ብቻውን የሚመጣው የውጭ ዜጋ ማለት (MSNA) ያለ ወላጅ ወይም ሌላ ህጋዊ ሃላፊነት የሚወስድለት አዋቂ ሰው የሌለው ጣልያን የደረሰ ሰው ነው። ብቻህን የመጣህ ለአካለ መጠን ያልደረሰ የውጭ ዜጋ ከሆንክ ድንበሩ ስትደርስ ሊመልሱህ እንደማይችሉና ከጣሊያን ግዛት ሊያባርሩህ እንደማይችሉ ሕጉ ይደነግጋል ፡፡ በተጨማሪም ጣልያን ከደረስክ በእንግዳ መቀበያ ማእከል የማስተናገድ መብት አለህ፡ የህክምና አገልግሎት ማግኘትና ትምህርት ቤት መሄድ ትችላለህ፡፡
በባህር ወይም በየብስ ጣሊያን ስትደርስ ፖሊስ ማንነትህንና ዕድሜህን ያጣራል። ማንነትህን በሚያጣሩበት ግዜ አስቶርጓሚ እንዲደረግልህ መብትህ ነው። የሆነ ሰነድ ካለህ (ፓስፖርት፣ መታወቅያ፣ የትምህርት ሰርተፊኬት፣ የትውልድ ምስክር ወረቀት ወይም ሌላ)፡ የወደቀም ቢሆን ሊልኩልህ ከሚችሉ ሰዎች ግንኙነት አድርግ፡ የማንነትህንና የዕድሜህን ማረጋገጫ ይሆናሉ። ማንነትህን በሚያረጋግጡበት ግዜ ፖሊስ ፓስፖርትህን ሊወስደው ይችላል፡፡ ከመውሰዳቸው በፊት በስእል ወይም ፎቶ ኮፒ መያዝህን ኣረጋግጥ።
ከእንግዳ መቀበያ ማዕከሉ ኦፕሬተሮችና አስተርጓሚ ባለበት በቃለ መጠይቁ ላይ ት ሳተፋለህ። ይህ ቃለ መጠይቅ ያንተ መረጃ (ኢንፎርሜሽን) ለማሰባሰብና ( አገር ፣ ዕድሜ ፣ ቤተሰብ ፣ የጤና ሁኔታ ወዘት …) የሚያስፈልጉህ ነገሮች እንዲሟላልህ እድል ይፈጥራል። ምርመራዎቹ ለአካለ መጠን ያልደረስክ እንደሆንክ የሚያሳዩ ከሆነ ፣ ለአካለመጠን ያልደረሰ የውጭ አገር ዜጋ ተብለህ (MSNA) ለፍርድ ቤት ሪፖርት ይደረጋሉና ሞግዚት ወይም ቱቶር ይደረግልሃል።
ሞግዚቱ አንተ ከሚስተናገዱበት መቀበያ ማዕከል ውጭ ሆኖ በፍርድ ቤቱ የተሾመ ሰው ነው። ሞግዚቱ በሕጋዊነት አንተን ወክሎ ጣሊያን ውስጥ በምትቀላቀልበት ወቅት በሕግ በሚጠየቁ አንዳንድ ኣስፈላጊ ነገሮች አንተን ይረዳሃል።
አስተውል፡ ሞግዚት መኖሩ ያንተ መብት ነው፡ እሱን መሾም የጣሊያን መንግሥት ግዴታ ነው! በሕጉ መሠረት ፍ/ቤቱ ሞግዚት እስከሚሾም ድረስ፡ የተቀበሉህ ማዕከል ኃላፊ የሆነው ሰው ይህንን ተግባር ይፈጽማል፡፡
ከመቀበያ ማዕከል ኦፕሬተሮችና ከቱቶሩ ጋር በመሆን የተለያዩ መንገዶችን መገምገም ትችላላቹህ ፦
በቤተሰብ ወይም በአሳዳጊዎች እንክብካቤ ምክንያት የመኖሪያ ፈቃድ መጠየቅ።
ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆች የሚሰጥ የመኖሪያ ፍቃድ የሚሰጠው ከ 18 ዓመት በታች መሆናቸው ሲረጋገጥ ነው። ጥያቄው በቀጥታ አካለ መጠን ካልደረሰው ታዳጊ ለፖሊስ ዋና መስሪያ ቤት ፍልሰት ቢሮ ወይም በአብዛኛዎቹ ጉዳዮች ከሞግዚቱ ወይም የመቀበያ ማዕከሉ ኣስተዳዳሪ ፊት መቅረብ አለበት ፡፡ የመኖሪያ ፈቃዱ ለአካለ መጠን እስከሚደርስ ድረስ ይሠራል ፡፡
ለዓለም አቀፍ ጥበቃ የቀረበው ማመልከቻ በትውልድ አገራቸው ግጭትን ፣ ስደትን ፣ ስቃይን ፣ ጥፋተኛነትን ወይም ሌላ ኢ፡ሰብዓዊ አያያዝን የሚፈሩ ታዳጊዎችን ይጠብቃል ፡፡
በሂደቱ ውስጥ ሁሉ አንተን የሚረዳ ሞግዚት ወይም ቱቶር በሚገኝበት በፖሊስ ዋና መስሪያ ቤት ለዓለም አቀፍ ጥበቃ ማመልከት ትችላለህ፡፡ ማመልከቻህ ለምርመራ ወደ ሚጠራው የግዛቱ ኮሚሽን (CT) ይቀርባል ፡፡ በኋላ ፣ ኮሚሽኑ የሚሰጥህ እውቅና፤ ዓለም ዓቀፍ የስደትኞች ጥበቃ (ስታቱስ ዲ ሪፉጃቶ)፣ ንኡስ ጥበቃ (ፕሮተስዮነ ሱሲድያርያ) ወይም ልዩ ጥበቃ (ፕሮተስዮነ ስፔቻለ) ናቸው። እነዚህ፡ ወራት ሊጠይቁ የሚችሉ አሰራሮች ናቸው።
ለማህበራዊ ጥበቃ ምክንያቶች የሚሰጥ የመኖሪያ ፈቃድ ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆች፡ ከጥቃቅን ጥቃቶች ወይም የወንጀል ሰለባዎች እንደ ዝሙት ብዝበዛ ፣ ባርነት ፣ ህገወጥ የሰዎች ዝውውርና ወሲባዊ ጥቃትን ይጠብቃል። ጥያቄህን በሞግዚትህ ወይም በቱቶርህ ፊት ለፖሊስ ጣቢያ ማቅረብ ትችላለህ፡፡ የፖሊስ ዋና መስሪያ ቤት የእውነቶችን ትክክለኛነት ካረጋገጠ በኋላ፡ ፈቃዱን ለመጀመርያ ግዜ ለ 6 ወር ሲሰጥ የአንድ አመት የእድሳት ዕድልም ሊኖር ይችላል።
በቤተሰብ ምክንያቶች የመኖሪያ ፈቃድ የሚያገኙ ለአካለ መጠን ያልደረሰ ልጆች፦
ምርጫው ከአካለ መጠን ያልደረሰ ልጅ ጋር በጥንቃቄ መገምገምና እንደ ሌሎቹ ፈቃዶች በፖሊስ ዋና መሥሪያ ቤት መቅረብ አለበት።
አሥራ ስምንት ዓመት ሲሞላው፡ ለአካለ መጠን ያልደረሰ የሚለው የተሰጠ እውቅና ይቛረጣል። ከአሳዳጊ እና ከማኅበራዊ አገልግሎቱ ጋር በመስማማት ዕድሜው 18 ዓመት ሳይሞላው ሁለት አማራጮች ይገመገማሉ ፦
አዎ በሌላ የአውሮፓ ግዛት ውስጥ ከዘመድህ ጋር መገናኘት ትችላለህ፡፡ በመቀላለህ ጥያቄ ላይ ቱቶርህ እና የመቀበያ ማዕከል ኦፕሬተሮች ይደግፉሃል፡፡ የአሰራር ሂደቱ የተወሰኑ ሰነዶችን ለፖሊስ ዋና መስሪያ ቤት ማስገባትና በውጭ ካሉ ዘመዶች ጋር ያለው ዝምድናና አንተን ለመንከባከብ ያላቸውን ችሎታ ማረጋገጥን ያካትታል፡፡
አዎ ፡ ወደ ትምህርት ቤት የመሄድ መብት አለህ፡፡ ለመመዝገብ ሞግዚትህ ወይም የመቀበያ ማዕከል ሥራ አስኪያጁ ይረዱሃል።
አዎ ፡ አንተ ህክምና የማግኘት መብት አለህ፡፡ ቱቶርህ የምዝገባህን ጥያቄ ለብሔራዊ ጤና አገልግሎት ለአከባቢው የጤና ባለሥልጣን ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
አሁን የደረስክ `ከሆነና ለባለስልጣናት እስካሁን ሪፖርት ካላደረጉ አሁንም ቢሆን የክልል ኮድ ካርድ STP (Straniero Temporaneamente Presente) በመስጠት የጤና እንክብካቤ የማግኘት መብት አለህ፡፡ በዚህ ድረገጽ www.jumamap.it/map ላንተ በጣም የቀረበውን የጤና አገልግሎት ማግኘት ትችላለህ፡፡
ለጥገኝነት ጠያቂዎች እና ለስደተኞች ከክፍያ ነፃ ቁጥር – Numero verde (አርቺ ፡ በ ዩኤንኤችሲአር ድጋፍ – Arci – con il supporto di Unhcr)
ከ 35 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች በአስቶርጓሚዎች በሚያቀርበው ጣሊያን ውስጥ ነፃ የሕግ ድጋፍና የአገልግሎት አቅጣጫ ይሰጣል። ከሰኞ እስከ አርብ ከ 9፡ 30 እስከ 17:30 ድረስ ይሠራል።
ነፃ ቁጥር: 800 90 55 70
ለላይካ ሞባይል: 351 1 37 63 35
Helpline Minori Migranti (Save the Children)
ከሰኞ እስከ አርብ ከ 10:00 እስከ 17:00 ድረስ ለአካለ መጠን ላልደረሱ ሕፃናት ነፃ የብዙ ቋንቋ አገልግሎት የስልክ አገልግሎት
ነፃ ቁጥር:: 800 14 10 16
ለላይካ ሞባይል: 351 2 20 20 16
Miniila App (Missing Children Europe)
ለአካለ መጠን ላልደረሱ ስደተኛ ሕፃናት ጠቃሚ መረጃን የሚያቀርብ የስማርትፎን መተግበሪያ ፡፡ ዓላማው እንደ ሆስፒታል መተኛት ፣ ምግብ የሚገኝበትና በአቅራቢያው ያሉ የጤና አገልግሎቶችን በመሳሰሉ ጠቃሚ አገልግሎቶች ላይ መረጃ ተደራሽነትን ለማመቻቸት ነው።
አፕሊኬሽኑ ለማውረድ: https://miniila.com/
U-Report on the Move (Arci – con il supporto di Unicef – አርቺ በ ዩኒሴፍ ድጋፍ)
በጣሊያን ውስጥ ለአካለ መጠን ያልደረሱ እና ለወጣት ስደተኞች የተሰየመ መድረክ: መረጃና የህግ እና አስተዳደራዊ ድጋፍ ፣ ለአካባቢ አገልግሎቶች መረጃ ፣ የስነ፡ልቦና፡ማህበራዊ ድጋፍ ጣልቃ ገብነቶች (ከስነ–ልቦና ባለሙያዎች እና ከስነ–ልቦና ሐኪሞች ጋር የማዳመጥ ቦታ)።
እኛን ለማነጋገር: http://bit.ly/messageUROTM
JumaMap – Services for Refugees (አርቺ ፡ በ ዩኤንኤችሲአር ድጋፍ – Arci – con il supporto di Unhcr)
ጣልያን ውስጥ ለስደተኞች ፣ ጥገኝነት ጠያቂዎችና ለጥገኞች የብዙ ቋንቋዎች አገልግሎት ካርታ: የህግ እና የጤና ድጋፍ ፣ የስነ፡ልቦና፡ማህበራዊ ድጋፍ ፣ የጣሊያን ቛንቋ ትምህርቶች ፣ ፀረ፡ሁከት ማዕከላት ፣ ለአካል ጉዳተኞች የሚሰጠው ድጋፍ ፣ የሥራ አቅጣጫ ፣ ምግብ የሚበላበት ቦታዎችና የምግብ አሰራጭነት ፣ እንግዳ መቀበያ ፡፡
ሌሎች ጠቃሚ መገናኛቻዎች:
Telefono azzurro – ቴሌፎኖ አዙሮ
114 Emergenza Infanzia ሕፃናትና ጎረምሳዎች ለአደጋ በሚጋለጡበት የአደጋና የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ ሪፖርት ማድረግ ለሚፈልጉ ሁሉ የታለመ አንድ ድንገተኛ አገልግሎት መስጫ ነው። አገልግሎቱ በቀን ለ 24 ሰዓታት በሳምንት ለ 7 ቀናት ይሠራል ፡፡
የአደጋ ጊዜ ቁጥር: 114
የማዳመጥ መስመር: 1 96 96
ለጠፉ ታዳጊዎች ቀጥተኛ የስልክ መስመር
116000 የህፃናትና የጎረምሳ ወጣቶች የመጥፋት ጉዳዮችን በሚመለከት ሪፖርት ለማድረግ ነፃ አገልግሎት የሚሰጥ ነው ፡፡ የአገልግሎቱ ኦፕሬተሮች በቀን ለ 24 ሰዓታት ንቁ ሆነው ሪፖርቶችን ሰብስበው መረጃውን ለክልል ብቃት ላለው የፖሊስ ኃይል ይልካሉ። እንዲሁም የጠፋ መገኘቱን ወይም መታየቱን ሪፖርት ለማድረግ መደወል ይችላሉ።