ከኦክቶቨር 26 እስከ ኖቨምበር 24 ድረስ የሚከተሉት እርምጃዎች በመላው ጣሊያን ውስጥ ተግባራዊ ይሆናሉ:
እንቅስቃሴዎች
ሁሉም ሰዎች በሕዝብ ወይም በግል የትራንስፖርት መንገዶች እንዳይጓዙ በጥብቅ ይመከራል። ከታች ከተቀሱት በስተቀር፦
✓ ለሥራ ፣ ለጥናት ፣ ለጤንነት ምክንያቶች ፣ ኣስፈላጊ ሁኔታዎች ወይም የማይታገዱ ስራዎች ለማከናወን።
ስፖርት
✓ ቢያንስ ሁለት ሜትር የደህንነት ርቀትን ከግምት ውስጥ በማስገባት ስፖርቶችን ወይም የግለሰብ እንቅስቃሴዎችን ከቤት ውጭ ለማከናወን ይፈቀዳል፡
✘ አስፈላጊ በሆኑ የእንቅስቃሴ እርዳታ ማእከላት ውስጥ ከሚያገለግሉ በስተቀር ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ፣ የመዋኛ ገንዳዎች ፣ የመዋኛ ማዕከላት ፣ የውበት መንከባከብያ መስጫ ማእከላት ፣ የተፈጥሮ ሙቅ ውሃ ተርማሎች ኣገልግሎት እንዳይሰጡ ታግደዋል፡
✘ ሁሉም ንክኪ ያልቸው ስፖርቶችና ውድድሮች ኣይፈቀዱም፦ ሁሉም ንክኪ ያላቸው እንቅስቃሴዎችና በፍላጎት የተመሰረቱ ጫዋታዎች ጭምር፡
✓ በሕዝብና በግል የስፖርት ማእከሎችና ክለቦች፡ በክፍት ቦታ የሚካሄዱ መሰረታዊ የስፖርት እንቅስቃሴዎችና አካላዊ እንቅስቃሴዎች ማህበራዊ ርቀትን በማክበርና ባለ መቀራረብ ለማከናወን ይፈቀዳሉ፡
✓ በጣሊያን ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴ (CONI) በብሔራዊ ወይም በክልላዊ ፍላጎት ዕውቅና የተሰጡ የግልና የቡድን ስፖርቶችን የሚመለከቱ ዝግጅቶችና ውድድሮች ለማከናወን ብቻ ናቸው የሚፈቀዱት።
ሰልፎች
✓ የህዝብ ሰልፎችን ማከናወን የሚፈቀደው ማህበራዊ ርቀትን በማክበር በስታቲስቲክስ መልክ ብቻ ነው።
ሲነማና ተያትሮች
✘ በትያትር አዳራሾች ፣ በኮንሰርት አዳራሾች ፣ በአዳራሾች ውስጥ ለሕዝብ ክፍት የሆኑ ትዕይንቶች፣
ሲኒማ ቤቶችና ሌሎች በክፍት ቦታ የሚትዩ ጨምሮ ተቋርጠዋል።
የመዝናኛ ኣዳራሾችና ጭፈራ ቤቶች
✘ የጨዋታ ኣዳራሾች ፣ የካርታ መጫወቻ ክፍሎች ፣ የቢንጎ አዳራሾችና የካዚኖ ጨዋታዎች ታግደዋል።
✘ በዝግም ሆነ በክፍት ቦታዎች የሚካሄዱ ጭፈራዎች ታግደዋል።
ድግሶችና በዓላት
✘ ሲቪልና ሃይማኖታዊ ሥነ፡ሥርዓቶችን ጨምሮ፡ በቤት ውስጥና በክፍት ቦታዎች የሚዘጋጁ በኣሎችና ድግሶች ታግደዋል።
✘ ለስራ ምክንያት፣ ለኣስፈላጊ ወይም ለኣስቸኳይ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር፡ ካንተ ጋር የማይኖሩ ሰዎች በቤት ላለመቀበል ይመከራል።
✘ ማንኛውም ኣይነት ድግሶችና ባዛሮች እንደታገዱ ይቆያሉ።
ሙዝየሞች ፣ ኮንፈረንሶች እና ኮንግረሶች
✓ ማህበራዊ መራራቅን በማክበር፡ ሙዝየሞችና የባህል ቦታዎች ክፍት ሆነው ይቆያሉ:
✓ ማህበራዊ ርቀትን በማክበር የአምልኮ ቦታዎችን መግባት ይፈቀዳል:
✘ ስብሰባዎች እና ኮንግረሶች ታግደዋል፡፡
ትምህርት
✓ የሕፃናት መዋያ፣ የመጀመሪያ ደረጃና መካከለኛ ትምህርት ቤቶች፡ ትምህርታቸው ወደ ትምህርት ቤት በመሄድ ይቀጥላሉ:
✓ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ቢያንስ 75% ትምህርቶችን በመስመር ላይ እንጂ በአካል መውሰድ የለባቸውም ፡፡ ክልሎችም ሙሉ በሙሉ በመስመር ላይ ለማከናወን ሊጠይቁ ይችላሉ:
✓ የመግቢያ እና መውጫ ሰዓቶች እንዲሁ ከሰዓት በኋላ በፈረቃ መቀየር አለባቸው፡ ከ 9 ሰዓት በፊት ወደ ክፍሉ ለመግባት አይቻልም፡
✘ የትምህርት ቤት ጉዞዎች እንደታገዱ ይቆያሉ።
ክለቦች ፣ ቡና ቤቶች ፣ ምግብ ቤቶች እና ሱቆች
✓ ቡና ቤቶች ፣ መጠጥ ቤቶች ፣ ምግብ ቤቶች ፣ አይስክሬም ቤቶች ፣ የኬክ ቤቶችና የምግብ አቅርቦት አገልግሎት የሚሰጡ ከ 5:00 እስከ 18:00 ድረስ ክፍት ሆነው መቆየት ይችላሉ፡
✓ አብረው የሚኖሩ ካልሆኑ በስተቀር በጠረጴዛው ውስጥ ቢበዛ ለ 4 ሰዎች በጠረጴዛው ውስጥ ፍጆታ ይፈቀዳል፡
✘ ከ 18:00 ሰዓት በኋላ በሕዝብ ቦታዎች ምግብንና መጠጦችን መብላትና ለሕዝብ ክፍት ማድረግ የተከለከለ ነው፡
✓ የታዘዘ ምግብ: ወደ ታዘዘበት ማድረስ ሁል ጊዜ ይፈቀዳል፡ እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ፡ (የአከባቢ መቆለፊያ በሌለበት)፡ የታዘዘ ምግብ ማድረስ፡ በቦታው መጠቀም ግን የተከለከለ ነው፡
✓ ሱቆች ቢያንስ አንድ ሜትር የግለሰቦችን ርቀትን እስካረጋገጡ ድረስና የመግቢያዎች ብዛት እስከተገደቡ ድረስ ክፍት ሆነው መቆየት ይችላሉ፡;
✓ ለሕዝብ ክፍት በሆኑና በትላልቅ የንግድ ተቋማት ውስጥ: በሚገኙበት ቦታ ላይ በተመሳሳይ ጊዜ ወደ ስፍራው የገቡትን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች የሚገልጽ ምልክት በመግቢያ ላይ ማሳየት ግዴታ ነው።


