የሥራ ቦታ ደህንነት፣ በሥራ አካባቢ ሊከሰቱ የሚችሉ
አደጋዎችን (በሠራተኞች ላይ የሚደርሱ አደጋዎችንና
ጉዳቶችን፣ በሽታዎችን መሸከም እና መስፋፋትን)
ለመከላከልና ለመጠበቅ የተፈጠሩ ደንቦችና መሣሪያዎች
ጥምረት ሲሆን፣ በዚህም የሥራ ቦታዎችን ይበልጥ
አስተማማኝ ማድረግ ነው።
የስራ ቦታ ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ለመከላከል፣ የደህንነት
እና የንፅህና ደንቦችን መከተል፣ አደገኛ ሁኔታዎችን
መገንዘብ፣ በስራ ቦታ ደህንነት ስልጠናዎች ላይ መሳተፍ
እና አሰሪዎ ሊያቀርብልዎ የሚገባውን ተገቢውን የግል
መከላከያ መሳሪያዎች (ለምሳሌ ጫማ፣ የራስ ቆብ፣
ጓንት፣ ወዘተ) መጠቀም አስፈላጊ ነው። በተጨማሪም
አደገኛ ወይም ያልተለመዱ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ
ወዲያውኑ ሪፖርት ማድረግ አስፈላጊ ነው።
በጣሊያን፣ መደበኛ የሙሉ ጊዜ የሥራ ሰኣት በሳምንት 40
ሰዓት ነው፣ ነገር ግን እንደ ኮንትራትዎ ይወሰናል።
የተጨማሪ የሥራ ሰዓታት በኮንትራቶች ውስጥም ይሰጣል፣
ነገር ግን ውስን መሆን እና ሁልጊዜም በአሰሪው ፈቃድ
ሊሰጥ ይገባል፣ በጽሁፍ ወይም በማንኛውም ሁኔታ
በግልጽ መቀመጥ ኣለበት። ሰራተኛው በየ24 ሰዓት ውስጥ
ለ11 ተከታታይ የእረፍት ሰአታት እና በየሰባት ቀኑ ቢያንስ
ለ24 ተከታታይ ሰአታት እረፍት የማግኘት መብት አለው፣
ይህም ብዙውን ጊዜ እሁድ ነው። የሚከፈልበት አመታዊ
ፈቃድ ቢያንስ ለአራት ሳምንታት ሊቆይ ይገባል እና ድርድር
የለሽ ነው።
አይ, ኢጣሊያ ዝቅተኛ የደመወዝ ክፍያ ከሌላቸው ጥቂት
የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት አንዷ ነች። በቅርብ ጊዜ
በተደረጉ ጥናቶች መሰረት፣ ዝቅተኛ ደመወዝ በአማካይ ከ
€7 እስከ €9 በሰአት ከታክስ በፊት ይለያያል።
አንድ ሰው አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ወይም ለመበዝበዝ ምቹ
በሆነ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ ኢ-ፍትሃዊ የስራ ሁኔታዎችን
እንዲቀበል ሲገደድ የጉልበት ብዝበዛ ይባላል። ብዝበዛ
አድራጊው ለግል ጥቅሙ ሲል የሰራተኛውን ኣስገዳጅ ሁኔታ
ይጠቀማል። ብዙውን ጊዜ የሚበዘበዙ ሰዎች የገቡበት
ሁኔታ ምን እንደሆነ እንኳን አያውቁም።
በኢጣሊያ ህግ መሰረት ብዝበዛ የሚፈጸመው በሚከተሉት
ሁኔታዎች ነው፦
– ክፍያው ከሀገሪቱ የደመወዝ ስታንዳርድ አንፃር
ወይም ከሚሰራው ሰዓት ጋር ሲነጻጸር በጣም
ዝቅተኛ ከሆነ።
– እረፍት፣ በዓላት ወይም የህመም ፈቃድ ሳይኖር
ብዙ ሰዓት ከተሰራ።
– የስራ ቦታ የደህንነት ደንቦች ካልተከተሉ።
– ሰራተኛውን የሚያዋርድ መንገድ በመጠቀም
የሚመራ ከሆነ።
– የሚቀርበው የመኖሪያ ሁኔታ አስከፊ ከሆነ።
ወንጀሉ ይበልጥ ከባድ የሚሆነው በሚከተሉት ሁኔታዎች
ነው፦
– ከሶስት በላይ ሰራተኞችን የሚያካትት ከሆነ።
– መስራት ከማይችሉ ታዳጊዎች ጋር የተያያዘ ከሆነ።
– ሰዎችን ከባድ አደጋ ላይ የሚጥል ከሆነ።
– ድርጊቱ በኃይል ወይም በማስፈራራት የተፈጸመ
ከሆነ፣ ወዲያውኑ የግዴታ እስር ይከተላል። በዚህ
ሁኔታ ከባድ የጉልበት ብዝበዛ እንደሆነ ይቆጠራል።
– ብዝበዛ ከሌሎች ከባድ ወንጀሎች ጋር ሊያያዝ
ይችላል፣ ለምሳሌ፦
– ባርነት
– የሰዎች ዝውውር (ለጉልበት፣ ለሴተኛ አዳሪነት፣
ለመለመን፣ ለአካል ክፍሎች ዝውውር)
– ባሪያዎችን መግዛት ወይም መሸጥ
የጣሊያን ህጎች በህገወጥ የሰዎች ዝውውር፣ በባርነት
ወይም በስራ ብዝበዛ ወንጀል የተጎዱ ሰዎችን ለመጠበቅ
በርካታ እርምጃዎችን ይደነግጋል። በተለይም፣ በመጀመሪያ
ከግምት ውስጥ መግባት ያለበት መሳሪያ አንቀጽ 18 ነው።
ይህ አንቀጽ ህገወጥ የሰዎች ዝውውር ወይም “የኃይል እና
ከባድ ብዝበዛ ሰለባ” ለሆኑ የውጭ ዜጎች ልዩ የመኖሪያ
ፈቃድ እንዲሰጣቸው የሚያስችል ሲሆን ይህም ለልዩ
ጉዳዮች የመኖሪያ ፈቃድ ይባላል።
አዎ፣ ይችላሉ። ሂደቱ እንደ ሁኔታው ይለያያል።
. የሰዎች ዝውውር፣ የጥቃት ወይም ከባድ ብዝበዛ ሲኖር::
የሰዎች ዝውውር፣ ጥቃት ወይም ከባድ ብዝበዛ
ከተፈጸመብዎ፣ በ"ልዩ ጉዳዮች" የሚሰጠውን የመኖሪያ
ፈቃድ (በኢሚግሬሽን ሕግ አንቀጽ 18 ስር) ማመልከት
ይችላሉ። ይህንን ፈቃድ ለማግኘት ሁለት መንገዶች አሉ።
– ያለ ፖሊስ ጥሪ—በፀረ-ጥቃት ማዕከላት፣ በጤና
እና ማህበራዊ አገልግሎት ማእከላት ወይም
በሌሎች ተቋማት አማካኝነት የህብረተሰብ ጥበቃ
ፕሮግራም ውስጥ በመግባት።
– በፖሊስ ጥሪ ወይም የወንጀል ክስ ከተጀመረ።
ይህ ፈቃድ ለ6 ወራት የሚሰራ ሲሆን፣ በህግ ጉዳዮች
አስፈላጊ ከሆነ ለአንድ አመት ወይም ከዚያ በላይ ሊታደስ
ይችላል ፤ በዋነኝነት የሥራ ብዝበዛ ወንጀል ከሆነ
– በምርመራ ወይም በማጣራት ሂደት የሥራ ብዝበዛ
ወንጀል በግልጽ ከታየ፣ "ልዩ ጉዳዮች – አንቀጽ 18-
ቴር" የመኖሪያ ፈቃድ ማግኘት ይቻላል። ይህ ፈቃድ
ለ6 ወራት የሚሰጥ ሲሆን፣ ሊታደስም ይችላል።
በኢጣሊያ የሚገኙ የሰለባው ቤተሰብ አባላትም ተመሳሳይ
ተጋላጭነትን ለማስወገድ በቤተሰብ ምክንያት የመኖሪያ
ፈቃድ ማግኘት ይችላሉ።
ኣይከሰስም፣ ልዩ በሆኑ ሁኔታዎች የመኖሪያ ፍቃድ
ሲጠየቅ፣ ፍርድ ቤቱ ክሱን ያቆማል፣ እናም የመኖሪያ
ፍቃድ ከተሰጠ፣ የ “የምንም ሁኔታ” ብይን ይሰጣል፣
በዚህም ሂደቱን ያጠናቅቃል።
የሥራ ብዝበዛው በፖሊስ ምርመራ ወይም በዳኝነት ሂደት
ውስጥ ከተገኘ ህጉ የግድ የጥፋቱ ሰለባ ጥፋት አድራጊዎችን
ማሳወቅ አለበት አይልም። ይልቁንስ በወንጀል ሂደቱ ውስጥ
ወንጀል ፈጻሚዎቹን ለማግኘት በሚደረገው ጥረት
አስተዋፅኦ ማድረግ ብቻ ይጠበቅበታል።
በሌላ በኩል ደግሞ የሥራ ቁጥጥር ቢሮ (የሠራተኞችን
መብቶች መከበር የሚከታተል የህዝብ ተቋም) ብዝበዛውን
ሪፖርት ካደረገ፣ የመኖሪያ ፈቃድ ለማግኘት አዎንታዊ
አስተያየት መስጠት ይችላል።
አያስፈልግም, ይህ በሕግ መሰረት ለዚህ ዓይነቱ የመኖሪያ
ፈቃድ የሚያስፈልግ መስፈርት አይደለም። ለቤተሰብ አባላት
በቤተሰብ ምክንያት የመኖሪያ ፈቃድ ማግኘት ከፈለጉ ይህ
መስፈርት ያስፈልጋቸው እንደሆነ እስካሁን ግልፅ አይደለም። ነገር ግን, በአንቀጽ 18-ter መሰረት የመኖሪያ ፈቃድ
ለማግኘት በሚጠይቁበት ጊዜ, ሰውየው ለመኖር ያሰበበትን
ቦታ ማመልከት ያስፈልጋል.
የኢሚግሬሽን ጽሕፈት ቤት (Questura) ይህንን መስፈርት
እንደማይቀር የሚቆጥረው ከሆነ, በጽሁፍ ምክንያት
እንዲጠይቁ እና ጠበቃ እንዲያማክሩ ይመከራል::
ነጻ የህግ ድጋፍ የሚሰጡ ቢሮዎች ዝርዝር ለማየት:
https://www.jumamap.it/map/litemap.php?se
r=leg
አካባቢያዊ የሰራተኛ ኢንስፔክቶሬት ቢሮዎችን ለማየት:
https://www.ispettorato.gov.it/lagenzia/strutt
ura-organizzativa/le-sedi-inl/cerca-le-sedi-
territoriali/
“ልዩ ሁኔታዎች” የመኖሪያ ፈቃድ ያለው ሰው የጤና
አገልግሎትና የትምህርት አገልግሎት የማግኘት፣ የመኖሪያ
ምዝገባ የማድረግ፣ የስራ ማፈላለጊያ ማዕከላት
የመመዝገብ፣ እንዲሁም በቅጥር ስር ወይም በግል
የመስራት መብት አለው።
አዎ፣ ለነዋሪነት ፈቃድ ማመልከቻ ያስገባ ማንኛውም ሰው
መስራት መጀመር ይችላል። ማመልከቻው እንደገባ
የሚያሳየው ደረሰኝ፣ የነዋሪነት ፈቃዱ ገና ባይወጣም
እንኳ፣ ጣሊያን ውስጥ ለጊዜው እንዲቆይ እና እንዲሰራ
ያስችለዋል።
የስራ ማጣት በArt. 18 ter መሰረት የተሰጠ የመኖሪያ ፈቃድ እንዲሰረዝ ምክንያት አይሆንም።
በስራ ብዝበዛ ሰለባ የሆነ የውጭ አገር ሰራተኛ የህብረተሰብ
እና የስራ ውህደት የመረጃ ሲስተም (SIISL) መመዝገብ
መብት አለው። በዚህ ፕላትፎርም የስራ ልምድ ማቅረብ እና
የተለያዩ የስልጠናና የስራ እድሎችን ማየት ይቻላል። በSIISL
ለመመዝገብ በቀጥታ የኢንፒኤስን (INPS) ፕላትፎርም
መጠቀም ወይም የጥብቅና ድርጅት ማነጋገር ይችላል።
በሁሉም ሁኔታዎች ዲጂታል መታወቂያ (SPID ወይም CIE)
ያስፈልጋል።
“ልዩ ሁኔታዎች – አንቀጽ 18 ቴር” የሚል የመኖሪያ ፈቃድ
ያላቸው ግለሰቦች:
– የሁለቱንም የማካተት አበል (Assegno di
inclusione) እና ለጥገኞች የሚሰጥ ነጠላ እና
– ሁለንተናዊ አበል (Assegno unico e universale per
i figli a carico) የማግኘት መብት አላቸው።
የሁለንተናዊ አበል ለማግኘት የመኖሪያ ሁኔታዎን፣ የገቢዎን
እና የንብረትዎን ሁኔታ በተመለከተ የተወሰኑ መስፈርቶችን
ማሟላት አለብዎት። ለጥገኞች የሚሰጥ ነጠላ እና
ሁለንተናዊ አበል ለማግኘት ደግሞ የመኖሪያ ፈቃዱ ባለቤት
እና ጥገኞች የሆኑ ልጆቻቸው ብቁ ይሆናሉ።
ለእነዚህ ጥቅሞች ማመልከቻው የመኖሪያ ፈቃድ ጥያቄ
ቀርቦ እንደነበር የሚያረጋግጥ ደረሰኝ ብቻ በማቅረብ
ማስገባት ይቻላል።
በሀገር አቀፍ ደረጃ ሰፊ የሆነ ድጋፍ፣ መረጃ እና የምክር
አገልግሎት አለ። በማንኛውም ጊዜ ስምዎን ሳይገልጹ በነጻ
እና ስም-አልባ በሆነ መስመር ሀገር አቀፍ የስልክ ቁጥር
800290290 መደወል ይችላሉ።
እንዲሁም፣ ከሠራተኛ ማኅበራት፣ ከማህበራት እና
ከተመዘገቡበት የአከባቢ ማዘጋጃ ቤት አገልግሎቶች ጋር
መነጋገር ይችላሉ። በስራ-ተኮር ብዝበዛ ላይ ድጋፍ የሚሰጡ ማዕከሎች ዝርዝርን
ለማየት፡
https://www.jumamap.it/it/soleil/
የህግ እርዳታ የሚሰጡ ማዕከሎች ዝርዝርን
ለማየት፡https://www.jumamap.it/map/litemap.
php?ser=leg
አዎ፣ ይህን ማድረግ በጣም አስፈላጊ ነው። በተለይም አሰሪ
ከስራ ጋር በተያያዘ በአደጋ ምክንያት ሰራተኛ ከ3 ቀናት በላይ
ከስራ የቀረ የሆነ እንደሆነ (አደጋው የደረሰበት ቀን
ሳይጨምር) ለ INAIL (የኢንሹራንስ ተቋም) ማሳወቅ
አለበት። በስራ ምክንያት የሚመጡ በሽታዎችም
በሰራተኛውም ሆነ በአሰሪው ለ INAIL ሪፖርት መደረግ
አለባቸው።
ከስራ ቦታ ጉዳት ከደረሰቦ፣ የሚከተሉትን ማድረግ አለቦ፦
– ጉዳቱ ቀላል ቢመስልም እንኳ ወዲያውኑ ለአሰሪዎ
ማሳወቅ። ይህን ካላደረጉ፣ ከማሳወቆ በፊት
ለቆዩባቸው ቀናት የሚከፈል የገንዘብ ድጋፍ (ካሳ)
ላያገኙ ይችላሉ።
– ለአሰሪዎ ስለህክምና ምስክር ወረቀት
(የመታወቂያ ቁጥር፣ ቀን እና ለማገገም
የሚጠበቀው ጊዜ) እና ስለሌሎች ተያያዥ ምስክር
ወረቀቶች መረጃ መስጠት።
በስራ ምክንያት የሚመጣ በሽታ ካለብህ፣ የሚከተሉትን
ማድረግ አለቦ፦
– በሽታውን መታየት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ባሉት
15 ቀናት ውስጥ ለአሰሪዎ ማሳወቅ። ይህን
ዘግይተው ካደረጉ፣ ሪፖርት ከማድረጎ በፊት
ለነበሩት ቀናት የካሳ ክፍያ የማግኘት መብትዎን
ያጣሉ።
– በዚህም ሁኔታ የመጀመሪያውን የህክምና
ምስክር ወረቀት እና ከሱ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን
የህክምና ምስክር ወረቀቶች መረጃ መስጠት
አለዎ።
አንድ አሰሪ ከሶስት ቀናት በላይ ከስራ መቅረትን
የሚያመላክት የህክምና ምስክር ወረቀት ከደረሰው በኋላ
በሁለት ቀናት ውስጥ በINAIL ድህረ ገጽ ላይ በሚገኘው ቅጽ በመጠቀም በኤሌክትሮኒክ መንገድ ሪፖርት ማቅረብ
አለበት። አሰሪው ሪፖርቱን ካላቀረበ፣ ሰራተኛው ራሱ በግል
እርምጃ መውሰድ ይችላል።
ሰራተኞች ወዲያውኑ የህክምና እርዳታ የማግኘት እና በስራ
ላይ በሚደርስ አደጋ ወይም በሙያዊ በሽታዎች ምክንያት
ለደረሰ ጉዳት የካሳ ክፍያ (ገንዘብ) የማግኘት መብት
አላቸው። የስራ ቀጣሪው ለስራ ቦታ ደህንነት ኃላፊነት አለበት
እና አስተማማኝ የስራ አካባቢ ማቅረብ አለበት።
ቀጣሪዎ የውል እና የማህበር መብቶችዎን አያከብርም
ብለው ካሰቡ፣ ይህን ኢፍትሃዊ ሁኔታ ለማስቆም እና
ለደረሰብዎ ጉዳት ካሳ ለማግኘት ከፈለጉ፣ የሰራተኛ ማህበር
ድርጅትን ወይም ጠበቃን ማነጋገር ይችላሉ።
ማንኛውም ዓይነት ትንኮሳ ወይም መድልዎ በሥራ ቦታዎ
ዋና ኃላፊ፣ የሥራ ቦታ ደህንነት ኃላፊ፣ ወይም እንደ ፖሊስና
ካራቢኒየሪ (Polizia, Carabinieri) ያሉ የሕግ አስከባሪ
አካላት ወይም የክልል የሥራ ተቆጣጣሪ (Ispettorato
territoriale del lavoro) ጋር ወዲያውኑ ማሳወቅ
አስፈላጊ ነው። የሰራተኞች መብት በሚጣስበት ጊዜ
ሊገናኙዋቸው የሚችሉ ድርጅቶች እና ባለስልጣናት አሉ።
ከዘር፣ ጾታ፣ ጾታዊ ዝንባሌ ወይም ከጤና ሁኔታ ጋር
በተያያዘ ከሚደርስ መድልዎ ራስዎን ለመከላከል
የሚከተለውን ገጽ ይመልከቱ:
https://www.jumamap.it/it/faq/discriminazion
i/
ለሴት ተጎጂዎች (በሥራ ቦታ ላይ ብቻ ሳይሆን) የመከታተል፣
የትንኮሳ እና የጥቃት ድርጊቶች ከደረሰብዎ የነፃ የስልክ
ቁጥር 1522 ደውለው ማንነትዎ ሳይገለጽ እርዳታና ድጋፍ
ለማግኘት ሊያነጋግሩት የሚችሉትን በአቅራቢያዎ የሚገኝ
ማህበር እንዲጠቁምዎ መጠየቅ ይችላሉ። በአቅራቢያዎ
የሚገኝ ማህበር ለማግኘት እና ስለ ጉዳዩ የበለጠ ለመረዳት
ስለ ጾታ-ተኮር ጥቃት የሚገልጸውን የJuma Map ድረ-ገጽ
ይመልከቱ።
በኢጣሊያ የጉልበት ብዝበዛን ለመዋጋት በርካታ ፕሮጀክቶች
መኖራቸውን ያውቃሉ?
Piemonte, Friuli Venezia Giulia, Emilia
Romagna, Liguria, Veneto
Common Ground
https://www.piemonteimmigrazione.it/lp/comm
onground
Lazio, Toscana, Umbria, Molise, Marche
S.O.L.E.I.L.
https://www.jumamap.it/it/soleil/
Umbria
Umbria Legale e Sicura
https://www.regione.umbria.it/-/umbria-legale-e-sicura-interventi-di-supporto-all-integrazione-
sociale-sanitaria-abitativa-e-lavorativa
Sicilia, Basilicata, Calabria, Campania, Puglia
Su.Pr.Eme
https://www.supremeitalia.org/focus/helpdes
k-anticaporalato/
Sardegna
C.A.S.L.I.S.
Queste FAQ sono state realizzate da Arci a
partire dai testi di Infomigranti
https://www.infomigranti.org/services/lavoro/
Consulta tutti i progetti attivi:
https://integrazionemigranti.gov.it/it-it/Altre-info/e/2/o/18///id/32/Azioni-e-progetti
Queste FAQ sono state realizzate da Arci a
partire dai testi di Infomigranti
https://www.infomigranti.org/services/lavoro/
![]()


