
አሶላቮሮ፡ የስራ የቅጥር ኤጀንሲዎች ብሔራዊ ማህበር፣ ከ UNHCR ጋር በመተባበር ያስተዋውቃል፣ “አኮልየንሳኤላቮሮ ፕሮጀችት” ፦ ለዓለም አቀፍ ጥበቃ፣ ጊዜያዊ ጥበቃና ልዩ ጥበቃ ፈቃድ ተጠቃሚዎች የሥራ ስምሪት አገልግሎትና ተጨባጭ ድጋፍ ይሰጣል።
የሚሰጠው አገልግሎቶች
ጣሊያን ለሚደርሱት በቅጥር ኤጀንሲዎች ዋስትና ያለው ፡ ከክፍያ ነፃ ፡ ለማህበራዊ ማካተትና ስራ የማግኘት አገልግሎት ከሚሰጡ አገልግሎቶች መካከል፦
- መምርያና የመጀመሪያ ስልጠና – የጣሊያን የስራ ገበያና የኤጀንሲ ስራ ግንዛቤን ለማሳደግ ያለመ የመጀመሪያ የመረጃ ስብሰባ ከክፍያ ነፃ። በስብሰባው ወቅት በኤጀንሲዎቹ በኩል ወደ አገራችን ለሚመጡት አገልግሎቶችና የአገልግሎቶች ካርታን ያቀርባሉ
- የብቃት ሚዛን – የክህሎት ወይም የብቃት ሚዛን ለሰልጣኙ በጣም ተስማሚ ወደሆነው የስልጠና መንገድ ለመምራት ችሎታዎችን ለመቅረጽና ግላዊ ባህሪያቱን ለመተንተን የሚያስችል መሰረታዊ መሳሪያ ነው (የጣሊያን ቋንቋ እና ባህል መሰረታዊ ኮርስ ወይም ሙያዊ ስልጠና ኮርስ)።
- መሰረታዊ የጣሊያን ኮርሶች – በኮርሱ ወቅት ሰልጣኞች ለምግብና ለማደሪያ ወጪዎች ክፍያ እንዲከፈላቸው መጠየቅ ይችላሉ እና በሰዓት € 3.50 አበል የማግኘት መብት አላቸው። በስልጠናው መጨረሻ ላይ የአንድ ጊዜ አበል € 1,000 ይከፈላል።
- የሙያዊ ስልጠና ኮርሶች – በኮርሱ ወቅት ሰልጣኞች ለምግብና ለማደሪያ ወጪዎች ክፍያ እንዲከፈላቸው መጠየቅ ይችላሉ እና በሰዓት € 3.50 አበል የማግኘት መብት አላቸው። በስልጠናው ማብቂያ ላይ የአንድ ጊዜ አበል € 1,000 ይከፈላል (በመጀመሪያ የጣሊያን ቋንቋ እና ባህል መጨረሻ ላይ ካልተሰጠ)
ኮርሱን ለሚሳተፉ ሰዎች ያሉ መብቶች
በመሰረታዊ ወይም ሙያዊ ስልጠና ኮርስ ላይ የሚሳተፉ ወይም በቅጥር ኤጀንሲ የተቀጠሩ
የአለም አቀፍ ጥበቃ፣ ጊዜያዊ ጥበቃ እና ልዩ ጥበቃ ፈቃድ ያላቸው ተጠቃሚዎች አንዳንድ ጠቃሚ ድጎማዎች የማግኘት መብት አላቸው። በዝርዝር ሲታይ ፡-
- የመዋዕለ ሕፃናት ድጎማ – ወርሃዊ መዋእለ ሕጻናት መዋጮ ቢበዛ € 150 ህጻኑ ሶስተኛ አመት እስኪሞላው ድረስ እና በማጣቀሻው ጊዜ ውስጥ የመዋዕለ ሕፃናት ክትትል እስኪጠናቀቅ ድረስ
- ለትምህርት ድጋፍ – ለትምህርት የወጡትን ወጪዎች ለመደገፍ አንዳንድ ድጎማዎች እነሆ፡
- ለልጆቻቸው የማስተማሪያ ቁሳቁሶችና መጽሃፍት ግዢ ድጎማ (€ 200)
- በምሽት ኮርሶች ላይ ለሚማሩ ተማሪዎች መጽሃፍ ወይም ሌላ የማስተማሪያ ቁሳቁስ ግዢ ድጎማ (€ 200)
- ለዩኒቨርሲቲው ክፍያ ለከፈሉት ወጪዎች ድጎማ (€200)
- ለ 1 ኛ እና 3 ኛ ደረጃ የልምምድ ተማሪዎች መፅሃፍ ወይም ሌላ ትምህርታዊ ቁሳቁስ ለመግዛት ድጎማ (€ 200)
- ለጨቅላ ሕፃናት መሠረታዊ ፍላጎቶች ግዥ የሚከፈል ክፍያ – ለልጅዎ እንክብካቤ አስፈላጊ የሆኑ ዕቃዎችን ለመግዛት ለሚያወጡት ወጭ እስከ ሶስተኛ ዓመት እድሜ ድረስ፣ ቢበዛ €800 መዋጮ። ጥያቄው ለእያንዳንዱ ልጅ ሊደረግ ይችላል።
- ለስነ ልቦና እርዳታን የተከፈለ መመለስ – ለአንድ ደንበኛ እስከ 200 ዩሮ ድረስ ለራስ ወይም ለቤተሰብ አባላት ለደረሰባቸው የስነ ልቦና ወጪዎች ድጎማ።
ለበለጠ መረጃ፡- “Accoglienza&Lavoro” ፕሮጀክት