አረንጓዴ የለይፍ ምልክት

Share on facebook
Share on twitter
Share on whatsapp
Share on telegram

አረንጓዴ የይለፍ ሰነድ ወይም ወረቀት ፡ በአውሮጳ (“የአውሮጳ ሕብረት ዲጂታል የኮቪድ ሰርተፊኬት”) በጣሊያንና በአውሮፓ በተረጋገጠ መንገድ ለመጓዝ የሚያገለግል ሰነድ ነው ፡፡ የምስክር ወረቀቱ ከጁላይ 1 ቀን 2021 ጀምሮ በሁሉም የአውሮፓ ህብረት ግዛቶች ውስጥ ይሠራል ፡፡ 

ከኦገስት 6 ቀን ጀምሮ በነጭው አካባቢም ቢሆን ለነዚህ ግዴታ ይሆናል

 • በዝግ ምግብ ቤቶችና ቡና ቤቶች ውስጥ በጠረጴዛው ላይ ለሚመገቡ
 • ወደ ሙዝየሞችና ኤግዚቢሽኖች ለመግባት 
 • ለሕዝብ ክፍት የሆኑ ዝግጅቶችን፣ኮንሰርቶችን፣ ዝግጅቶችንና የስፖርት ውድድሮችን ለሚሳተፉ
 • በባህላዊ፣ ማህበራዊ መዝናኛ ማዕከሎች በቤት ውስጥ (በዝግ) እንቅስቃሴዎች ለሚሳተፉ  (ለልጆች የትምህርት ማእከሎችና የበጋ ማዕከላት በስተቀር)
 • በቁንጅና ሳሎኖችና ስፖርት ማዕከሎች (መዋኛ ገንዳዎች ፣ ጂሞች ፣ የቡድን ስፖርት ሜዳዎች) በዝግና ወደ ተርማሎች ለመግባት
 • የሽማግሌዎች መኖርያ ክሊኒኮች ለመግባት
 • በቤተሰብ መዝናኛዎችና በመዝናኛ ፓርኮችን ለመግባት
 • በባዛሮች፣ በበዓላት በስብሰባዎችና በኮንግረስ ለሚሳተፉ
 • በበዓላትና በዝግጅቶች ለሚሳተፉ
 • በሕዝባዊ ውድድሮች ውስጥ ለሚሳተፉ
 • የጨዋታ ክፍሎችን የውርርድ ክፍሎችን ቢንጎ እና ካሲኖዎችን ለሚገቡ

አረንጓዴው ይለፍ ፡ ጣሊያን ውስጥ በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በዲጂታል ቻናሎችና በአካል በመሄድ  ይሰጣል ፡፡

መጠየቅና ማግኘት ይቻላል

–  ስፒድ ወይም ከጤና ካርድ ወይም ከመታወቅያ ጋር ወደ dgc.gov.it ጣቢያ በማገናኘት

Immuni ከሚለው አፕሊኬሽን

IO ከሚለው አፕሊኬሽን

የኤሌክትሮኒክ የጤና መዝገብዎን በመግባት

ከቤተሰብዎ ሐኪም ነፃ ምርጫ ካለው የሕፃናት ሐኪም ወይም ወደ ፋርማሲ በመሄድ


ማረጋገጫውን ሰርተፊኬት ማን ሊያገኝ ይችላል?

የምስክር ወረቀቱ በቀጥታ (በአውቶማቲክ) የሚቀርብና በሚከተሉት ሁኔታዎች ያለክፍያ እንዲሰጥ ተደርጓል፦

) የመጀመሪያውን መጠን ወይም የአንድ ጊዜ ክትባት 15 ውስጥ ለተከተበ

 • አገልግሎቱ ሁለተኛው መጠን እስከሚሰጥ ድረስ (ሁለት ክትባቶችን የሚያካትቱ ክትባቶችን በተመለከተ) ወይም 9 ወር (ለአንድ፡መጠን ክትባቶች)
 • የምስክር ወረቀቱ የመጀመሪያውን መጠን (ሁለት ለሚፈልጉ ክትባቶች) ወይም የአንድ ጊዜ ክትባት ከተሰጠ 15 ቀናት በኋላ በዲጂታል ወይም በወረቀት መልክ ይሰጣል።

) የክትባቱን ዑደት ላጠናቀቀ፦

 • አገልግሎቱ 9 ወራት
 • የምስክር ወረቀቱ በዲጂታዊ ወይም በወረቀት መልክ የአንድ ጊዜ ክትባት ከተሰጠ 15 ቀናት በኋላ ወይም ሁለተኛው መጠን ከተሰጠ 2 ቀናት በኋላ ይሰጣል፡፡

) ከኮቪድ 19 የዳነና  ማግለልን ላጠናቀቀ 

 • አገልግሎቱ ፡ ከዳነ ቦኋላ ለ 6 ወራት 
 • በዚህ ጉዳይ ላይ ለአረንጓዴው ፓስፖርት ፍላጎት ላለው አካል (በወረቀት ወይም በዲጂታል መልክ) ከተኛበት ሆስፒታል ወይም ሆስፒታል ላልገባ ህመምተኛ ከሃኪሙ ፡  ከዳነ ቦኋላ ከሚቀጥለው ቀን ጀምሮ ይሰጣል ፡፡

) ለኮቪድ – 19 ሞለኪውላዊ አንቲጂን ምርመራ ላደረገ ወይም አሉታዊ ውጤት ላገኘ

 • አገልግሎቱ ፡  ምርመራ ካደረገ 48 ሰዓታት
 • በዚህ ጉዳይ ላይ አረንጓዴው ይለፍ (ፓስፖርት) ኣመልካቹ ባቀረበው ጥያቄ መሰረት በጥቂት ሰዓታት ውስጥ (በወረቀት ወይም በዲጂታል) በመንግስትና በግል የጤና ተቋማት በፋርማሲዎች ወይም ከሐኪሙ ይሰጠዋል፡፡
Pidgin English
Pular
Soninke
Bambara

ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆች፥ በሌላ የአውሮፓ ሀገር ውስጥ ካሉ ቤተሰብ አባል ጋር እንዴት መቀላቀል ይችላሉ

ጣሊያን ውስጥ ብቻቸውን የደረሱና በሌላ የአውሮፓ ሀገር የቤተሰብ አባል ያላቸው ታዳጊዎች፡ ደህንነቱ በተጠበቀ አሰራርና በነጻ ቤተሰቦቻቸውን ለመቀላቀል ማመልከት ይችላሉ። በ CIDAS እና UNHCR የተዘጋጁ የመረጃ

 126 Visite totali,  4 visite odierne

vaccini Covid validi in Italia

የትኞቹ በውጭ አገር የሚደረጉ የፀረ ኮቪድ ክትባቶች ናቸው በጣሊያን ውስጥ አረንጓዴ ማለፊያ ለማግኘት ተቀባይነት ያላቸው

የትኞቹ በውጭ አገር የሚደረጉ የፀረ ኮቪድ ክትባቶች ናቸው በጣሊያን ውስጥ አረንጓዴ ማለፊያ ለማግኘት ተቀባይነት ያላቸው፦  ኮቪሺልድ (የህንድ የሴረም ተቋም),  አር – ኮቪ (አር ፋርም) R-CoVI (R-Pharm) 

 437 Visite totali,  3 visite odierne

በብሔራዊ የጤና ስርዓት ካልተመዘገቡ ወይም የጤና ካርድ ከሌለዎት ለአረንጓዴ ማለፊያ እንዴት ማመልከት እንደሚቻል

ክትባት የወሰዱ ፣ ነገር ግን በብሔራዊ የጤና ስርዓት ያልተመዘገቡ ፣ የኤሌክትሮኒክ መታወቂያ ካርድ ፣ የጤና ካርድ ፣ SPID ወይም IO የመተግበሪያ አፕሊኬሽን የሌላቸው ፣ ይህንን

 1,076 Visite totali,  4 visite odierne