ወደ ሥራ ሊለወጡ በሚችሉ የመኖሪያ ፈቃዶች ላይ ያሉ አዳዲስ ዜናዎች

Share on facebook
Share on twitter
Share on whatsapp
Share on telegram

በዲክሰምበር 20/2020 የስደተኞችን ጉዳይ በሚመለከት፡ በሕግ ቁ. 173 ኣዳዲስ ኣስፈላጊ ነገሮች ኣጽድቀዋል።

ኣዳዲስ ዜናዎች

ወደ ስራ ምክንያት ሊቀየሩ የሚችሉ የመኖርያ ፈቃዶች ዝርዝር

በአንቀጽ 6 ኮማ 1 ቢስ የወጣ የስደተኞች ሕግ (ቴስቶ ኡኒኮ)፡ መኖርያ ፈቃዶች መስፈርቶችን ካሟሉ፡ ወደ ስራ ምክንያት ሊቀየሩ የሚችሉ የመኖርያ ፈቃዶች ይጨምራሉ።

ለትምህርት ምክንያት ከሚሰጡ የመኖርያ ፈቃዶች በተጭማሪ፡ መኖርያ ፈቃዶቹ ወደ ስራ ምክንያት ልቀየሩ ይችላሉ:

  • ለፕሮቴስዮነ ስፔቻለ የሚሰጥ የመኖርያ ፈቃድ፡ (ኣመልካቹ በአንቀጽ ቁ. 10 ኮማ 2 ድንጋጌ መሰረት፡ በከባድ ወንጀል ተበክሎ የአለም አቀፍ ጥበቃን ካልተከለከለ ወይም በአንቀጽ 12 ድንጋጌ ቁ. 251/2007 በተመለከተና በአንቀጽ 16 ድንጋጌ ቁ. 251/2007 መሰረት ለብሔራዊ ደህንነት አደጋ ካልሆነ በስተቀር)
  • ለተፈጥሮ አደጋ ምክንያት የሚሰጥ የመኖርያ ፈቃድ 
  • በመኖርያ ምርጫ የሚሰጥ የመኖርያ ፈቃድ
  • ለዜግነት ወይም ለሃገር ኣልባ ለሆኑ የሚሰጥ የመኖርያ ፈቃድ
  • ለስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች የሚሰጥ የመኖሪያ ፈቃድ
  • ለሥነ፡ጥበባዊ እንቅስቃሴ የሚሰጥ የመኖሪያ ፈቃድ
  • ለሃይማኖታዊ ምክንያቶች  የሚሰጥ የመኖሪያ ፈቃዱ
  • ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆች ለመንከባከብ የሚሰጥ የመኖሪያ ፈቃድ
  • ለሕክምና የሚሰጥ የመኖሪያ ፈቃድ