የቤተሰብ ውህደት

የቤተሰብህን አባላት በሕጋዊና ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ ወደ ጣሊያን ለማምጣት የሚያስችል አሰራር ነው።

ከሚከተሉት የቤተሰብ አባላት ጋር እንደገና ለመገናኘት መጠየቅ ይችላሉ፦

 

  • የትዳር ጓደኛ (ባል ወይም ሚስት) በህጋዊ መንገድ ያልተለያዩና እድሜያቸው ቢያንስ አስራ ስምንት አመት የሆናቸው፣ ወይም በሲቪል አንድነት ያለው አጋር (በጣሊያን ወይም በውጭ)፣ የውጭ ዜጋና በጣሊያን ውስጥ የማይኖር;
  • ለአካለ መጠን ያልደረሱ የራስ ልጆች፣ የማደጎ፣ በአደራ የተሰጡ፣ ከትዳር ጓደኛ ወይም ከጋብቻ ውጪ የተወለዱ፣ ያላገቡ ሌላው ወላጅ ካለ፡ ፈቃዱን እስከሰጠ ድረስ;
  • ጥገኛ የሆኑ ለአካለ መጠን የደረሱ ልጆች፣ በትክክለኛ ምክንያቶች አስፈላጊ ፍላጎቶቻቸውን ማሟላት ካልቻሉና ሙሉ በሙሉ የአካል ጉዳተኛ ከሆኑ;
  • እስከ 65 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ጥገኛ ወላጆች፣ በትውልድ አገራቸው ወይም ከሚመጡበት ኣገር ሌላ ልጆች ከሌላቸው;
  • ከ65 ዓመት በላይ የሆናቸው ጥገኛ የሆኑ ወላጆች፣ ሌሎች ልጆች ቢኖሩዋቸውም፡ ነገር ግን በተመዘገቡና ከባድ የጤና ምክንያቶች እነርሱን መርዳት ካልቻሉ።

ከ18 አመት በታች ከሆንክና ብቻህን ከሆንክ ከወላጆህ ወይም አንተን ከሚንከባከቡ ሌሎች የቤተሰብ አባላት የተነጠልክና በጣሊያን ውስጥ እንደ ስደተኛነት እውቅና ካገኘህ፣ ምንም ይሁን ምን የዕድሜ ገደብ በሌለው ከወላጆህ ጋር የመገናኘት መብት አለህ።

ለቤተሰብ ዳግም ውህደት ለማመልከት፣ የዓለም አቀፍ ጥበቃ ላላቸው ሰዎች፣ የሚያስፈልጉ፦

 

  • የመኖሪያ ፈቃዱ፡ ያልወደቀ ወይም በመታደስ ሂደት ላይ መሆን አለበት። በዚህ ሁኔታ፣ ጥያቄው ጊዜው ካለፈበት በ 60 ቀናት ውስጥ መሆን አለበት;
  • ፓስፖርት ወይም የጉዞ ሰነድ (ካለ) ;
  • የዝምድና ግንኙነቶችን የሚያመለክት፣ ለአካለ መጠን ያልደረሰ ዕድሜና የቤተሰብ ሁኔታ (ካለ) የሚያረጋግጡ ሰነዶች።

በጣሊያን ውስጥ በመደበኛነት ለሚኖሩ ሌሎች የመኖሪያ ፈቃድ ዓይነቶች ላላቸው ሰዎች የገቢና የመኖርያ ብቁነት መስፈርቶችን ማክበር አስፈላጊ ነው። ለተጨማሪ መረጃና ለተለያዩ የመኖሪያ ፈቃዶች እንደገና ለቤተሰብ ማገናኘት ማመልከት ስለሚቻልና አስፈላጊ መስፈርቶች ላይ፣ የወሰኑትን የሜልቲንግ ፖት አውሮፓ ድረገጽ Melting pot Europa ማየት ይችላሉ።

የቤተሰብ መልሶ ማገናኛ ሰነድ (የኑላ ኦስታ ) ጥያቄ

የአሰራር ሂደቱ ሁለት ደረጃዎችን ያካተተ ነው፡ የኑላ ኦስታን ጥያቄ በምትገኝበት ግዛት የስደተኞች ጉዳይ የሚመለከት ጽ/ቤት (ስፖርተሎ ኡኒኮመጠየቅና በውጭ አገር በጣሊያን ኤምባሲ ወይም ቆንስል የቪዛ ጥያቄን መከተል።

ኑላ ኦስታን ለመጠየቅ ማድረግ ያለብህ:

  • የ ስፒድ (SPID) ዲጂታል መሳርያ ማግኘት (በጣልያን ፖስታ ቤት በመሄድ ማግኘት ትችላለህ);
  • የ 16.00 ዩሮ የቀረጥ ማህተም መግዛት (ማርካ ዳ ቦሎ);
  • ስፒድ የሚሰራውን ስራ በማመስገን፡ በዚህ ድረገጽ www.nullaostalavoro.dlci.interno.it በመግባት የሚከተለውን ሰነድ በሞምላት የገዛሀውን የቀረጥ ማህተሙን (ማርካ ዳ ቦሎ)ቁጥር መሙላት;

ከዚያ በምትኖርበት ቦታ የሚገኙ የኢሚግሬሽን ጽ/ቤት (ስፖርተሎ ኡኒኮይጠሩሃል እናም የሚከተሉትን ሰነዶች ይዘህ መሄድ ያስፈልገሃል:

  • ማመልከቻው ስታመለክት ቁጥሩን በማመልከቻው ያካተትከው ማርካ ዳ ቦሎ ኦሪጂናሉ;  • ሌላ የ € 16.00 የቀረጥ ቴምብር በኑላ ኦስታ ላይ የሚለጠፍ;
  • የመኖሪያ ፈቃድህና ፎቶ ኮፒ;
  • ለሚመጡት የቤተሰብህ አባላት የሰነዶቻቸው ቅጅ (ካለ)።

የቤተሰብህ የዝምድና ሁኔታ የሚያረጋግጥ ሰነድና የመኖርያ ኣድራሻ (ራስህን ጽፈህ ልታዘጋጅ ትችላለህ)።

ኑላ ኦስታን አንዴ ካገኘህ በኋላ ቪዛውን ለማግኘት፡ ኦሪጂናሉ ወደ ቤተሰቦችህ በመላክ፡ ወደሚመለከተው የጣልያን ቆንስል ወይም ኤምባሲ እንዲሄዱ ማድረግ፡ እስከዚያው ኤምባሲው በቴሌማቲክ ወይም በመስመር ከኢሚግረሽን ኦፊሱ (ስፖርተሎ ኡኒኮይደርሰዋል።

እንዲሁም ከስፖርተሎ ኡኒኮው; የጽሑፍ መልእክት ከነስልክ ቁጥሩ ይላክልሃል፡ በዚህም መሰረት ወደ ጽ/ቤቱ  (ስፖርተሎ ኡኒኮበመሄድ ለቤተሰብህ ቀጠሮ ትይዛለህ። በእርግጥ የቤተሰብህ አባል ጣሊያን ከገባበት ጊዜ አንስቶ ጽ/ቤቱ ለማነጋገርና የመኖሪያ ፈቃድ እንዲሰጥ ለመጠየቅ 8 ቀናት ይኖራቹሃል፡፡

ሁሉንም ነገር በትክክል ካከናወንክና ማመልከቻው ተቀባይነት ካገኘ፡ ከቀረበበት ቀን አንስቶ በ 90 ቀናት ውስጥ ኑላን ኦስታውን ታገኛለህ። የኑላ ኦስታ ጥያቄ በሆነ ምክንያት ተቀባይነት ካላገኘ ግን የእሱ መብት እንዳለህ ካመንክ፡ ለመኖሪያው ቦታ ተራው ፍ/ ቤት (ልዩ ክፍል) ይግባኝ ማለት ትችላለህ፡፡

ሕጉ ቪዛው ከተጠየቀ በ 30 ቀናት ውስጥ እንዲሰጥ ይጠይቃል ፣ ግን ጊዜው ሊረዝም ይችላል።

  • ማመልከቻውን ከመላክህ በፊት ሁሉንም የማመልከቻውን መስኮች በተለይም የቤተሰብህ አባላትን ስምና የልደት ቀን የሚመለከቱትን በጥንቃቄ ተመልከት። ስሞችና የልደት ቀናት በፓስፖርት ውስጥ ካሉት ጋር መዛመድ አለባቸው።
  • የቤተሰብህ አባላት ያሉበት የትውልድ ወይም የመኖሪያ ቦታ ኣመልክት። በእነዚህ አገሮች የጣሊያን ዲፕሎማሲያዊ ተልዕኮ ከሌለ የቤተሰብህ አባላት ለቪዛ የሚያመለክቱበትን ሀገር ወዲያውኑ አሳውቅ ። እንዲሁም በኋላ የቤተሰብህ አባላት የመኖሪያ አገር መቀየር ይቻላል፣ ነገር ግን ይህ በፕሬፌክተሩ የሚፈቀድናና የተወሰነ ጊዜ ይወስዳል።
  • የአለም አቀፍ ጥበቃ የመኖርያ ፈቃድ ባለቤቶች፣ የገቢና የጤና መድህን ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት አያስፈልጋቸውም።
  • ኑልላ ኦስታ የሚሰራው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ6 ወራት ነው፣ ስለዚህ በ6 ወራት ውስጥ ወደ ኤምባሲው ማድረስ አለህ። ሁሉም ሰነዶች ለቪዛ ማመልከቻ በጊዜው ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጥ እና በኤምባሲው ውስጥ በቀጠሮው ላይ መዘግየቶች ካሉ ፣ የአርቺ ነፃ የስልክ ቁጥር፣ የአካባቢ ማህበራትን  ወይም ጠበቃን ያለክፍያ አግኙ።

በጣልያን ካሪታስ፣ ኮንሶርስዮ ኮሙኒታስና ዩኤንኤችሲአር የተዘጋጀ፦ የበለጠ መረጃ ለማግኘት http://ricongiungimento.it/ ይመልከቱ።

የቪዛ ማመልከቻ ለውጭ የጣሊያን ግንኙነት (ኤምባሲዎች እና ቆንስላዎች)

ምን ሰነዶች ያስፈልጋሉበውጭ አገር የኢጣሊያ ኤምባሲዎች የመረጃ ወረቀቶችን ያማክሩ

የኑላ ኦስታን ሰነድ ከሰበሰብክ በኋላ ኦርጅናሉ ለቤተሰብ አባላት መላክ አለብህ። አንዴ ከተቀበሉ በኋላ፣ ቤተሰብህ ለቪዛ ለማመልከት ከጣሊያን ኤምባሲ ወይም ቆንስላ ጋር ቀጠሮ መያዝ አለበት።

  • የቤተሰብ ትስስርን የሚያረጋግጡ ሰነዶች ሁሉም በጣሊያንኛ መተርጎምና ህጋዊ መሆን አለባቸው።
  • የጣሊያን ዲፕሎማቲክ ተጠሪዎች አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ፡ ማንኛውንም ተጨማሪ ሰነድ መጠየቅ ይችላሉ። ሁሉም ሰነዶች በኦሪጅናልና በቅጅ መቅረብ አለባቸው። ኮፒዎቹ ከቪዛ ማመልከቻ ጋር ሲቀርቡ ዋናው ሰነዶች ለአመልካቾች ይመለሳሉ። በጣሊያን ውስጥ የሚኖር የቤተሰብ አባል የመታወቂያ ካርድ ወይም ፓስፖርት ፎቶ ኮፒ ካልተጠየቀ በስተቀር ምንም አይነት ቅጂ አይቀበልም።
  • በስም ፣ ቅድመ ስሞች ፣ የስም ቅደም ተከተል እና / ወይም የተሳሳተ የልደት ቀን እና / ወይም የትዳር ጓደኛ / ልጅ / ወላጅ ቦታ በ “ኑላ ኦስታ” ውስጥ ያሉ የፊደል አጻጻፍ ልዩነቶች ማመልከቻውን ለማካሄድ መዘግየትን ያስከትላል ፣ ልዩነት የጣሊያን የፖሊስ ዋና መሥሪያ ቤት ኃላፊነት ነው። በቪዛ ማመልከቻ ቅጹ ላይ አመልካቹ የሚሰራውን የሞባይል ስልክ ቁጥር እና የኢሜል አድራሻውን ማመልከት አለበት። ቆንስላ ጄኔራል በዚህ ሚዲያ ጠቃሚ ማሳሰቢያዎችን ሊልክ ስለሚችል እና በኢሜል ምላሽ ሊሰጡ ስለሚችሉ አመልካቹ ኢሜይሉን እንዲያረጋግጥ ይመከራል። ከተቻለ ጥያቄውን በ ፔክ በኩል ማስተላለፍ ጥሩ ነው፤ ለዚህም የአካባቢ ማህበራትን ማነጋገር እና፨ወይም በጠበቃ መታገዝ ይቻላል።
  •   አስታውስ የሶስተኛ ወገኖች ወይም አካላት ክፍያ የቤተሰብን የማገናኘት ሂደቶችን ውጤታማ ጥቅም ወይም ቀላል ከማድረግ ጋር እንደማይዛመድ አስታውስ።
  • ቪዛው የሚሰራው ለአንድ አመት ነው።
  • ለዲኤንኤ ምርመራ፣ የአርቺ ነፃ የስልክ ቁጥር ወይም የዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት OIM: +39 06 441609.225 /233 /260 /210) ማግኘት ትችላለህ።  የምርመራው ዋጋ ለአንድ ሰው €230 ነው። ለምርመራው መክፈል ካልቻክ፣ ዋስትና ካላቸው ማህበር ድጋፍ መጠየቅና በነፃ እንዲደረግ መጠየቅ ትችላለህ።
  • ለበለጠ መረጃ፣ ድጋፍ ወይም ምክር ፡ ወይም ቢሮን አላግባብ መጠቀምና የመብት ጥሰት ቢያጋጥም እንኳን ፡ በጣሊያን የሚገኙ የአካባቢ ማህበራትን ማነጋገር ወይም የሚከፈልበት የህግ ምክር መጠየቅ ትችላለህ።

ማመልከቻውን ለመሙላት መረጃና ድጋፍ ለማግኘት ማንን ማግኘት እችላለሁ?

ለጥገኝነት ጠያቂዎች እና ስደተኞች (ARCI) ነፃ የስልክ ቁጥር ያግኙ፡–  800905570 o (+39)3511376335 

ወይም ኢሜይል ጻፍላቸው

numeroverderifugiati@arci.it  

ለበለጠ መረጃ፣ ድጋፍ ወይም ምክር ፡ ወይም ቢሮን አላግባብ መጠቀምና የመብት ጥሰት ቢያጋጥም እንኳን ፡ በጣሊያን የሚገኙ የአካባቢ ማህበራትን ማነጋገር ወይም የሚከፈልበት የህግ ምክር መጠየቅ ትችላለህ።

በውጭ አገር ባሉ የጣሊያን ኤምባሲዎች ላይ ያሉ የመረጃ ወረቀቶች

ለቤተሰብ ምክንያቶች የመኖሪያ ፈቃድ ጥያቄ

ቤተሰብህ ጣሊያን በገቡ በ 48 ሰአታት ውስጥ የእንግዳ ተቀባይነት ሰነድ ይዘህ ለፖሊስ ዋና መሥሪያ ቤት ማድረስ አለህ።

በመጡ በ 8 ቀናት ውስጥ፣ የቤተሰብህ አባላት በቤተሰብ ምክንያቶች የመኖሪያ ፍቃድ ለመጠየቅ ቅጾቹን የያዘውን ኪት በሚሰጣቸው የኢሚግሬሽን ዴስክ ውስጥ መግለጽ አለባቸው።

እነዚህ መረጃዎች የተዘጋጁት ከፓሌርሞ አርቺ ፖርኮ ሮሶ ጋር በመተባበር ነው።

I VIDEO

JumaMap ምንድነው

JumaMap – Services for Refugees በፍጥነት በአካባቢህ ያሉ ጠቃሚ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ የተዘጋጀ ካርታ ነው።
እዚህ መተኛት፣ መብላት፣ የጣሊያን ቋንቋ መማር፣ የጤና፣ የህግ ወይም የሥነ–ልቦና ድጋፍ ማግኘት የሚቻለውን ቦታ እና ለሚንቀሳቀሱ እና ለመኖሪያ የሌላቸው ሰዎች የተዘጋጀ ብዙ ሌሎች አገልግሎቶች ማፈለግ ትችላለህ/ትችላለሽ።

ፕላትፎርሙ በ17 ቋንቋዎች ይገኛል።
ቋንቋውን ከላይ ባለው ሜኑ መምረጥ ትችላለህ/ትችላለሽ — አልባኒያኛ፣ አማርኛ፣ ዓረብኛ፣ በንጋሊ፣ ቻይንኛ፣ ዳሪ፣ ፋርሲ፣ ፈረንሳይኛ፣ እንግሊዝኛ፣ ፓሽቱ፣ ፑንጃቢ፣ ራሽያኛ፣ ሶማሊኛ፣ ስፓኒሽ፣ ትግርኛ፣ ዩክሬንኛ፣ ኡርዱ፣ ዎሎፍ።

JumaMap በስልክህ/ስልክሽ ላይም መጠቀም ትችላለህ/ትችላለሽ፤ www.jumamap.it ይጎብኙ።

እንኳን በደህና መርበብ ማዕከል (Welcome Center)

በፊት ለፊት እገዛ ከፈለጉ እዚህ መምጣት ይችላሉ፦

ሰኞ
10:00 – 14:00 – የማህበራዊ አቀናባሪ ጽሕፈት

ማክሰኞ
10:00 – 14:00 – የሥነ–ልቦና ድጋፍ (18–26 ዓመት)
14:00 – 17:00 – የጤና ድጋፍ
14:00 – 18:00 – የማህበራዊ አቀናባሪ ጽሕፈት
14:00 – 18:00 – የህግ ድጋፍ

ረቡዕ
10:00 – 14:00 – የማህበራዊ አቀናባሪ ጽሕፈት

ሐሙስ
10:00 – 14:00 – የህግ ድጋፍ (18–26 ዓመት)
14:00 – 18:00 – የማህበራዊ አቀናባሪ ጽሕፈት

ዓርብ
10:00 – 14:00 – የማህበራዊ አቀናባሪ ጽሕፈት
16:30 – 19:30 – የህግ ድጋፍ

ዲጂታል ድጋፍ

ማክሰኞ 9:30 – 14:00
ረቡዕ 10:00 – 15:00
ሐሙስ 9:30 – 16:30

ለተጠጋጋሚ እና ለስደተኞች ነጻ የስልክ ቁጥር

ለመረጃ እና ለስልክ ድጋፍ የArci ነጻ ቁጥር ይደውሉ፦
800 905 570 (ከጣሊያን)
+39 351 1376335 (WhatsApp፣ Lycamobile እና ከውጭ)

ከሰኞ እስከ ዓርብ 9:30–17:00 ይመልሳል፤ ቋንቋዊ ተርጓሚዎች በ35 ቋንቋዎች ይረዱ።
ወይም ኢሜይል ይላኩ፦ numeroverderifugiati@arci.it

ለአካላዊ ጉዳተኞች የነጻ ስልክ

NABILA ለሰዎች ሁሉ ስለሚንቀሳቀሱ እና ችግኝ ያላቸው ሰዎች ድጋፍ፣ መምሪያ እና መስማት የሚሰጥ አገልግሎት ነው።
በነጻ ቁጥር 800 999 977 ይደውሉ።
በፊት ለፊት ለመናገር፣ በArci Nazionale የኢሚግሬሽን ቢሮ Via dei Monti di Pietralata 16 – ሮማ ቀጠሮ ይያዙ።

ለታናሾች እና ለወጣት ሰዎች የመስማት ቦታ

U-Report On The Move ህጋዊ ድጋፍ ማግኘት፣ እንዲሁም ስሜቶችህን፣ ችግኝህን እና ያስጨንቅህን ነገር በጤና እና በነጻ ሁኔታ ለመናገር የሚያስችል ደህንነታዊ ቦታ ነው።
ባለሙያ/ባለሞያ ይሰማልሃል/ልሽ እና እንዲሁም ትክክለኛውን ድጋፍ እንዲያገኝ ይረዳል።
አገልግሎቱ ከሰኞ እስከ ዓርብ 9:00–18:00 ነው።

ለመጠቀም፣ በFacebook Messenger መልእክት ይላኩ፣ በU-Report On The Move ፕላትፎርም።
የሥነ–ልቦና ባለሙያዎች ሙሉ በሙሉ ይመልሳሉ እና የተስተካከለ ድጋፍ ይሰጣሉ።