Categories
Evidenza Lavoro

የ2023 የህዝብ ውድድር ማሻሻያ፡ በምርጫው ውስጥ ስደተኞችን እና የውጭ ዜጎችን ማካተት

የህዝብ ውድድሮች ማሻሻያ (በኦገስት 6 ቀን 2021 ወደ ህግ ቁጥር 113 የተለወጠው አዋጅ ቁጥር 80/2021) በህዝብ አስተዳደር ውስጥ የቅጥር ተደራሽነትን እና ጥራትን ለማሻሻል አስፈላጊ ለውጦችን ያስተዋውቃል። በጣም አስፈላጊ ከሆኑ ዜናዎች መካከል፡ ከጣሊያን ዜጎች በተጨማሪ ዓለም ኣቀፋዊ የጥገኝነት ዕውቅና ያለው መኖርያ ፍቃድ ያላቸው ሰዎችና የአውሮፓ ህብረት የመኖሪያ ወይም የረጅም ጊዜ የአውሮፓ ህብረት የመኖሪያ ፍቃድ ያላቸው ዜጎች ለህዝብ ውድ ድር ማመልከት ይችላሉ፤


ለወላጅነት፣ ለጾታ እኩልነት እና የተለየ የመማር እክል ላለባቸው ከፍተኛ ጥበቃዎች ዋስትና ተሰጥቷቸዋል።

  ለውድድር ሂደቱ መደምደሚያ፡ ከፍተኛው 6 ወራት ገደብ  ተዘጋጅቷል፤

– ለሕዝብ ውድድሮች ለማመልከት የ “inPA” ምልመላ ፖርታልን ወይም ድረ ገጽ ብቻ መጠቀም አስፈላጊ ይሆናል –  www.InPA.gov.it ። በድረ ገጹ ላይ መመዝገብ ነፃ ነው እና በ SPID ፣ CIE እና CNS መለያ ስርዓቶች ብቻ ሊከናወን ይችላል።

“SPID: ምን እንደሆነ፣ ማን ሊጠይቀው እንደሚችል እና እንዴት” የሚለውን ገጹን ይመልከቱ – SPID: a cosa serve, chi può richiederlo e come

ድረ ገጹ በህዝባዊ የስራ አቅርቦት እና ፍላጎት መካከል ያለውን ስብሰባ የሚያቃልል እና የሚያፋጥነውን የፈጠራ ዲጂታል ስርዓት በመጠቀም የህዝብ አስተዳደር ምልመላ ጥራትን ለማሻሻል ያለመ ነው።

ለበለጠ መረጃ እዚህ ጠቅ ያድርጉ Clicca qui per maggiori info

 4,020 Visite totali,  8 visite odierne

Categories
Asilo e immigrazione Evidenza

አዲስ የስደት አዋጅ 2023፡ በመግቢያ ፍሰቶች ላይ ቀላልነት፣ ከ”መደበኛ ያልሆነ” የኢሚግሬሽን እና የልዩ ጥበቃ ገደቦች ተቃራኒ

አዲሱ የኢሚግሬሽን አዋጅ (የደንብ ህግ 20/2023) ስራ ላይ ውሏል። ከዚህ በታች ዋናዎቹ ለውጦች:

“ያልተለመደ” ከኢሚግሬሽን ጋር በተያያዙ ወንጀሎች ላይ የቅጣት መጠን መጨመር፦

ከሕገወጥ ስደት ጋር በተያያዙ ወንጀሎች የተነሳ ሞት ወይም ጉዳትአዲስ ወንጀል፣ ይህም ለከባድ ቅጣቶች ይሰጣል፡

 • 10 እስከ 20 አመት ለአንድ ወይም ከዚያ በላይ ሰዎች ለከባድ ወይም በጣም ከባድ ጉዳቶች;
 • ለአንድ ሰው ሞት 15 እስከ 24 ዓመታት;
 • ለብዙ ሰዎች ሞት 20 እስከ 30 ዓመታት።

ማባረር፡

የጥፋተኝነት ውሳኔ ተከትሎ የታዘዙትን የመባረር ድንጋጌዎች ተግባራዊ ለማድረግ የዳኛው ውሳኔ ማረጋገጥ አስፈላጊ አይሆንም።

የፍሰት አዋጅ፡

 • የውጭ ሰራተኞችን ህጋዊ የመግቢያ ፍሰት እቅድ ለማውጣት አዳዲስ መንገዶች

ለበታች ሥራ ወደ ጣሊያን የሚገቡ የውጭ ዜጎች ኮታ ለአንድ ዓመት ብቻ ሳይሆን ለሦስት ዓመታት መሆኑ (2023-2025) ይገለጻል።

መደበኛ ያልሆነ የፍልሰት ትራፊክ አደጋ ላይ የሚዲያ ዘመቻዎችን የሚያስተዋውቁ ወንድ እና ሴት ሰራተኞች፡ በቅድምያ መብት ያገኛሉ።

 • ለውጭ አገር ዜጎች የበታች ሥራ የመግቢያና የመኖሪያ ፈቃድ ደንቦች ላይ ለውጦች

የውጭ ዜጎች ከጣሊያን ኩባንያዎች ጋር ያለው የሥራ ግንኙነት ጅምር ቀለል ያለ ይሆናል  እና የኑላ ኦስታው ሂደት የተፋጠነ ይሆናል፡ እንዲሁም ለወቅታዊ ስራዎች።

የስልጠና ፕሮግራሞች

በትውልድ አገራቸው ኮርስ ወስደው ያለፉ የውጭ ዜጎች፡ በጣሊያን እውቅና የተሰጣቸውና በሠራተኛ ሚኒስቴር የተደገፉ የሥልጠና ኮርሶች ያለፉ ወደ ጣሊያን እንዲገቡ ከፍሰቱ ድንጋጌ ኮታ ውጭ ሊጠይቁ ይችላሉ ።

የታደሰው የመኖሪያ ፍቃድ ያለው ጊዜ፡

ለቋሚ ሥራ ፣ ለግል ሥራ ወይም ለቤተሰብ መልሶ ማገናኘት የተሰጠው የመኖሪያ ፈቃድ እድሳት ከፍተኛው የሶስት ዓመት ጊዜ ሲሆን ቢያንስ ለሁለት ዓመት ይቆያል።

በልዩ ጥበቃ ላይ አዳዲስ ገደቦች

ለልዩ  ጥበቃ እውቅና ለማግኘት፣ የሚጠይቅ ሰው የግልና የቤተሰብ ህይወት ጥበቃን የሚያመለክት ማጣቀሻ ተሰርዟል።

ማስጠንቀቂያ፡ ለውጡ የሚመለከተው ከ 10/03/2023 ጀምሮ ለሚቀርቡ ማመልከቻዎች ብቻ ነው፣ ቀድሞ በ ኴስቱራ ቀጠሮ ካላቸው በስተቀር።

በፖሊስ ዋና መሥሪያ ቤት ቀጠሮ ለሌላቸው ነገር ግን ከ10/03/2023 በፊት ላመለከቱ፣ ማመልከቻው በፖሊስ ዋና መሥሪያ ቤት የቀረበበትን ኢ-መይል ያትሙ (እንዲያዙ) እናሳስባለን።

“በዘር፣ በፆታ፣ በቋንቋ፣ በዜግነት፣ በሃይማኖት፣ በፖለቲካዊ አመለካከቶች፣ በግላዊ ሁኔታዎች ወይም በማህበራዊ ጉዳዮች ምክንያት ስደትን ሊያስከትል ይችላል ተብሎ በሚገመገምበት ጊዜ” ልዩ ጥበቃ መስጠቱን ይቀጥላል  (ART 19, Comma 1 del TUI)

ቀደም ሲል 03/10/2023 በፊት የተሰጡ ልዩ ጥበቃ ፈቃዶች ለጥበቃ እውቅና የተሰጣቸው እናየግል እና የቤተሰብ ህይወትን ማክበርለሌላ አመት ሊታደስ ይችላል, እና ሁልጊዜ ወደ ሥራ ፈቃድ ሊለወጥ ይችላል። 

ከ 03/10/2023 በኋላ ለልዩ ጥበቃ ያሉ ጥያቄዎች 

የእኛ ምክር እንደ የጥገኝነት ጠያቂዎች: ለሰብአዊ መብት ጠባቂዎች እንደ አርቺ ለስደተኞች ከክፍያ ነፃ ቁጥር (800905570 ወይም +39 3511376335 ወይም ለ numeroverderifugiati@arci.it በመጻፍ) ወይም ታማኝ ጠበቃን በማነጋገር በማንኛውም ሁኔታ ማመልከቻ ማቅረብ ነው። ለልዩ ጥበቃ, ሰነዶችን ወይም ዝርዝር ዘገባን ከጥያቄው ጋር በማያያዝ እንዲሁም የግል ህይወት ገፅታዎችን (ማህበራዊ-ስራ ማካተትና / ወይም የቤተሰብ ህይወት) በስደተኞች ህግ በአንቀጽ 5 ኮማ  6 የቴስቶ ኡኒኮ ኣንቀጽ 8 ላይ: በሕገ መንግስት ኣንቀጽ 117 ግምት ውስጥ በማስገባት እሱም ሁልጊዜ መከበር ያለበት ሕግ ነው። 

Categories
Asilo e immigrazione Asilo e immigrazione Evidenza Evidenza Lavoro Lavoro

የውጭ ሀገር ሰራተኞች ወደ ሀገር ውስጥ ለመግባት አዲሱ የፍሰት ድንጋጌ ተሰራጭተዋል

... ጥር 26 ቀን 2023 የጠቅላይ ሚኒስትር  የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዲሴምበር 29 ቀን 2022 (የፍሰት ድንጋጌ) ታትሟል ይህም ለሥራ ወደ ጣሊያን የሚገቡ የውጭ አገር ሠራተኞችን ኮታ አስቀምጧል። 

ከፍተኛው የመግቢያ ብዛት 82,705 ሰዎች ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ፡

 • 44,000 ለወቅታዊ የሥራ ምክንያቶች;
 • 38,705 ለወቅታዊ ባልሆኑ የሥራ ምክንያቶች፣ ከእነዚህም ውስጥ፡-

የመኖሪያ ፈቃዶችን መለወጥ –  ከታች ከተዘረዘሩት የመኖርያ ፈቃድ ያላቸው ሰዎች ፈቃዱን ለመለወጥ መጠየቅ ይችላሉ፦

 1. ወቅታዊ የሥራ መኖርያ ፈቃዶች
 2. ለትምህርት ዓላማዎች የመኖርያ ፈቃዶች
 3. በሌሎች የአውሮፓ ህብረት አገሮች ውስጥ ያልተገደበ የመኖሪያ ፈቃድ

  እንዴት ማመልከት እንደሚቻል

  ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከነበረው የኣሰራር ሁኔታ በተለየ፡ ለሠራተኛው እንዲቀጠር የፈቃድ ጥያቄን ከመላኩ በፊት፣ አሠሪው ሥራውን ለመሙላት በብሔራዊ ክልል ውስጥ ያሉ ሌሎች ሠራተኞች እንደሌሉ አሠሪው ብቃት ካለው የቅጥር ማእከል ጋር ማረጋገጥ ይኖርበታል።

  ይህንን ማረጋገጫ ለመፈጸም አሠሪው ይህንን ቅጽ በመሙላት ለሠራተኞች ጥያቄ ወደ የቅጥር ማእከል መላክ አለበት። መመርያው እዚህ ኣንብብ guida per i datori/datrici di lavoro.

  የፍቃድ ጥያቄው ሊደረግ የሚችለው፡

  ሀ) የቅጥር ማእከል ለቀረበው ጥያቄ ምላሽ ካልሰጠ፣ ጥያቄው ከቀረበበት ቀን ጀምሮ በአስራ አምስት የስራ ቀናት ውስጥ፤

  ለ) በቅጥር ማእከል የተዘገበው ሠራተኛ ለቀጣሪው ለተሰጠው ሥራ ተስማሚ ካልሆነ

  ሐ) ከቅጥር ማእከል የተላከው ሠራተኛ ለቃለ መጠይቁ አሳማኝ ምክንያት በሌለበት ሲቀር፡ ከጥያቄው ቀን ጀምሮ ቢያንስ ከ 20 የሥራ ቀናት በኋላ።


  ከነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ አንዱ ከተከሰተ አሠሪው ለሥራ ፈቃድ ማእከል፡ በራሱ ማረጋገጫ የተጻፈ ሰነድ ከማመልከቻው ጋር በማያያዝ ማስታወቅ አለበት።

  በደንብ ያስተውሉ፡ በብሔራዊ ክልል ውስጥ ያሉ ሰራተኞች አለመኖራቸውን ማረጋገጥ፡ ለወቅታዊ ሰራተኞች እና በውጭ አገር የሰለጠኑ ሰራተኞች አስፈላጊ አይደለም። 

  ማመልከቻዎቹ ከቀረቡ 30 ቀናት በኋላ ምንም እንቅፋቶች ከሌሉ ፈቀዳው በቀጥታ ይወጣና ኑላ ኦስታው ይላካል – በቀጥታ በመስመር ላይ ከተላከ ፡ በትውልድ ሀገሮች የኢጣሊያ ዲፕሎማሲያዊ ተወካዮች (ኤምባሲዎች) ማመልከቻው ከቀረበበት በ 20 ቀናት ውስጥ የመግቢያ ቪዛ መስጠት አለባቸው ።
decreto flussi
Categories
aiuti sociali Asilo e immigrazione corsi Evidenza Lavoro Ucraina

አሶላቮሮ፡ ለስደተኞች የሥራና የድጋፍ አገልግሎቶች

አሶላቮሮ  የስራ የቅጥር ኤጀንሲዎች ብሔራዊ ማህበር፣ UNHCR ጋር በመተባበር ያስተዋውቃል፣ “አኮልየንሳኤላቮሮ ፕሮጀችት” ፦ ለዓለም አቀፍ ጥበቃ፣ ጊዜያዊ ጥበቃና ልዩ ጥበቃ ፈቃድ ተጠቃሚዎች የሥራ ስምሪት አገልግሎትና ተጨባጭ ድጋፍ ይሰጣል።

የሚሰጠው አገልግሎቶች

ጣሊያን ለሚደርሱት በቅጥር ኤጀንሲዎች ዋስትና ያለው ፡ ከክፍያ ነፃ ፡ ለማህበራዊ ማካተትና ስራ የማግኘት አገልግሎት ከሚሰጡ አገልግሎቶች መካከል፦ 

 • መምርያና የመጀመሪያ ስልጠና – የጣሊያን የስራ ገበያና የኤጀንሲ ስራ ግንዛቤን ለማሳደግ ያለመ የመጀመሪያ የመረጃ ስብሰባ ከክፍያ ነፃ። በስብሰባው ወቅት በኤጀንሲዎቹ በኩል ወደ አገራችን ለሚመጡት አገልግሎቶችና የአገልግሎቶች ካርታን ያቀርባሉ
 • የብቃት ሚዛን – የክህሎት ወይም የብቃት ሚዛን ለሰልጣኙ በጣም ተስማሚ ወደሆነው የስልጠና መንገድ ለመምራት ችሎታዎችን ለመቅረጽና ግላዊ ባህሪያቱን ለመተንተን የሚያስችል መሰረታዊ መሳሪያ ነው (የጣሊያን ቋንቋ እና ባህል መሰረታዊ ኮርስ ወይም ሙያዊ ስልጠና ኮርስ)።
 • መሰረታዊ የጣሊያን ኮርሶች – በኮርሱ ወቅት ሰልጣኞች ለምግብና ለማደሪያ ወጪዎች ክፍያ እንዲከፈላቸው መጠየቅ ይችላሉ እና በሰዓት € 3.50 አበል የማግኘት መብት አላቸው። በስልጠናው መጨረሻ ላይ የአንድ ጊዜ አበል € 1,000 ይከፈላል።
 • የሙያዊ ስልጠና ኮርሶች – በኮርሱ ወቅት ሰልጣኞች ለምግብና ለማደሪያ ወጪዎች ክፍያ እንዲከፈላቸው መጠየቅ ይችላሉ እና በሰዓት € 3.50 አበል የማግኘት መብት አላቸው። በስልጠናው ማብቂያ ላይ የአንድ ጊዜ አበል € 1,000 ይከፈላል (በመጀመሪያ የጣሊያን ቋንቋ እና ባህል መጨረሻ ላይ ካልተሰጠ)

ኮርሱን ለሚሳተፉ ሰዎች ያሉ መብቶች

በመሰረታዊ ወይም ሙያዊ ስልጠና ኮርስ ላይ የሚሳተፉ ወይም በቅጥር ኤጀንሲ የተቀጠሩ

የአለም አቀፍ ጥበቃ፣ ጊዜያዊ ጥበቃ እና ልዩ ጥበቃ ፈቃድ ያላቸው ተጠቃሚዎች አንዳንድ ጠቃሚ ድጎማዎች የማግኘት መብት አላቸው። በዝርዝር ሲታይ ፡-

 • የመዋዕለ ሕፃናት ድጎማ – ወርሃዊ መዋእለ ሕጻናት መዋጮ ቢበዛ € 150 ህጻኑ ሶስተኛ አመት እስኪሞላው ድረስ እና በማጣቀሻው ጊዜ ውስጥ የመዋዕለ ሕፃናት ክትትል እስኪጠናቀቅ ድረስ
 • ለትምህርት ድጋፍ – ለትምህርት የወጡትን ወጪዎች ለመደገፍ አንዳንድ ድጎማዎች እነሆ፡
 1. ለልጆቻቸው የማስተማሪያ ቁሳቁሶችና መጽሃፍት ግዢ ድጎማ (€ 200)
 2. በምሽት ኮርሶች ላይ ለሚማሩ ተማሪዎች መጽሃፍ ወይም ሌላ የማስተማሪያ ቁሳቁስ ግዢ ድጎማ (€ 200)
 3. ለዩኒቨርሲቲው ክፍያ ለከፈሉት ወጪዎች ድጎማ (€200)
 4. ለ 1 ኛ እና 3 ኛ ደረጃ የልምምድ ተማሪዎች መፅሃፍ ወይም ሌላ ትምህርታዊ ቁሳቁስ ለመግዛት ድጎማ  (€ 200)
 • ለጨቅላ ሕፃናት መሠረታዊ ፍላጎቶች ግዥ የሚከፈል ክፍያ – ለልጅዎ እንክብካቤ አስፈላጊ የሆኑ ዕቃዎችን ለመግዛት ለሚያወጡት ወጭ እስከ ሶስተኛ ዓመት እድሜ ድረስ፣ ቢበዛ €800 መዋጮ። ጥያቄው ለእያንዳንዱ ልጅ ሊደረግ ይችላል። 
 • ለስነ ልቦና እርዳታን የተከፈለ መመለስ – ለአንድ ደንበኛ እስከ 200 ዩሮ ድረስ ለራስ ወይም ለቤተሰብ አባላት ለደረሰባቸው የስነ ልቦና ወጪዎች ድጎማ።

ለበለጠ መረጃ፡- Accoglienza&Lavoroፕሮጀክት Categories
Evidenza Regole e comportamenti

የፍሰት አዋጅ (ዴክሬቶ ፍሉሲ)፡ የማመልከቻው እስከ ሴፕቴምበር 30 መራዘም

decreto flussi

የመኖሪያ ፈቃዶችን ለመለወጥና የአውሮፓ ህብረት ላልሆኑ ዜጎች ወደ ውጭ አገር በማሰልጠን ፕሮጀክቶች ውስጥ ለመግባት ማመልከቻ የማቅረቢያ ቀነ፡ ገደብ እስከ መስከረም 30 ቀን 2022 ተራዝሟል። የፍሰት ድንጋጌው (የዲሴምበር 21 ቀን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ድንጋጌ) ወደ ጣሊያን ለመግባት የሚችሉትን የውጭ ሰራተኞች ከፍተኛውን ኮታ 69,700 አስቀምጧል።

 

በዚህ መሰረት፣ ማመልከቻዎች አሁንም ሊቀርቡ ይችላሉ:

 

1) ወደ የስራ መኖርያና ለግል ሥራ ፈጣሪነት የመኖሪያ ፈቃዶችን ለመለወጥ የጠየቁ

እስካሁን ካለው ኮታ ጋር ሲነጻጸር ወደ 45% የሚጠጉ ናቸው።

 

2)   የአውሮፓ ህብረት ላልሆኑ ዜጎች ወደ ጣሊያን መግባት በትውልድ አገራቸው የስልጠናና የትምህርት መርሃ ግብሮችን ላጠናቀቁ 
በእውነቱ፣ በትውልድ አገራቸው የትምህርትና የሥልጠና መርሃ ግብሮችን ላጠናቀቁ ሠራተኞች ቅበላ እስከ አሁን በቁጥር 100 ላለፈም (በሐምሌ 25 ቀን 1998 በወጣው የሕግ ድንጋጌ አንቀጽ 23 አንቀጽ 286 መሠረት)። 

 

እንዴት ማመልከት እንደሚቻል

የአሰራር ሂደቱን ለመጀመር አሰሪው (ጣሊያን ወይም ጣሊያን ውስጥ በህጋዊ መንገድ የሚኖር የውጭ ሀገር ዜጋ) የአውሮፓ ህብረት ያልሆነ ሰራተኛ ለመቅጠር ፍቃድ መጠየቅ አለበት በዚህ ሊንክ ኦንላይን በመሙላትhttps://nullaostalavoro.dlci.interno.it 

 

ማመልከቻ ለማስገባት እስከ ሴፕቴምበር 30 – 2022 ግዜ ይኖራል(ማርች 17 – 2022 የሚለውን ተራዝመዋል) እና ቀድመው ላስገቡ  በቅደም ተከተል ቅድሚያ ይሰጣል።

ማሳሰቢያ፡ አፕሊኬሽኑን ለመሙላት SPID መታወቂያ መያዝ ያስፈልጋል

በሴፕቴምበር 30 – 2022 የሚያበቃው Before You Go ፕሮጀክት እስካሁን በጣሊያን ውስጥ የስደት መንገድ ለመምራት ያሰቡ 583 ሰዎችን ለማካተት አመቻችቷል: በትውልድ አገራቸው ከባህላዊ፣ ከቋንቋ፣ ከማህበራዊ እና ከስራ እይታ አንጻር ማዘጋጀ። በፕሮጀክቱ ላይ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጎብኙ።
Categories
Covid Evidenza Salute

ከኤፕሪል 1 ጀምሮ ስለ ጭምብል እና አረንጓዴ ማለፊያ አዲስ ህጎች

decreto 17 marzo

ጭምብሉን እና አረንጓዴ ማለፊያን አጠቃቀም በተመለከተ አዲስ ህጎች (decreto del 17 marzo 2022): ከኤፕሪል 1 ቀን 2022 ጀምሮ በሥራ ላይ የሚውሉ ዋና ዋና ነገሮችና አዳዲስ ደንቦች እዚህ አሉ። 

በማርች 31 የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮቪድ-19 ያበቃል።  

 

ጭንብሎች

እስከ ኤፕሪል 30 – 2022 የኤፍኤፍፒ2 (FFP2) ጭንብል መጠቀም ግዴታ ነው:

 

 • በመጓጓዣዎች
 • ለሕዝብ ክፍት የሆኑ ትርኢቶች በሚካሄዱባቸው ቦታዎች 

 

በሥራ ቦታ፡ የመተንፈሻ መከላከያ መሳሪያዎችን መልበስ በቂ ይሆናል (ኤፍኤፍፒ2  ጭምብሎች መልበስ 

የግድ አይደሉም) ።

 

የአረንጓዴ ማለፊያ በሥራ ቦታ

ከኤፕሪል 1 ጀምሮ ሁሉም ሰራተኞች በመሰረታዊ አረንጓዴ ማለፊያ ወደ የስራ ቦታዎች መድረስ ይችላሉ።  ከ መይ 1 ጀምሮ ግን ከአሁን በኋላ አስገዳጅ አይሆንም።

 

እስከ ዲሴምበር 31 ቀን 2022 ክትባቱ በጤና ባለሙያዎች በሆስፒታሎች እና በአረጋውያን መንከባከቢያ ውስጥ ላሉ ሰራተኞች የግዴታ እንደሆነ ይቆያል: ይህንን ግዴታ ሳይወጡ የሚቀሩ ሰራተኞች ከስራ መታገዳቸውን ይቀጥላል። 

 

አረንጓዴ ማለፊያ እስከ ዲሴምበር 31 ድረስ ለአረጋውያን ጎብኚዎች (RSA) ፣ በሆስፒታልና በሆስፒታል ክፍሎች የግዴታ ሆኖ ይቆያል:  ነገር ግን ከኮቪድ ከተፈወሱና ግሪን ፓስ ከያዙ ታምፖነ ማድረግ ግዴታ አይሆንም።

 

ትምህርት ቤት

ለመዋዕለ ሕፃናት፣ አንደኛ ደረጃና መለስተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ እና ሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች: ቢያንስ 4 አዎንታዊ (ፖዚቲቭ) ጉዳዮች ባሉበት ጊዜ ክትትሉን በተገኙበት ይቀጥላሉ, እና ከስድስት ዓመት በላይ ለሆኑ ተማሪዎች፡ በመሃላቸው ፖዚቲቨ የሆነ ከተገኘ፡ ለ አስር ቀናት ፡ የ ፍፍጵ፪ ጭምብሎችን መጠቀም መጠቀም ኣለባቸውው። ሁሉም በኮቪድ ኢንፌክሽን ለተጠቁ ተማሪዎች ተለይተው ከሆነ፡ የርቀት ትምህርት እንቅስቃሴን (DAD) የሕክምና የምስክር ወረቀት ካላቸው መከታተል ይችላሉ። የፈጣን ወይም የሞለኪውላር አንቲጂን ምርመራ ኣሉታዊ ወይም ነጋቲቨ ውጤት ካላቸው ወደ ክፍል ለመመለስ በቂ ነው። 

 

ማግለልና ኳራንታይን 

ከኤፕሪል 1 ጀምሮ በኮቪድ ላይ አዎንታዊ ከሆነ ሰው ግንኙነት ያለው ማንኛውም ሰው እራሱን ማግለል የለበትም። ስለዚህ ማግለያው ተሰርዟል ነገር ግን ራስን መቆጣጠር እንዳለበት ተረጋግጧል:   ምልክቶች ካሉ ከተያዙ ከ 5 ቀናት በኋላ ታምፖነ ወይም ምርመራ ማድረግ አስፈላጊ ነው ፣ በጣም አስፈላጊ ለሆነ ጉዳይ ብቻ መውጣት ይችላሉ።

ለኮቪድ አዎንታዊ ለሆኑ ሰዎች መገለል ኣለባቸው፡ አሉታዊ ውጤት እስኪመጣ ድረስ እቤት ውስጥ መቆየት አለባቸው።

 

ሌሎች ዜናዎች

በተጨማሪ የማርች 17 አዋጅም ያስታውቃል:

 

 • የቀለም ዞኖች ስርዓት መጨረሻ
 • ከኤፕሪል 1 ጀምሮ ከቤት ውጭና የቤት ውስጥ የስፖርት መገልገያዎች አቅም ወደ 100% ይመለሱ።

 4,442 Visite totali

Categories
Asilo e immigrazione Evidenza Ucraina

የአውሮፓ መመሪያ ጊዜያዊ ጥበቃ አጸደቀ

 

አስፈላጊ ዜና
የአውሮፓ ህብረት በዩክሬን ውስጥ ካለው ጦርነት ጋር በተያያዘ ለጊዜያዊ ጥበቃ የሚሰጠውን መመሪያ ለመቀበል ወስኗል (direttiva 55/2001).
የዩክሬን ዜጎች፣ ጥገኝነት ጠያቂዎች፣ የአለም አቀፍ ጥበቃና የረጅም ጊዜ የመኖሪያ ፍቃድ በዩክሬን የሚኖሩና የቤተሰባቸው አባላት ታዳሽ የመኖሪያ ፍቃድ የማግኘትና የሚከተሉትን አገልግሎቶች የማግኘት መብት አላቸው:
ትምህርት ቤት
ሥራ
መጠለያ
ማህበራዊ እንክብካቤ
የጤና ጥበቃ

አስተውል
ጣሊያን የዚህን መመሪያ ማስፈጸሚያ ድንጋጌ እስካሁን አላወጣችም። ሂደቶቹ ሲገኙ እንገልጸዋለን።


ይህ በእንዲህ እንዳለ ማስታወስ የምንፈልገው:
ቪዛ እና ፍቃድ ሳያስፈልግ በጣሊያን ለ፺ ቀናት መቆየት ይቻላል። ለማየት እዚህ ተጫን (clicca qui per maggiori informazioni)
በተገን ጠያቂዎች መቀበያ ማእከላት እንደ(SAI) እና በማዘጋጃ ቤቶች በሚተዳደረው የአቀባበልና ውህደት ስርዓት (ጽዓዒ) ማእከላት የእንግዳ መቀበያ ቦታ ለመጠየቅ ይቻላል (clicca qui per maggiori informazioni)

 

ወደ ዩክሬን የድንገተኛ አደጋ ክፍል ሂድ

Vai alla sezione Emergenza Ucraina
Categories
Asilo e immigrazione Evidenza Faq Ucraina

FAQ – Richiesta di Protezione Internazionale

[ITALIANO ]  [UCRAINO – український] [RUSSO – РУССО] [INGLESE – ENGLISH]

  • ጣሊያን እንደደረስክ፣ ወደ ድንበር ፖሊስ መሄድ 
  • በማንኛውም ጊዜ በፖሊስ ዋና መሥሪያ ቤ ትየኢሚግሬሽን ቢሮ (ጁማ ሊንክ ገብተህ ተመልከት

1) ፍላጎትህን ግልጽ ማድረግ ለመጀመሪያ ጊዜ ፖሊስ ጣቢያ ስትሄድ ለጥገኝነት ማመልከት እንደምትፈልግ መናገር አለብህ ወይም ስምህን፣ የአባት ስምህን፣ የትውልድ ዘመንህን ወዘተ የምትጽፍበትን ወረቀት ኣዘጋጅተህ  ጥገኝነት ለማግኘት ማመልከት እንደምትፈልግ በግልፅ መፃፍ ትችላለህ። 

ፖሊስ ጣብያው ከተዘጋ ለጥገኝነት ለማመልከት ቀጠሮ በመጠየቅ ኢሜል (ብቻህን ወይም ከጠበቃ ጋር) መላክ ትችላለህ።

2) የፖሊሱ ዋና መሥሪያ ቤት  ወረቀት ወይም ቸዶሊኖ (ማህተም እና ፊርማ ያለው) ይሰጥሃል፡ እንዲሁምየጥገኝነት ጥያቄህ የምትሞላበት” የቀጠሮ ቀን  ይሰጠሃል።

 

3) የጥገኝነት ማመልከቻውን ማቅረብና ቺ – 3 (C-3) ማዘጋጀት። – 3 ን (C-3) ከጨረስክ በኋላ 6 ወራት የሚቆይና የሚታደስ የጥገኝነት ጠያቂ መኖርያ ፈቃድ መጠየቅ ትችላለህ፡ ይህን ፈቃድ ከተሰጠህ ከሁለት ወራት ቦኋላ መስራት ትችላለህ።

ጥንቃቄ! 

ያለ የመግቢያ ቪዛ ጣሊያን ከገባህና ኣሻራ (ፎቶሰኛላሜንቶ) ካልወሰዱብህ፣ የፖሊስ ዋና መሥሪያ ቤት ሁለት ቀጠሮዎችን ሊሰጥህ ይችላል፡ የመጀመሪያው ኣሻራ ለመውሰድ፣ ሁለተኛው 3 ለማድረግ። 

 

ኣስታውስ፡ ቺ-3 ማለት የመኖሪያ ፍቃድ አይደለም፣ ግን ሁል ግዜ ካንተ ጋር ይዘሀው መሄድ አለብህየጥገኝነት ማመልከቻውን ለማስገባት ምን ሰነዶች ያስፈልጋሉ?

 

ምንም ሰነዶች አያስፈልጉህም። በፖሊስ ጣቢያ የሚሰጡህን ቅጾች ትሞላለህ

 

ጥንቃቄ!

የመታወቂያ ሰነዶች ካንተ ጋር (ለምሳሌ ፓስፖርት) ካለህ ከ 4 ጉርድ ፎቶዎች ጋር ወደ ፖሊስ ዋና መስሪያ ቤት እንድትሰጣቸው ትጠየቃለህ።

ፓስፖርቱ በፖሊስ ዋና መሥሪያ ቤት ለሂደቱ በሙሉ ይቆያል።

በተመሳሳይ ጊዜ፣ ለጥገኝነት ማመልከቻህ ይጠቅማሉ ብለህ ያሰብከውን ሁሉንም ሰነዶች (ዲፕሎማዎች፣ ፎቶግራፎች፣ ጋዜጣ፣ መታወቅያ) እድሜህን፣ ዜግነት ህን፣ ያረፍክበትን ሀገርና ቦታ የሚያመለከቱ ሰነዶችንና የጥገኝነት ጥያቄህን ምክንያት ጨምሮ ማስረከብ ይጠበቅብሃል።

 

በደንብ አስተውል 

የት እንደምትኖር ለማወቅና ከሂደቱ ጋር የተያያዙ ሁሉንም ግንኙነቶች ላንተ ለመላክ አድራሻ ይጠየቃሉ። የጓደኞችህ እንግዳ ከሆንክ እና የእንግዳ ተቀባይነት መግለጫ ከሰጡህ፣ ካንተ ጋር ይዘህላቸው ሂድ!

 

የመቆያ ቦታ ከሌለህ በፕሬፌክተሩ ወይም በማዘጋጃ ቤቱ የሚተዳደር የህዝብ መቀበያ ማእከል የመግባት መብት አለህ፦ በዚህ ማእከል ውስጥ ለሂደቱ ጊዜ (ሂደቱ እስከሚያልቅ) የመቆየት መብት አለዎት።

አድራሻ ባይኖርህም ለጥገኝነት ማመልከት መብት አለህ!

ለጥገኝነት ካመለከትክ በኋላ የፖሊስ ዋና መሥሪያ ቤት ሰነዶቹን ወደ ግዛቱ ለሚመለከተው የክልሉ ኮሚሽን ይልካል (ብዙውን ጊዜ በእያንዳንዱ የጣሊያን ክልል ቢያንስ አንድ አለ)

የግዛት ኮሚሽኑ ከጥገኝነት ጠያቂዎች ጋር ቃለ መጠይቅ የሚካሄድበትና ለአለም አቀፍ ጥበቃ ማመልከቻ ውሳኔ የሚሰጥበት ቢሮ ነው።

በኮሚሽኑ ውስጥ ከሚደረገው የቃለ መጠይቅ ውጤት፣ የሚከተሉት ውሳኔዎች ማስተላለፍ ይችላሉ:

 

 • የዓለም አቀፍ የስደተኛ (አዚሎ ፖሊቲኮ) ጥበቃ እውቅና፦ በዚህ ጉዳይ ላይ “ከፍተኛ” የዓለም አቀፍ ጥበቃ እውቅና አግኝተሃል፡, ምክንያቱም ወደ ትውልድ አገሩ በሚመለስበት ጊዜ እንደሚሰጋና አደጋ እንደሚያጋጥመው ይቆጠራል። በዚህ ውሳኔ ወደ ፖሊስ ዋና መሥሪያ ቤት በመሄድ “ጥገኝነት” የሚሰጥ በየ 5 ዓመቱ የሚታደስ የመኖሪያ ፈቃድና ጥገኝነት ላገኙ የሚሰጠውን የጉዞ ሰነት ማግኘት ትችላለህ።
 • የፕሮቴስዮነ ሱሲድያርያ ጥበቃን እውቅና መስጠት፦ ሌላው የአለም አቀፍ ጥበቃ አይነት ሲሆን ይህም 5 አመት የሚታደስ የመኖሪያ ፍቃድ የማግኘት መብት ይሰጠሃል። 
 • ልዩ (ፕሮቴስዮነ ስፔቻለ) ጥበቃን እውቅና፦: ይህ “ብሔራዊ” ጥበቃ ዓይነት ፈቃድ ነው፣ እና በፖሊስ ዋና መሥሪያ ቤት ውስጥ 2 ዓመት የመኖሪያ ፈቃድ፣ ታዳሽ እና ወደ ሥራ ሊለወጥ የሚችል፣ የማግኘት መብት ይሰጥሃል።
 • ለሕክምና አስፈላጊነት ወይም ለጤንነት ችግር የሚሰጥ እውቅና: “ከባድ የስነ፡ልቦና፡አካላዊ ሁኔታዎች ወይም ከከባድ በሽታመኖሩን በሚታወቅበት ጊዜ ቢበዛ ለአንድ ዓመት ፈቃድ ይሰጠሃል፡ የሚታደስና ለስራ ምክንያቶች ፈቃድ ሊቀየር ይችላል።  
 • መከልከል (ዲኔጎ) ኮሚሽኑ የአለም አቀፍ ወይም ልዩ ጥበቃ እውቅና ለማግኘት ሁኔታዎች አለመኖራቸውን ገምግሟል።

 

ጥንቃቄ!

ለአዲስ ቃለ መጠይቅ ልትጠራም ትችላለህ። ይህ ሊሆን የሚችለው ሙሉውን የግል ታሪክህ ለመረዳትና ውሳኔ ለመስጠት በቂ ካልሆነ ነው። መጨነቅ አያስፈልግም፣ ይህ ማለት ውስብስብ ጉዳይ ነው ማለት ነውበቃለ መጠይቁ ወቅት ሁል ጊዜ ያሉህን መብቶች፦

 • ቃለ መጠይቁን አፍ በፈታህበት ቋንቋህ (ወይንም በደንብ በምታውቀው ቋንቋ )ወይም በገለልተኛ አስተርጓሚ እርዳታ መምራት;
 • ለኮሚሽኑ የምታጋረው መረጃ ምስጢራዊነት – (ከሀገርህ ባለስልጣናት ጋር የማይጋራ);
 • በጠበቃ መታገዝ;
 • ከአስተርጓሚው ጋር ያለው አለመግባባት መናገር;
 • እረፍት መጠየቅ;
 • ከባድ ሁኔታዎች በሚያጋጥሙበት ጊዜ እንዲቋረጥ መጠየቅ (ለምሳሌ በጤና ምክንያት);
 • ቃለ መጠይቁን እንደገና እንዲነበብልህ ማድረግና ማንኛውም ዓይነት እርማቶች የሚያስፈልጉ ከሆነ ማረም;

በንድፈ ሀሳብ፣ ማመልከቻህን ባቀረብክ በአንድ ወር ውስጥ ለአለም አቀፍ ጥበቃ ማመልከቻህ ምላሽ ማግኘት አለብህ። በተግባር ግን፣ ብዙ ጊዜ ሊወስድ ይችላል፣ እና በእርግጠኝነት ማወቅ አይቻልም። 

 

አስተውል

ለሂደቱ በሙሉ የጥገኝነት ጠያቂ መኖርያ ፈቃዱ ባለቤት ሆነህ ትቆያለህ። የኮሚሽኑ መልስ፡ እምቢተኝነት (“አሉታዊ”) ከሆነ፣ አሉታዊውን ውሳኔ ለፍርድ ቤት  መቃወም (“ይግባኝ”) ማለት ትችላለህ። ሂደቱ እስካለ ድረስ፣ የ 6 ወር የጥገኝነት ጠያቂ ፈቃዱን ለማደስ መብት አለህ። ፍርድ ቤቱ የሚሰጠው የጥበቃ ዓይነት፦ (ዓለም አቀፍ ጥገኝነት (ኣዚሎ) ንዑስ ጥበቃ (ፕሮቴስዮነ ሱሲድያርያ) ልዩ ጥበቃ (ፕሮቴስዮነ ስፔቻለ) ሕክምና(ኩረ መዲከ) እነዚህ እውቅናዎች መስጠት ወይም በአሉታዊ መልኩ ሊወስን ይችላል። ፍርድ ቤቱ አሉታዊውን መልስ ከሰጠህ፣ ለአለም አቀፍ ጥበቃ አዲስ ማመልከቻ ለማቅረብ መገምገም ትችላለህ (ለጥገኝነት ለማመልከት አዳዲስ ምክንያቶች ካሉ “እንደገና መድገም” (ሬተራታ) ይባላል), ወይም ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ። ትኩረት፥ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ማለት የፍርድ ቤቱን አሉታዊነት ወዲያውኑ አያግድም፣ ስለዚህ የመባረር ትእዛዝ እንዳይሰጡህ ስጋት አለ!
በቂ ገንዘብ ከሌልህ አሁንም ለጠበቃ ይግባኝ ማለት ትችላለህ፣ “ነጻ የህግ ድጋፍ” (ግራትዊቶ ፓትሮቺኞ)ተብሎ የሚጠራውን አገልግሎት በማግኘት ግዛቱ ለጠበቃው የሚከፍለው ይሆናል: በዚህ ጉዳይ ላይ ጠበቃው የገቢህን መጠን የምታረጋግጥበት ራሽን የምታዘጋጀው አንዳንድ ወረቀቶች እንድትፈርም ያደርጋል።

የታመነ ጠበቃ የማታውቅ ከሆነ ወደ አንተ ቅርብ ወደሚገኝ ፍርድ ቤት ሄደህ ያሉትን የህግ ባለሙያዎች ዝርዝር ማየት ትችላለህ፣ ከፈለግክ በአቅራብያህ የሚገኘውን አርቺ (ARCI) ክበብ ፈልግ፡ በአቅራቢያህ ወደሚገኙ የህግ ኣማካሪዎች ሊመራህ ይችላል። በ jumamap.it  በከተማ ውስጥ የህግ አገልግሎቶችን ዝርዝር ማግኘት ትችላለህ።

ያለበለዚያ ለጥገኝነት ጠያቂዎች እና ለስደተኞች ነፃ የስልክ ቁጥር መደወል ትችላለህ። ከመደበኛ ስልክ (800 905 570) እና ከሞባይል ስልክ (3511376335) መደወል የሚቻልበት ነፃ የስልክ መስመር ሲሆን በዚህም የህግ ድጋፍ እና የማማከር አገልግሎት ማግኘት ትችላለህ።

 

Categories
aiuti sociali Evidenza Minori

አሰኞ ኡኒኮ ፋሚልያረ

አሰኞ ኡኒኮ ፋሚልያረ ማለት በአንዳንድ ሁኔታዎች በእያንዳንዱ ቤተሰብ ስር ለሚኖሩ ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆች 21 ዓመታቸው እስከሚደርሱ የሚሰጥ የኤኮኖሚ ድጋፍ ነው።   

ቸኩ ወይም አሰኞው የሚከፈለው  ከኢንፕስ በኢሴ (ISEE) ወይም የቤተሰብ የኤኮኖሚ ሁኔታ በሚያመላክተው መሰረት ነው። ድጎማውን ለማግኘት ቤተሰቦች ከጃንዋሪ 1 2022 ጀምሮ ለኢንፕስ (INPS) ወይም እንደ  ፓትሮናቶ ደጋፊ ተቋማት ማመልከት ይችላሉ። ተቆራጩ ከመጋቢት 2022 ጀምሮ INPS ይከፈላል። 

ቼኩን እስከ ጁን 302022 ድረስ መጠየቅ ይቻላል፣ እንዲሁም ላለፈው ወርሃዊ ክፍያ (ከማርች 2022 ጀምሮ) የማግኘት መብት አለው።

ለቼኩ ማን ማመልከት ይችላል

ለቼኩ ለማመልከት የሚከተሉትን መስፈርቶች ሊኖርዎት ይገባል ፦

 • የጣልያን ዜግነት፣ ወይም የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገር (ወይም የቤተሰባቸው አባላት) ዜግነት፣ ወይም የአውሮፓ ህብረት አባል ያልሆነ ዜጋ በመሆን የአውሮፓ ህብረት የመኖሪያ ፍቃድ የረጅም ጊዜ የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸው፤ ወይም ከስድስት ወር በላይ የሥራ እንቅስቃሴን ለማከናወን የተፈቀደ የሥራ ፈቃድ መኖርያ ፈቃድ የተሰጣቸው መሆን፤ ወይም በጣሊያን ውስጥ ከስድስት ወር ለሚበልጥ ጊዜ ለመቆየት በተፈቀደላቸው በምርምር ምክንያቶች የመኖሪያ ፈቃድ ባለቤት መሆን;
 • ጣሊያን ውስጥ የገቢ ግብር ክፍያ የሚያከናውኑ;  
 • በጣሊያን ውስጥ ቢያንስ ለሁለት ዓመታት መኖር ምንም እንኳን ቀጣይ ባይሆንም ወይም ቢያንስ ለስድስት ወር ቋሚ ወይም ቋሚ ያልሆነ የሥራ ውል ያላቸው

የቼኩ ባህሪያት 

 • ድጎማው ሁለንተናዊ ነው ሁሉም የገቢ ምንጮች መብት ኣላቸው ቀጣይ የገቢ ምንጭ (ISEE) በቀነሰ መጠኑ ይጨምራል።
 • ድጎማው አዲስ ልጅ ከተወለደ በ 120 ቀናት ውስጥ፣ ከተፀነሰ 7 ኛው ወር ጀምሮና ለእያንዳንዱ በቤተሰቡ ስር ያለ ልጅ እስከ 21 አመት ድረስ ሊጠየቅ ይችላል።
 • ዕድሜያቸው 18 በላይ ለሆኑ እና 21 ዓመት በታች ለሆኑ በቤተሰብ ስር ያሉ ልጆች ለድጎማው ብቁ ለመሆን ከሚከተሉት ሁኔታዎች ውስጥ አንዱን ማሟላት አለባቸው:
  • የትምህርት ቤት ሙያዊ ስልጠና ኮርስ ወይም የዲግሪ ኮርስ ለሚከታተሉ;
  • የስራ ልምድ ኮርስ የሚከታተልና አጠቃላይ ገቢ በዓመት 8000 በታች ነው;
  • ወይም እንደ ሥራ አጥነት ተመዝግቦ ከሕዝብ የሥራ ስምሪት አገልግሎት ጋር ሥራ እየፈለገ ነው;
  • ሁለንተናዊ ሲቪል ሰርቪስ ያካሂዳል።
 • ማመልከቻው አንዴ ከቀረበ በኋላ ቼኩ ከማርች ወር ጀምሮ  በማንኛውም ሁኔታ 60ቀናት ውስጥ ይታወቃል።
 • ቼኩ የሚከፈለው በዜግነት ገቢ ተጠቃሚዎች ካልሆነ በስተቀር በባንክ ሒሳብ ቁጥር (IBAN) ወይም በአገር ውስጥ የባንክ ሒሳብ ማስተላለፍ ነው።
 • ድጎማው አጠቃላይ የቤተሰብ ገቢን አይነካም።

ማሳሰቢያ: በማመልከቻው ጊዜ, ተመጣጣኝ ቼክ ለማግኘት የኢሴ (ISEE) የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይቻላል. የኢሴ የምስክር ወረቀት ሳይያያዝ ማመልከቻ ከገባ፣ ገቢ ምንም ይሁን ምን ኢንፕስ (INPS) አነስተኛውን መጠን ብቻ ይከፍላል።

የድጎማው ተኳኋኝነት ከሌሎች ማህበራዊ እርዳታዎች ጋር

ከማርች 2022 ጀምሮ፣ ድጎማው ልጆች ላሏቸው ቤተሰቦች ያነጣጠሩ አንዳንድ የመንግስት ኢኮኖሚያዊ ድጎማዎችን ይተካል።

 

 • አሰኞ ፋሚልያረው የወሊድ ጉርሻን (የነገ እናት ቦነስ) የወሊድ አበል (የህፃን ቦነስ) ኣሰኞ ፋሚልያረ (የቤተሰብ አበል) እና ከ21 አመት በታች ለሆኑ ከቤተሰብ የሚኖሩ ልጆች የሚቀነሱትን ይተካል። 
 • አሰኞ ፋሚልያረው ወይም የቤተሰብ የኤኮኖሚ ድጎማ፡ ከዜጋው ገቢና ከህፃናት እንክብካቤ ድጎማ ጋር ተኳሃኝ ነው።

ማሳሰቢያ፡ የዜግነት ገቢን አስቀድመው ከተቀበሉ፣ ኣሰኞ ፋሚልያረው ቀጥሎ ይቀበላል።

የቼኩን መጠን ማመሳሰል 

በዚህ ድረ ገጽ በመግባት ቼኩን፡ በኢንፕስ (INPS) ተመሳሳይ ኣሰራር ማስላት ይችላሉ።:

https://servizi2.inps.it/servizi/AssegnoUnicoFigli/Simulatore

ከአሰኞ ፋሚልያረው የተገለሉ ተጠቃሚዎች

በአሁኑ ወቅት፣ ቼኩን ለማግኘት ከተዘረዘሩት የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸው ውጪ አንዳንድ የዜጎች ምድቦች አሁንም አልተካተቱም። በዚህ ረገድ፣ ይህንን በሚመለከት ማንኛቸውም ለውጦች ካሉ፣ በዚህ ገጽ ላይ ይቀርባሉ።

እንዴት ማመልከት ይቻላል – ለማመልከት ወደ ኢንፕስ (INPS) ድህረ ገጽ መግባት አለባቹህ:

https://serviziweb2.inps.it/PassiWeb/jsp/spid/loginSPID.jsp?uri=https%3a%2f%2fservizi2.inps.it%2fservizi%2fAssegnoUnicoFigli&S=S

ወይም 803164 (ከመደበኛ ስልክ) ወይም 06164164 (ከሞባይል ስልክ) ይደውሉ ወይም በኢንፕስ 0 በታወቁ ፓትሮናቶዎች በኩል ይጠይቁ  https://www.inps.it/servizi-online/servizi-per-i-patronati/informazioni/gli-enti-di-patronato

 

ጣልያንኛ ስለማትናገሩ አስተርጓሚ ከፈለጋቹህ ለጥገኝነት ጠያቂዎች እና ስደተኞች ነፃ የስልክ ቁጥር (አርቺ ARCI) ያግኙን 800 905 570 ለላይካ ሞብይል፥ 3511376335 assegno unico
Pidgin English
Bambara
Pular
Soninke
Categories
Covid Evidenza Salute

ከጃንዋሪ 10 በኋላ የክትባት ግዴታና አረንጓዴ ማለፊያ-አዲሱ ህጎች

obbligo vaccino over 50

በጃንዋሪ 10 – 2022፣ በክትባትና በአረንጓዴ ማለፊያ ላይ ያሉትን ህጎች የሚያድስ አዲስ አዋጅ ተግባራዊ ሆነ። ማን የግዴታ ክትባት መውሰድ አለበት? ሱፐር አረንጓዴ ማለፊያን ማሳየት አስፈላጊ የሚሆነው መቼ ነው እና አሁንም የአረንጓዴ ማለፊያን መያዝ በቂ የሚሆነው መቼ ነው? እስከ ማርች 31 ቀን 2022 ወይም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እስኪያበቃ ድረስ በሥራ ላይ የሚቆዩት በአዲሱ አዋጅ የተጠቀሱት አንዳንድ በጣም አስፈላጊ ህጎች እዚህ አሉ።

በመጀመሪያ ደረጃ: ከጃንዋሪ 10 ጀምሮ የሶስተኛውን መጠን ለመቀበል ጊዜው ይቀንሳል፦ ከ ሁለተኛው ክትባት በኋላ ከ 5 ወራት ይልቅ ከ 4 ወራት  በኋላ ሊከናወን ይችላል። በተጨማሪም በፌብሩዋሪ 1 ላይ አረንጓዴ ማለፊያ 9 ወደ 6 ወራት ይቀንሳል

ከዚያ ለአንዳንድ ልዩ ምድቦች ደንቦች አሉ-የትኞቹን እንይ ።

50 በላይ 

አዲሱ ድንጋጌ ከታች ለተጥቀሱት እንዲከተቡ ያስገድዳል

 • ሁሉም የጣልያንና የውጭ ዜጎች፣ ቢያንስ 50 አመት የሆናቸው (ወይ እስከ ጃንዋሪ 15 የሚሞላቸው፣ በጣሊያን የሚኖሩ ወይም በአገራችን መኖርያ ፈቃድ ያላቸው፣ በብሔራዊ የጤና አገልግሎት ውስጥ የተመዘገቡም ያልተመዘገቡም 

የሕክምና የምስክር ወረቀት ማሳየት የሚችሉት ከክትባት ግዴታ ነፃ ናቸው። የአካባቢ የጤና ባለስልጣን (ASL) በሀኪሙ አስተያየት መሰረት ከፀረ SARS-CoV-2 ክትባት እንደማይወስድ የምስክር ወረቀት ይሰጣል በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በጉዳዩ ላይ የሰጠውን ሰርኩላር በማክበር።

ከፌብሩዋሪ 15 ቀን 2022 ጀምሮ ከሃምሳ በላይ የሆናቸው ሠራተኞች ወደ ሥራ ቦታው በሚገቡበት ጊዜ የተጠናከረ አረንጓዴ ማለፊያ የሌላቸው፣ የሰሩበት የመከፈል መብት ሳይኖራቸው ያለ ምክንያት ከስራ እንደቀሩ ይቆጠራሉ፡ ነገር ግን የዲሲፕሊን መዘዞች ሳይኖር እና የስራ መብታቸው እንደተጠበቀ ሆኖ።

ከፌብሩዋሪ 15 እስከ ጁን 15 ድረስ የሱፐር አረንጓዴ ማለፊያ በስራ ቦታም ግዴታ ይሆናል። የእጅ ባለሞያዎችና ፕሮፌሽናል ሰራተኞች ስራቸውን ለመስራት በሚሄዱበት ቤትም ይሁን በሌሎች መስርያ ቤቶች ወይም ጽ/ቤቶች  ሲሄዱ የሱፐር ግሪን ፓስ እንዲኖራቸው ይጠበቅባቸዋል።

  መሰረታዊ አረንጓዴ ማለፊያ 

      ከጃንዋሪ 20 ጀምሮ ለሚከተሉትን የግድ ይሆናል፦

 • ወደ ፀጉር አስተካካዮችን፣ የሴቶች ፀጉር ሰሪዎችና የውበት ባለሙያዎችን ለመሄድ 

ከፌብሩዋሪ 1 ጀምሮ የመሰረታዊ አረንጓዴ ማለፊያ ማሳየት ከታች ለተዘረዘሩት ኣስፈላጊ ይሆናል፦

 • ወደ ባንኮች ለመግባት
 • ወደ ፖስታ ቤት ለመሄድ
 • የምግብ ሸቀጦችና ፋርማሲዎችን ሳይጨምር ወደ ንግድ ተቋማትን ለመግባት 

ሱፐር አረንጓዴ ማለፊያ  

ከጃንዋሪ 10 ጀምሮ የግዴታ ይሆናል፦

 • በማንኛውም የህዝብ ማመላለሻ ውስጥ ለመግባት
 • ህዝብ ወደ ሚሰበሰብበት እንደ፡ ቡና ቤቶችና ሬስቶራንቶች፣ ሙዚየሞች፣ ሆቴሎችና ለመሄድ 
 • ወደ መዋኛዎችና  ጂሞች ለመሳተፍ  

ክትባቱን ያልወሰዱ 

ያልተከተቡ ሰዎች ከፌብሩዋሪ 15 ጀምሮ የሚሰራ የተጠናከረ አረንጓዴ ማለፊያ ለማግኘት የመጀመሪያውን መጠን እስከ ጃንዋሪ 31 ድረስ መውሰድ አለባቸው።

ክትባቱን ያልወሰዱ ከፌብሩዋሪ 1 ጀምሮ ከታች ወደ ተጠቀሱት መግባት ኣይችሉም፦

 • በማንኛውም የህዝብ ማመላለሻ
 • ወደ ቡና ቤቶችና ሬስቶራንቶች
 • ወደ ሆቴሎችና ሙዚየሞች  
 • ወደ መዋኛዎችና  ጂሞች 

ያልተከተቡ ሰዎች እንደ ፋርማሲዎች፣ ሱፐርማርኬቶች፣ የትምባሆና የፌራመንታ መደብሮች ያሉ መሰረታዊ ፍላጎቶችን ወይም አስፈላጊ ምርቶችን ወደሚሸጡ መደብሮች ብቻ መግባት ይችላሉ።

ደንቦቹን ለማያከብሩ ያሉ ቅጣቶች  

የክትባት ግዴታ እስከሚቀጥለው ጁን 15 ድረስ ፀንቶ ይቆያል። ከፌብሩዋሪ 1 ቀን 2022 ጀምሮ ክትባት ላልወሰዱት የአንድ ጊዜ የ100 ዩሮ ቅጣቶች ይተገበራሉ። ቁጥጥሩን የሚከናወነው በገቢዎች ኤጀንሲ ነው፡ በጤና ካርዱ እና በመታወቅያ መካከል ቁጥጥር ያደርጋሉ። የክትባት ግዴታውን በመጣስ ወደ ሥራ ቦታ ለሚገቡ ሠራተኞችም ቅጣቶቹ ይቀጥላሉ። የድንጋጌዎቹ መጣስ ከ600 እስከ 1500 ዩሮ ክፍያ ይቀጣል።  የንግድ ሥራ ባለቤቶች ቁጥጥሩን ካላከበሩ ቅጣቱ ከ 400 እስከ 1,000 ዩሮ ይደርሳል። 

 1,976 Visite totali