ ሜትር ርቀት ጠብቅ።

ጭምብሉን ልበስ
በምትንቀሳቀስበት ግዜ ወይም በጋራ ቦታዎች ውስጥ ሁል ጊዜ ያዘው። በምትቀመጠው የትምህርት ቤት ዴስክ ወይም ጠረጴዛ የአንድ ሜትር ርቀት የሚጠበቅ ከሆነ ማውለቅ ትችላለህ። ከ6 ዓመት በታች ለሆኑ ኣይመለከትም።

በመግቢያዎቹ መረጃ አግኝ
ለአንድ ተማሪ አንድ ረዳት ብቻ ነው የታቀደው። የት/ቤትህ ድረ ገጽ በመግባት ስለ ደንቦቹ ማወቅ ትችላለህ።

እራሳችንን በመጠበቅ እኛም ሌሎችን እንጠብቅ

Evidenza

የ2023 የህዝብ ውድድር ማሻሻያ፡ በምርጫው ውስጥ ስደተኞችን እና የውጭ ዜጎችን ማካተት

የህዝብ ውድድሮች ማሻሻያ (በኦገስት 6 ቀን 2021 ወደ ህግ ቁጥር 113 የተለወጠው አዋጅ ቁጥር 80/2021) በህዝብ አስተዳደር ውስጥ የቅጥር ተደራሽነትን እና ጥራትን ለማሻሻል አስፈላጊ ለውጦችን

 3,164 Visite totali,  5 visite odierne

Continua a leggere »
Asilo e immigrazione

አዲስ የስደት አዋጅ 2023፡ በመግቢያ ፍሰቶች ላይ ቀላልነት፣ ከ”መደበኛ ያልሆነ” የኢሚግሬሽን እና የልዩ ጥበቃ ገደቦች ተቃራኒ

አዲሱ የኢሚግሬሽን አዋጅ (የደንብ ህግ 20/2023) ስራ ላይ ውሏል። ከዚህ በታች ዋናዎቹ ለውጦች: “ያልተለመደ” ከኢሚግሬሽን ጋር በተያያዙ ወንጀሎች ላይ የቅጣት መጠን መጨመር፦ “ከሕገወጥ ስደት ጋር

 3,884 Visite totali,  5 visite odierne

Continua a leggere »

የሱዳን አምባሲ በካርቱም

ሱዳን የሱዳን አምባሲ በካርቱም አድራሻ የአውሮፓ ሃውስ ኮምፕሌክስ፣ 21ኛው መንገድ 39 ፡ ብሎክ 61 ፡ ካርቱም 2 ፖ.ሳ.ቁ. 739  ካርቱም ፡ ሱዳን https://goo.gl/maps/3NQ12KmnMmVKjfJ48    መገናኛ

 4,122 Visite totali,  5 visite odierne

Continua a leggere »