FAQ – ተደጋግሞ የሚነሱ ጥያቄዎች

በትውልድ አገርህ ህግ መሰረት ለጋብቻ እንቅፋት እንደሌለህ ወይም እንዳላገባህ የሚገልጽ ሰነድ በጣልያን ለሚመለከተው የጋብቻ ኣስፈጻሚ ጽሕፈት ቤት ማቅረብ አለብህ (c.d. “nulla osta”)  

አስፈላጊ፡ የትውልድ አገርህን ባለሥልጣናት ማነጋገር ካልቻልክ ወይም ካልፈለግክ፡ በምትኖርበት ማዘጋጃ ቤት፡ ለጋብቻ አስፈጻሚ የመዝገብ ቤት ሠራተኛውን ከፍርድ ቤት ከስድስት ወር ባልበለጠ ጊዜ የተፈረመ ሰነድ (አቶ ኖቶርዮ) ማቅረብ አለብህ። 

የእውቅና ወረቀት ወይም አቶ ኖቶርዮ ማድረግ የምትችለው

ወደ ፍርድ ቤት በመሄድና በኃላፊነትህ ስር በሁለት ምስክሮች ፊት ባለትዳር ኣለመሆንህን ማስመስከር

ማግባት እንደምትችል ለሚጠየቀውን የሚመሰክሩ (“ማረጋገጫ ሰጭ”) ሁለት ሰዎች በመያዝ ወደ ኖታዮ መሄድ።

ያላገባህ መሆንህን የምታሳውቅበት ሰነድ ለማዘጋጀት ወይም ለመጻፍ ወደ ጋብቻ ኣስፈጻሚው የማዛጋጃ ቤቱ ጽህፈት ቤት ወይም ወደ ኖታዮ መሄድ። 

ለጋብቻ እንቅፋት እንደሌለህ ወይም እንዳላገባህ የሚገልጽ ሰነድ በጣልያን ለሚመለከተው የጋብቻ ኣስፈጻሚ ጽሕፈት ቤት ማቅረብ አለብህ (c.d. “nulla osta”)

በጣልያን አገር : ዩኤንኤችሲአር – UNHCR ለስደተኞች የጋብቻ ማረጋገጫ የመስጠት ሃላፊነት ያለው ድርጅት ነው።

1. ስድስት ወር ያላለፈው አቶ ኖቶርዮ (ኦርጅናል)

የእውቅና ወረቀት ወይም አቶ ኖቶርዮ ማድረግ የምትችለው

ወደ ፍርድ ቤት በመሄድና በኃላፊነትህ ስር በሁለት ምስክሮች ፊት ባለትዳር ኣለመሆንህን ማስመስከር;  

ማግባት እንደምትችል ለሚጠየቀውን የሚመሰክሩ (“ማረጋገጫ ሰጭ”) ሁለት ሰዎች በመያዝ ወደ ኖታዮ መሄድ።

ያላገባህ መሆንህን የምታሳውቅበት ሰነድ ለማዘጋጀት ወይም ለመጻፍ ወደ ጋብቻ ኣስፈጻሚው የማዛጋጃ ቤቱ ጽህፈት ቤት ወይም ወደ ኖታዮ መሄድ።

2. ከኮሚሽን ያገኘሀው የአለም አቀፍ የጥገኝነት እውቅና ሰነድ ፎቶ ኮፒ;

3. ያልወደቀ የመኖርያ ወረቀት ፈቃድ ፎቶ ኮፒ;

4. የምታገባትን ወይም የምታግቢውን ያልወደቀ የመታወቅያ ወረቀት ፎቶ ኮፒ

ሰነዶቹን በፖስታ ወደ UNHCR አድራሻ ፣ በቪያ ለዮፓርዲ 24 – 00185 ሮም ወይም በተረጋገጠ (PEC) ኢሜል መላክ ትችላለህ (unhcr@pec.it) 

በአማራጭ የጽ/ቤቱ መክፈቻ ሰዓቶች በመመልከት ወደ ዩኤንኤችሲአር ኢታልያ (UNHCR ITALIA) ላርጎ ለዮፓርዲ 22  00185 ሮም በቀጥታ መሄድ ትችላለህ። ( https://www.unhcr.org/it/chi-siamo/contatti/ ).

የላክከውን ዶኩሜንት መልሰህ ለመቀበል ስልክ ቁጥርህ፣ የመኖርያ ኣድራሻህንና በቤትህ መጥርያ ያለውን ስምን በማካተት በደምብ መጻፍ አትርሳ።

ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ ማቅረብ ትትችላለህ ፣ ዳኛው በጋብቻው ላይ ምንም እንቅፋቶች እንደሌሉ እንዲያረጋግጥላቸው በመጠየቅ መዝጋቢው ጋብቻውን ለህዝብ በይፋ እንዲገለጽ ማዘዝ ይችላሉ ፡፡

Pidgin English
Pular
Soninke
Bambara